'አይስታንድ ዊዝ አዲስ' እንቅስቃሴ

ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ድጋፍ ሰኔ 16/2010 መስቀል አደባባይ የተደረገ ሰልፍ ተሳታፊዎች Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ድጋፍ ሰኔ 16/2010 መስቀል አደባባይ የተደረገ ሰልፍ

በአዲስ አበባ የባለ አደራ ምክር ቤት ለጥቅምት 2/2012 ዓ. ም ተጠርቶ የነበረው ሰልፍ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መከልከሉን ተከትሎ የተቃውሞ ሰልፉ ተሰርዟል።

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን "በአዲስ አበባ ከተማ የተፈቀደም ሰልፍ ይሁን በሰልፉ የሚዘጉ መንገዶች የሉም" የሚለውን መግለጫ ተከትሎም ምክር ቤቱ ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ "ለሃገሪቱ ሰላምና ለህዝቧ ደህንነት ቅድሚያ በመስጠት ሰልፉን ሰርዟል" ብሏል።

ይህንንም ተከትሎ በትዊተር ላይ ""IStandWithAddis" በሚል ሃሽታግ ብዙዎች ተቃውሟቸውን አስፍረዋል።

"ለእናንተ ደህንነት ነው በሚል እንዳሰሩን ተገልፆልናል" የባላደራ ምክር ቤት አስተባባሪ

ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ

ምንም እንኳን ትዊተር ላይ የሰፈሩት ሃሳቦች ከሰልፍ ክልከላው አልፎ ሌሎች ከአዲስ አበባ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን ቢያንሸራሽርም ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ሃሽታጉን ተጠቅሞ ሲፅፍ በዋናነት ከሰልፉ መከልከል ጋር እንደሆነ ይናገራል።

"አዲስ አበባ ውስጥ የተቃውሞ ሰልፍ መደረግ አለበት። ይህ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው። መንግሥት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን እንዲህ አይነት ሰልፍ ለሚጠሩ ቡድኖችም ሆነ ግለሰቦች ጥበቃ የማድረግ ግዴታ አለበት" ይላል።

ለዚህም ኢትዮጵያ የተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍ ህጎችም ሆነ ህገመንግሥቱን ዋቢ በማድረግ እነዚህ መብቶች እንዲከበሩ እንደሚያስገድድም ያስረዳል።

የሃገሪቱ ህግ ሊከበር ይገባል የሚለው መስፍን፤ በህጉ መሰረት ሰላማዊ ሰልፍን እንዲከለክሉ መብት አይሰጣቸውም።

"ግዴታ አለባቸው፤ በቸርነት የሚሰጡት መብት አይደለም፤ ይሄ የተጠራው ሰልፍ ሊያስደስተን ወይም ላያስደስተን ይችላል ቁም ነገሩ እሱ አይደለም" ይላል።

በተለይም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ስልጣን መምጣታቸውን ተከትሎ የመጡ መሻሻሎች እንዳሉ ሆነው፤ ሁሉም ነገር በአንድ ጊዜ ይስተካከላል የሚል እምነት እንደሌለው ይናገራል።

ከዚህም ጋር ተያይዞ የሰልፉ መከልከል ለመስፍን ባያስደነግጠውም እንዲህ አይነት ጥያቄዎችና ትችቶች የሚቀርቡበት ዋናው አላማ ያለው ነገር የበለጠ እንዲሻሻል ከመፈለግ ነው ይላል።

"የዚህ ዋና አላማ ዜጎች የበለጠ መብት እያገኙ፤ የበለጠ ጥበቃ እየተደረገላቸው፤ መብቶቻቸውን መተግበር የሚችሉበት ሁኔታ እየሰፋ እንዲሄድ ነው" በማለት ያስረዳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከመጡ በኋላ የተደረጉ ጥሩ መሻሻሎች የሚያሻሙ እንዳልሆኑ የሚናገረው መስፍን "እነዚህ ነገሮች ወደ ኋላ ሊመለሱ ይችላሉ። ወደ ኋላ መመለስ የለም የሚል በጣም አሳሳች ሃሳብ ውስጥ መገባት የለበትም" ይላል።

የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል?

በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የሞቱ ሰዎች አጽም ለቤተሰቦቻቸው እየተሰጠ ነው

በተለይም የሃገሪቱ ዋና ከተማ እንዲሁም የሃገር ውስጥም ሆነ ዓለም አቀፍ አትኩሮት ያለባት ከተማ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ ማድረግ አለመቻሉ በጣም ትልቅ ትርጉም እንዳለውም ይናገራል።

የከተማ መስተዳድሩም ሆነ የፌደራል መንግሥት ወደፊት የሚመጡ የተቃውሞ ሰልፎችንም ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የመፍቀድ ግዴታ እንዳለባቸው አፅንኦት ሰጥቶ ይናገራል።

"ምንም አይነት ማብራሪያም ሆነ ምክንያት ብዙ ርቀት አያስኬድም። ለዚህኛው ሰልፍ መከልከል አንድ ምክንያት ሊሰጥ ይችላል። ከዚህኛው በኋላ ሌሎች የተቃውሞ ሰልፎች ሊመጡ ይችላሉ። ለሁሉም እንደዛ አይነት አንካሳ መልስ የሚሰጥ ከሆነ ወደነበርንበት ነው የምንመለሰው" ይላል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው በፊትም የተቃውሞ ሰልፍ እንጂ የድጋፍ ሰልፍ ይፈቀድ እንዳልነበር አስረድቷል።

"መለኪያውም የተቃውሞ የፍቃድ ሰልፍ መፍቀድ ነው እንጂ ድጋፍ መፍቀድ አይደለም። ድጋፍማ የሚጠይቀው ነገር የለም" የሚለው መስፍን በተለይም በቀጣዩ ምርጫን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ ባለችው ኢትዮጵያ የተለያዩ የተቃውሞ ድምፆች መድረክ ያስፈልጋቸዋል ይላል።

"እየተደረገ ያለው ነገር በጣም አሳዛኝ ነው፤ ጥሩ ምልክትም አይደለም። በተለይም ከፊታችን ምርጫ ይመጣል እያልን የተቃውሞ ድምፆችን መታገስ፤ እነሱ እንዲደሰሙ እድል መስጠት ነው የሚያስፈልገው። በእንደዚህ አይነት ከቀጠልን ትንሽ መጥፎ ምልክት ሊሆን እንደሚችል እሰጋለሁ" ብሏል።

ነገ በአዲስ አበባ የሚደረግ ሠልፍም ሆነ ስብሰባ የለም-የአዲስ አበባ ፖሊስ

በተሻሻለው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ህግ ረቂቅ ጥፋተኛና አቃቤ ህግ ይደራደራሉ

የ "IStandWithAddis" ሀሽታግን በመጠቀም ተቃውሞውን የገለፀው ሌላኛው የአዲስ አበባ ነዋሪ ዘላለም አባተ ነው። የሰልፉ መከልከል ሕገ መንግሥቱን እንደሚጻረር የሚናገረው ዘላለም፤ ተቃውሞውን ለመግለጽ የማኅበራዊ ሚዲያ ንቅናቄውን መቀላለቀሉን ያስረዳል።

"ከተማዋ ላይ የነዋሪዎች መሰረታዊ መብቶች አይከበሩም" የሚለው ዘላለም ሰልፉ መከልከሉ በነጻነት የመናገር መብትን እንደሚገፍ ይገልጻል። የከተማዋ ነዋሪዎች ጥያቄ ሲኖራቸው ከማድመጥ ይልቅ የማዳፈን አዝማሚያ እንደሚስተዋልም ያክላል።

"በአንጻራዊነት ሌሎች አካባቢዎች ላይ የሚታየው ነጻነት በአዲስ አበባ የለም። ሌሎች ቦታዎች ላይ የተፈቀዱና በሆደ ሰፊነት የሚታዩ ነገሮች አዲስ አበባ ላይ ግን መንግሥት አይታገሳቸውም" ሲል ይናገራል።

አጭር የምስል መግለጫ የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በስፋት የተጋሩት ሀሽታግ

በተለይም ካለፈው ዓመት ወዲህ የከተማዋ ነዋሪዎች ሀሳባቸውን በነጻነት እንዳይገልጹ የተደረጉባቸው አጋጣሚዎች እየተደጋገሙ መምጣታቸው ነዋሪው የመገፋት ስሜት እንዲያድርበት ማድረጉን ይናገራል።

በተለይም ቅዳሜ ጥቅምት 1 ቀን 2012 ዓ. ም ከሰዓት እንዲሁም በነጋታው እሁድ እለትም ሀሽታጉን የትዊተር ተጠቃሚዎች በስፋት ሲጋሩት ነበር።

በተለይም ከባላደራ ምክር ቤት (ባልደራስ) ሕዝባዊ ሰልፍ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ለመቃወም ብዙዎች ሀሽታጉን ተጠቅመዋል። ግለሰቦቹ ከእሥር ከተፈቱ በኋላም ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ይከበር የሚል ጥያቄ በሀሽታጉ ተስተጋብቷል።

ከኢትዮጵያ ውጪ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንም በ "IstandWithAddis" ሀሳባቸውን ገልጸዋል። ከነዚህ አንዷ ደቡብ አፍሪካ በሚገኘው ኩዋዙሉ-ናታል ዩኒቨርስቲ ፒኤችዲዋን እየሠራች ያለችው እየሩሳሌም አማረ ናት።

ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ የኖቤል የሰላም ተሸላሚ መሆናቸው ይፋ በተደረገበት ማግስት አዲስ አበባ ውስጥ ሰላማዊ ሰልፍ ማካሄድ መከልከሉ "አሳፋሪ ነው" ትላለች።

በርካቶች የኢትዮጵያ ስም በዓለም አቀፍ መድረክ በበጎ በመጠራቱ እና ጠቅላይ ሚንስትሩ ተሸላሚ በመሆናቸው ደስታቸውን ገልጸው ሳይጨርሱ፤ ሕዝባዊ ሰልፍ የመከልከሉ ዜና መሰማቱን እየሩሳሌም ትነቅፋለች።

"ምን ተይዞ ምርጫ?" እና "ምንም ይሁን ምን ምርጫው ይካሄድ" ተቃዋሚዎች

"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ

"ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ቅንጦት አይደለም። ተቃውሞ ሸሽቶ፣ ትችት ፈርቶ፣ ጥሩ ጥሩውን ብቻ አውሩ፣ አባብሉኝ አይነት መንግሥት ለጀመርነው እና ለምናራምደው ጥሩ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ ጉዞ አይጠቅምም" ስትል ታስረዳለች።

አንጻራዊ ለውጥ አለ በሚባልበት በዚህ ወቅት ሕዝባዊ ሰልፍን መከልከል ተገቢ እንዳልሆነም ትናገራለች። የኖቤል ሽልማቱን በማስታከክ የተጠራ ሰልፍ እንዲካሄድ ተፈቅዶ፤ በተቃራኒው ከጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ. ም አስቀድሞ የታቀደ ሰላማዊ ሰልፍ መከልከሉ ትክክለኛ ውሳኔ አለመሆኑንም ታክላለች።

የባልደራስ ምክር ቤት ከሰልፉ ቀን ቀደም ብሎ ለሚመለከተው አካል ሰልፍ እንደሚያካሂድ ማሳወቁን በተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን ሲገልጽ ቢቆይም፤ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ፋሲካው ፋንታ ከታቀደው ሰልፍ አንድ ቀን ቀደም ብለው ቅዳሜ ዕለት ለቢቢሲ እንደገለፁት በከተማዋ ውስጥ የሚደረግ ሰልፍ እንደሌለ ተናግረው ነበር።

እስካሁንም ሰልፉ በምን ምክንያት እንዳይደረግ እንደተከለከለ የተገለጸ ነገር የለም። ሰልፉ የተከለከለበትን ምክንያት ለመጠየቅ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በተደጋጋሚ ብንደውልም ምላሽ ማግኘት አልቻልንም።