ምዕራባዊያን ከሁሉ በላይ ልጅ ለመውለድ ቅድሚያ ይሰጣሉ

ምዕራባውያን ለልጅ ቅድሚያ ይሰጣሉ Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ነፍሰ ጡር ሴት

የስዋንሲ ዩኒቨርሲቲ በምዕራቡና በምሥራቁ የዓለማችን ክፍል ውስጥ ያሉ ሰዎች ለትዳርና ለልጅ ያላቸውን ፍላጎት በተመለከተ ጥናት አካሂዷል።

በጥናቱ መሠረት ምዕራባዊያን ከሁሉ በላይ ልጅ ለመውለድ ቅድሚያ የሚሰጡ ናቸው።

ጥናቱ እንደሚያመለክተው በተለይ የእንግሊዝና የአውስትራሊያ ዜጎች ልጅ ለመውለድ ቅድሚያ የሚሰጡ አጋሮችን ይመርጣሉ።

ሴት አስገድዳ ከወንድ ጋር ወሲብ ብትፈጽም፤ አስገድዶ መድፈር ይባላል?

በስዋንሲ ዩኒቨርሲቲ አጥኚ የሆኑት ዶክተር አንድሩ ቶማስ እንደሚሉት ለዚህ ምክንያቱ ባላቸው የተሻለ የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሎት አማራጮች ምክንያት ነው።

የትዳር አጋርን ወይም የፍቅር ጓደኛን ለመምረጥ በሁለቱም ጾታና በሁሉም አገራት መልከ መልካም መሆንና የመልካም ባህሪ ባለቤት መሆን ከፍተኛውን ቦታ ይይዛሉ።

ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች የተውጣጡ ምሁራን ይህንን ጥናት ያከናወኑት 2500 ሰዎችን በመምረጥ ሃሳባዊ ገንዘብ ሰጥተው የትዳር ጓደኛ እንዲሆኗቸው የሚፈልጓቸው ሰዎች ላይ ማግኘት በሚፈልጉት ባህሪይ ላይ ገንዘቡን እንዲያውሉት ተፈቀደላቸው።

ገንዘቡንም ማዋል የሚችሉት የሕይወት አጋር በሚፈልጉበት ጊዜ ቅድሚያ በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ብቻ ነው።

በዚህም መሠረት ምዕራባዊያን ሴቶች 12.6 በመቶ እና ምዕራባዊያን ወንዶች 7.8 በመቶ የሚሆነውን በጀት የትዳር ጓደኛ አግኝተው ልጅ የመውለድ ፍላጎት ባላቸው ተጣማሪዎች ላይ እንዳጠፉት ጥናቱ አመላክቷል።

"ሰውነቴ ወሲብ እንድፈጽም አይፈቅድልኝም'' የብዙ ሴቶች የጤና እክል

ቻይናን፣ ኢንዶኔዥያንና ማሌዥያን በመሳሰሉት የምሥራቅ እስያ አገራት ደግሞ ወንዶች 6.6 በመቶ እና ሴቶች 6.2 በመቶ የሚሆነውን በጀታቸውን ተመሳሳይ ባህሪይ ባላቸው ተጣማጆቻቸው ላይ ማዋላቸውን ጥናቱ አረጋግጫለሁ ብሏል።

ጥናቱን ካጠኑት መካከል አንዱ የሆኑት ዶ/ር ቶማስ ልዩነቱ በምዕራባዊ ባህል ሰዎች የሚፈልጉትን የቤተሰብ እቅድ አማራጮችን ማግኘት መቻላቸው ነው ይላሉ።

በምዕራባዊያን ዘንድ ልጅ መውለድ፣ አለመውለድ ወይም የሚወለዱትን ልጆች ቁጥር መወሰን በተጋቢዎች ይሁንታ የሚወሰን ነው።

"በምዕራባውያን ባህል የእርግዝና መቆጣጠሪያ ማግኘት ችግር አይደለም፤ ውርጃም ይፈቀድልናል" ብለዋል ዶ/ር ቶማስ።

"ነገሮችን ለመተው አማራጮች አሉን። እንደ ምዕራባዊ ሰው ልጅ አልፈልግም ማለት ትችላለህ፤ በምሥራቃዊያን ባህል ግን አንድ ሰው በትዳር ውስጥ የሚገባው ተፈጥሯዊ በሆነ አጋጣሚ ነው" ባይ ናቸው ዶ/ር ቶማስ።

ኢንተርኔትን የሚሾፍረው የወሲብ ፊልም ይሆን?

በሁለቱም ባህሎች ከሁሉ በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው የጋራ መስፈርት መልካምነት ነው። ይህም በምሥራቃዊያን በኩል በሁለቱም ጾታና በምዕራባዊያን ሴቶች የተረጋገጠ ሲሆን ምዕራባዊያን ወንዶች ግን አካላዊ ውበትን ያስቀድማሉ።

በምዕራባዊያን ባህል ዘንድ ጨዋታ አዋቂ መሆንም ቅድሚያ የሚሰጠው መስፈርት ነው፤ ሴቶች 17.3 በመቶ በጀታቸውን የጨረሱበት ሲሆን ወንዶች ደግሞ 18.4 በመቶ የሚሆነውን በጀታቸውን ጨዋታ አዋቂ ሴት በመሻት አጥፍተውታል ይላል ጥናቱ።

ምሥራቃዊያን ደግሞ በአንጻሩ ጨዋታ አዋቂነት ብዙም ግድ አይሰጣቸውም። ከተሰጣቸው በጀት መካከል ሴቶቹ 11.1 በመቶ የሚሆነውንና ወንዶቹ 11 በመቶ የሚሆነውን በጀታቸውን ብቻ ተጫዋች የፍቅር ጓደኛ በመፈለግ አውጥተዋል ይላል የስዋንሲ ዩኒቨርሲቲው ጥናት።

ጥናቱ አክሎም ለምሥራቃዊያን ሃይማኖታዊ መሆንና ለአጋር ታማኝ መሆን ለትዳር ፈላጊዎች ቅድሚያ የሚሰጡ መስፈርቶች ሲሆኑ በምዕራባዊያን በኩል ግን እነዚህ ጉዳዮች ብዙም የሚያሳስቡ አይደሉም።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ