ዕድሜያችን የማቱሳላን ሲሶ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን?

ዕድሜያችን የማቱሳላን ግማሽ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን? Image copyright YURI_ARCURS/GETTY

ላለፉት ሁለት ክፍለ ዘመናት የሰው ልጅ አማካይ ዕድሜ ከዚያ ቀደም ከነበሩት ክፍለ-ዘመናት መሻሻል አሳይቷል፤ ከጊዜ ጊዜም እያደገ ነው።

በፈረንጆቹ 1840 ገደማ ሰዎች አማካይ የመኖሪያ ጣራቸው 40 ዓመት ነበር። የተመጣጠነ ምግብ፣ ንፅህና እንዲሁም የመጠለያ መስፋፋት ሲጀምር ጣራው ወደ 60 ያድግ ጀመር። ይህ የሆነው በ1900ዎቹ ነው።

20ኛው ክፍለ ዘመን ሁለት የዓለም ጦርነቶች የተስተናገዱበት ነው። እኒህ ጦርነቶች ከተካሄዱባቸው ዓመታት ውጭ ባሉት ዓመታት የሰው ልጅ የመኖር መጠን እያደገ እንጂ እየቀነሰ አልመጣም።

በተለይ 1970ዎቹ ላይ ስትሮክ እና ድንገተኛ ልብ ሕመምን የሚከላከሉ መድሃኒቶች መገኘታቸው ለውጥ እንዲታይ አደረገ።

አልፎም 21ኛው ክፍለ ዘመን መባቻ ላይ የሴቶች አማካይ ዕድሜ 80፤ የወንዶቹ ደግሞ 75 ደርሶ ነበር። ነገር ግን ድንገት ማሽቆልቆል ያዘ፤ በተለይ ደግሞ 2011 ላይ።

2015 ደግሞ ከፍተኛ የሞት መጠን የታየበት ዓመት ሆኖ አለፈ። የዛን ዓመት የነበረው የአየር ፀባይም እጅግ ለኑሮ አመቺ ያልሆነው ተብሎ ይነገራል።

ለዚህ ማሽቆልቆል ምክንያቱ ምን ይሆን ብለው የመረመሩ ባለሙያዎች ምናልባትም አማካይ የመኖሪያ ዕድሜው ጣሪያ መጨረሻ ላይ ደርሰን ይሆናል ሲሉ መላ ምት ያስቀምጣሉ።

ዕድሜ ጠገቧ የጥድ መፃሕፍት ቤት መደብር ትውስታ

ምድር ላይ በርካታ ዓመታት መኖራቸው በይፋ የተመዘገበላቸው ፈረንሳዊቷ ሴት ጂን ካልሜንት ሲሞቱ ዕድሜያቸው 122 ነበር። እቺን ዓለም ከተሰናበቱም 20 ዓመት አለፋቸው።

Image copyright copyrightALAMY
አጭር የምስል መግለጫ ምድር ላይ በርካታ ዓመታት መኖራቸው በይፋ የተመዘገበላቸው ፈረንሳዊቷ ሴት ጂን ካልሜንት ሲሞቱ ዕድሜያቸው 122 ነበር

አንድ ጥናት የሰው ልጅ ቢኖር ቢኖር 115 እንጂ እንደ አዛውንቷ ካልሜንት 122 አይረግጥም ሲል ቢያትትም ይህን ሃሳብ የሚቃወሙ በርካቶች ናቸው።

አሜሪካዊው የዘረ-መል ጥናት ባለሙያ ዴቪድ ሲንክሌር 'ላይፍስፓን' ብለው በሰየሙት መፅሃፋቸው ላይ የዘር ቅንጣቶችን በመደባለቅ በርካታ ዓመታት መኖር የሚችል ሰው መፍጠር ይቻላል ሲሉ ይሞግታሉ።

በዓለማችን የተሻለ የዕድሜ ጣሪያ ካላቸው ሃገራት መካከል ጃፓን አንዷ ናት። የጃፓን የዕድሜ ጣራ ከእንግሊዝ የተሻለ ነው። እንግሊዝ ደግሞ አሜሪካን በጠባብ ርቀት ትረመራታለች።

እስራኤል በቁፋሮ መስጂድ አገኘች

ባለፉት ጥቂት ዓመታት የቁጥሩ ማሽቆልቆል ያሳሳባቸው ሰዎች በርካታ መላምቶችን ያመጣሉ። ከእነዚህም በየጊዜው የተለያዩ ዓይነት በሽታዎች መምጣት አንዱ ነው። በልብ ሕመም እና ስትሮክ የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር እጅጉን እየቀነሰ ቢመጣም ከዕድሜ መግፋት ጋር ተያይዘው የሚመጡ [ዲሜንሺያን የመሳሰሉ] በሽታዎች ሌላ የሞት ምክንያት መሆን ጀምረዋል።

ወጣም ወረደ እንደ ማቱሳላ በርካታ መቶ ዓመታት መኖር ባንችል እንኳ ለምን መቶ አንደፍንም? የብዙዎች ጥያቄ ነው። ጥያቄው መልስ ባያገኝም፤ ጥናቱ ግን ቀጥሏል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ