የጠቅላይ ሚንስትሩን የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በበርካታ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች ተካሄዱ

የጠቅላይ ሚንስትሩን የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በበርካታ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው። Image copyright Addisu Arega, OBN
አጭር የምስል መግለጫ የጠቅላይ ሚንስትሩን የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በበርካታ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች እየተካሄዱ ነው።

የጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድን የኖቤል ሽልማት በማስመልከት በበርካታ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች ተካሄዱ።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የ2019 የሰላም የኖቤል ሽልማትን ማሸነፋቸውን ተከትሎ ከ20 በማያንሱ የኦሮሚያ ከተሞች የደስታ መግለጫ ሰልፎች የተካሄዱት።

ከኦሮሚያ ከተሞች በተጨማሪም በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ እንዲሁም በድሬ-ደዋ ከተማ አስተዳደር የደስታ መግለጫ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ የ2019 የኖቤል የሠላም ሽልማት አሸናፊ ሆኑ

የኦሮሞ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ማዕከላዊ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አዲሱ አረጋ በፌስቡክ ገጻቸው ላይ በ19 ከተሞች የተደረጉ የሚገኙ ሰልፎችን ምስል አውጥተዋል።

የደስታ መግለጫ ሰልፎች ከተካሄዱባቸው ከተሞች መካከል፤ ወሊሶ፣ ጅማ፣ አጋሮ፣ በደሌ፣ መቱ፣ ጊንጪ፣ አምቦ፣ ነቀምቴ፣ አዳማ፣ ዱከም፣ ባቱ፣ ሻሸመኔ፡ ጉጂ፣ ነገሌ ቦረ፣ ቡሌ ሆራ፣ ሱሉልታ፣ ለገጣፎ ለገዳዲ፣ ፊቼ እንዲሁም በምዕራብ እና ምሥራቅ ሐረርጌ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ከተሞችም የድጋፍ ሰልፎች ተካሂደዋል።

ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ

አርብ ዕለት ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ የኖቤል የሰላም ሽልማትን እንዳሸነፉ ከተሰማ በኋላ ለድጋፍ ሰልፎቹ በማህብራዊ ሚዲያዎች ላይ ጥሪ ሲደረጉ ነበር።

በጅማ በተካሄደው የደስታ መግለጫ ሰልፍ ላይ እየተሳተፉ ከነበሩት መካከል አንድ ወጣት ለቢቢሲ "የደስታ ሰልፍ ላይ ነን። ጅማ ከተማ ልዩ የሆነ ስሜት ውስጥ ነው የምትገኘው" ብሏል።

ከባህር ዳር - አዲስ አበባ የሚወስደው መንገድ ተከፈተ

ሌላኛው የጅማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የሆነው ወጣት ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው አውቶብሰ ወደ ስታዲየም መምጣቱን ገልጾ "የዐብይ ሽልማት የእኛም ሽልማት ጭምር ነው" የሚል መፈክር ይዞ መውጣቱን ተናግሯል።

በሌላ በኩል በሻሸመኔ በተካሄደው የድስታ መግለጫ ሰልፍ ላይ ተሳታፊ የሆነው የከተማዋ ነዋሪዎች ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ ሰልፈኞቹ ደስታቸውን ከመግለጻቸው በተጨማሪ በወለጋና በጉጂ አካባቢዎች መንግሥት ጸጥታ እንዲያሰከብር ድምጻቸውን አሰምተዋል ብሏል።