የኢትዮጵያዊያንን ትዳር አከርካሪ እየሰበረ ያለው ምን ይሆን?

የጋብቻ ቀለበት Image copyright ullstein bild

ወ/ሮ አበባ ገብረ ሥላሴ ከባለቤታቸው ከአቶ ገብረ ክርስቶስ ጋር በትዳር 50 ዓመታትን ማሳለፋቸውን ይናገራሉ። በቅርቡም ከዘጠኝ ልጆቻቸውና ከ17 የልጅ ልጆቻቸው ጋር በመሆን የ50ኛ ዓመት የጋብቻ በዓላቸውን አክብረዋል።

ከትዳር አጋራቸው ጋር ይህን ያህል ዓመት ሊኖሩ የቻሉት "መቻቻል በመካከላችን ስለነበር" ነው ይላሉ።

የትዳር አጋራቸው "ጥፋት ሳያጠፋ ቀርቶ አይደለም" የሚሉት ወ/ሮ አበባ፤ ነገር ግን ተረጋግተው ሰከን በማለት ነገሮችን ለመፍታት መሞከራቸው ደስተኛ የትዳር ህይወት ለማጣጣም እንደረዳቸው ይናገራሉ።

እንደ ባልና ሚስት ቁጭ ብሎ ለመነጋገር የከበዳቸው ጥንዶች፣ ልጅ ስለወለዱ ብቻ አብረው የሚኖሩ ባልና ሚስት፣ እርስ በርስ ጣት በመቀሳሰር የሚወነጃጀሉ አጋሮች ማየት ግን የተለመደ ነው።

ይህ አለመግባባት አድጎ ሰማኒያቸውን የቀደዱ፣ የመሰረቱትን ቤተሰብ የበተኑም ቀላል አይደሉም። ለመሆኑ የኢትዮጵያዊያንን የትዳር አከርካሪ ምን ይሆን እየሰበረ ያለው ስንል ከ10 ዓመት በላይ በጋብቻና ቤተሰብ ማማከር ላይ የቆዩትን ትዕግስት ዋልተንጉስና እንዳልክ አሠፋን ጠይቀን።

ትዕግስትና እንዳልክ ባለፉት 10 ዓመታት በትዳር ምክክር ላይ የሰሩ ሲሆን የእርቅ ማዕድ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መስርተው የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ ናቸው።

ከሰዎች ጋር ያለንን ግንኙነት ለማስተካከል የሚረዱ ዘጠኝ ሚስጥሮች

ከስም ፊት የሚቀመጡ መለያዎና አንድምታቸው

ቻይና ቅጥ ያጡ ሰርጎችን ልትቆጣጠር ነው

የትዳርና የፍቅር ግንኙነትን ፈተና ላይ ከሚጥሉ ነገሮች መካከል ይላል እንዳልክ፣ ጥንዶች ስለ ትዳርና የፍቅር ግንኙነት ያላቸው እውቀት ማነስ አንዱ ነው።

ትዕግስት በበኩሏ "ትዳር እኮ የሚጀምረው ከራስ ነው" በማለት የትዳር አጋርን ከመመልከት በፊት ራስን መመልከት እንደሚገባ ትገልፃለች።

ሰዎች ስለትዳርና ስለፍቅር ያላቸው እውቀት የተዛባ መሆን፣ የኢኮኖሚ አቅም መዳከም፣ የባሕል ልዩነት፣ አስተሳሰብ፣ የትምህርት ደረጃ፣ የትዳርና የፍቅር ግንኙነትን አጣብቂኝ ውስጥ ከሚጥሉ መካከል ይጠቀሳል ያለው እንዳልክ በይበልጥ ግን በሁለቱ የትዳር አጋሮች መካከል ያለ የተግባቦት ክህሎት ማነስ የችግሮች ሁሉ መንስኤ ሆኖ እንዳገኘው ይጠቅሳል።

ወ/ሮ አበባ በበኩላቸው አማቴንም ሆነ ምራቴን እንደቤተሰቤ መቀበሌ እና ደስተኛ መሆኔ ትዳሬ እንዲሰምር ረድቶኛል ይላሉ። "እኔና ባለቤቴ ተጣልተን እናውቃለን፤ ግን መቻቻል እስከዛሬ አኑሮናል" በማለት ከፍቺ ይልቅ ፍቅርን አስቀድመው እዚህ መድረሳቸውን ይመሰክራሉ።

ከትዳር በፊት ራስን ማየት

ትዕግስት ባለፉት ዓመታት የትዳር አጋሮችንና ቤተሰቦችን በምክክር ስታገለግል ያስተዋለችው ዋናው ነገር ትዳርን በመሪነት የሚሾፍረው ሁለቱ ጥንዶች ለራሳቸው ያላቸው ግምት መሆኑን ነው።

ይህንኑ ሃሳቧን ስታፍታታም ትዳር እንደተጀመረ ወንዱም ሆነ ሴቷ 'መልአካዊ' ባህሪ ያሳያሉ በማለት ነው።

ችግሮች መከሰት የሚጀምሩት እያደር ነው። "ቀን ቀንን ወልዶ በትዳር የዕለት ተዕለት አዙሪት ውስጥ የፍቅር ማዕበሉ ፀጥ ሲል የጥንዶቹን የግል ማንነት የሚመራው ለራሳቸው ያላቸው አመለካከት መገለጥ ይጀምራል" ስትልም ሃሳቧን ታብራራለች።

የሕፃናት ጋብቻ ቀንሷል- ዩኒሴፍ

"ልጆች እያሳደጉ ትምህርት ከባድ ቢሆንም፤ ፍላጎቱ ካለ ሁሉንም ይቻላል"

አክላም ትዳር የሚመሰርቱ ጥንዶች በቅድሚያ ኪሳቸውን ወይንም የባንክ አካውንታቸውን እንደሚያዩት ሁሉ፤ ለራሳቸው ያላቸውን እምነትና አመለካከትም ማየት እንደሚያስፈልጋቸው ትጠቅሳለች - ትዕግስት።

ሁለት ተቃራኒ ጾታዎች ትዳር ከመመስረታቸው በፊት በቅድሚያ ከራሳቸው ጋር ያላቸው ግንኙነት ምን ይመስላል የሚለውን መፈተሽ፣ የጎደለንን ነገር መመልከት፣ የሚፈሩትን ነገር ሳይደብቁ ይፋ አውጥተው መነጋገር ወሳኝ መሆኑንም ትመክራለች።

እንዳልክና ትዕግስት በትዳርና በፍቅር ግንኙነት ውስጥ በተደጋጋሚ የሚስተዋሉ ነገሮች አማካሪ አለመኖር እንደችግር ያነሳሉ። ወ/ሮ አበባም ሁሌም ምነው አማካሪ በኖረ ብለው እንደሚያስቡ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ በነበራቸው ወቅት ተናግረዋል።

ጥንዶቹ ወደ ጋብቻ ከመሄዳቸው በፊት ሊመሰርቱ ስለሚያስቡት ቤተሰብ፣ ቤተሰቡ ስለሚኖረው ግብ፣ ዕሴትና ሌሎች ነገሮች ቁጭ ብሎ የሚያማክር ወገን አለመኖር ወደ ትዳር ዘለው የሚገቡ ጥንዶች የሚገጥማቸውን ተግዳሮት በራሳቸው ብቻ እንዲወጡ ያደርጋቸዋል ይላሉ ባለሙያዎቹ።

እንዳልክ ይህንን ሀሳብ ለማጠናከርም "ትዳር በእውቀት ነው የሚመራው" በማለት ትዳር ምንድን ነው? እንዴት ይመራል? የሚሉና የወንድና የሴት ተፈጥሮን ማዕከል ያደረጉ መሠረታዊ እውቀቶች እንደሚያስፈልጉ ይናገራል።

Image copyright Tigist WalteNigus and Endalk Facebook pages

እውቀቱ ከየት ይገኛል?

ትዳርን በሁለት እግሩ አቁሞ ጠንካራ የቤተሰብ መሰረት ለማድረግ ተቋማት ያስፈልጋሉ ይላሉ ሁለቱም ባለሙያዎቹ።

ወ/ሮ አበባም የቀደሙ ሰዎች ትዳራቸወን እንዴት እንደመሩ በመጠየቅ ትምህርት ለማግኘት ይጥሩ እንደነበር ነግረውናል።

የማህበራዊ ተቋማት፣ ባህላዊ መስተጋብር ያለውን እውቀት መጠቀም፣ የመንፈሳዊ እናቶችና አባቶችን እንዲሁም ተቋማቱን መጠቀም፣ በተጨማሪም በሙያው የሰለጠኑ የጋብቻ የምክክር አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎችን መጎብኘት ስለ ትዳርና ግንኙነት እውቀት የምናገኝባቸው ስፍራዎች መሆናቸውን እንዳልክ ይናገራል።

ጎጆ መቀለስ ወይንም ሦስት ጉልቻ መመስረት ወልዶ ከመሳም፣ አንድ ጣሪያ ሥር ከመኖር የዘለለ መሆኑን የሚያማክር ወገን መኖር እንዳለበት ትዕግስትም ትናገራለች።

ቤተሰብና ጓደኛ የሚያከራየው ድርጅት

ሴቶች 'ፌሚኒስት' መባልን ለምን ይጠላሉ?

ሰዎች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት ስለ ተፈጥሯዊ ባህሪያቸው ማወቅ ተገቢ ነው የሚለው እንዳልክ፤ የሴት ተፈጥሯዊ ባህሪ ምንድን ነው? የወንዱስ? ባልነት የሚጠይቀው ኃላፊነት ምንድን ነው? እናትነትና አባትነት ውስጥ ያሉ ኃላፊነቶች ምንድን ናቸው? የሚለውን ማወቅ ጥንዶቹ በጋብቻቸው ውስጥ በመረዳዳትና በአግባቡ ለመተዋወቅ እንደሚረዳቸው ይናገራል።

የወንድ ልጅ ደመነፍሳዊ ባህሪ መጠበቅ፣ መከላከል፣ መሆኑን ማወቅ፤ ሴቷ ደግሞ ነገሮችን ዘርዝሮ የመረዳት፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ተፈጥሯዊ ክህሎቶችና እውቀቶች እንዳሏት መረዳት ትዳርን በእውቀት ለመምራት የሚረዱ መግቢያዎች ናቸው ይላል።

ወንድ ችግሮች ሲገጥሙት ወደ ራሱ ተፈጥሯዊ ዋሻ ገብቶ መፍትሄ እንደሚፈልግ መረዳት፣ ሴቶች ችግር ሲገጥማቸው ደግሞ ተነጋግሮ የሚፈቱበት መንገድን ተፈጥሮ እንዳደለቻቸው ማስተዋል፤ ችግር በሚገጥምበት ወቅት መፍታት የሚችሉባቸውን መንገዶች እንዲያውቁ ይረዳቸዋል ይላል እንዳልክ።

ሁለቱም ጾታዎች አንዳቸው የሌላኛቸውን ተፈጥሯዊ ባህሪ መረዳት ሲችሉ፤ ችግር በገጠማቸው ወቅት እንዴት እንደሚፈቱትና እንዴት በጋራ እንደሚወጡት ይረዳዳሉ። ካልሆነ ግን ላለመግባባት፣ ኩርፊያና ቅያሜ ያጋልጣል ይላል።

እነዚህን እውቀቶች ከንባብ፣ ከባለሙያ አልያም ከበይነ መረብ ማግኘት እንደሚቻልም ይጠቅሳል።

ትዕግስት በበኩሏ ከመጻህፍትም ሆነ ከበይነ መረብ የምናገኘውን እውቀት ለመውሰድ በቅድሚያ በራሳችን ያለብንን ክፍተት መረዳትና ያንንም ለማስተካከል ዝግጁነት ሊኖረን እንደሚገባ ትናገራለች።

ጎጆ ከመቀለስ፣ ከሦስት ጉልቻ በፊት ራስን መሥራት ቢቀድም መልካም መሆኑን ትናገራለች። አንድን ትዳር የሚመራው የሁለቱ ሰዎች መዋደድ፣ ሁለቱ ሰዎች ያላቸው ገንዘብ እና ፍቅር ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው ያላቸው ግምት ጭምር ነው ስትልም ሃሳቧን ታጠናክራለች።

ስት ጉልቻ ፈተናዎች

ትዕግስትና እንዳልክ በአስር ዓመት የማማከር ልምዳቸው ኢትዮጵያዊን ጥንዶችን ወገቤን እንዲሉ ያደረጓቸውን ጉዳዮች ታዝበዋል።

ችግር ውስጥ የገቡ ባለትዳርና ቤተሰቦች ውስጥ የሚታዩት መሠረታዊ ችግሮች አለመተማመን፣ አለመስማማት፣ የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት፣ ለራስ ያለ ግምት መውረድ፣ ወሲብና መግባባት አለመቻል መሆናቸውን የምትዘረዝረው ትዕግስት ናት።

ነገር ግን የዚህ ሁሉ ችግር ምንጭ ከሥሩ ይመንገል ተብሎ ሲቆፈር ጥንዶቹ ለራሳቸው የሚሠጡት ስፍራ ገኖ እንደሚታይ ትጠቅሳለች።

ያለመግባባት ምክንያት ሆነው በጥንዶች መካከል የሚነሱት ነገሮች በአጠቃላይ ከላይ የሚታዩ የበሽታው ምልክቶች እንጂ ራሱ በሽታው አይደለም ስትል ታጠናክራለች።

በትዳር ውስጥ አንዳንዱ ለራሱ ያለው ግምት 'እኔ ብቁ ነኝ' በሚል ማንነት የተለበጠ ሲሆን ሌላው ደግሞ 'ብቁ አይደለሁም' በሚል የራስ መተማመን ማጣት የተናጋ ነው የምትለው ትዕግስት "'ብቁ አይደለሁም፣ ተወዳጅ አይደለሁም' የሚል አጋር፤ ሌላኛው አጋሩን አይሰማም" በማለት ያለመግባባቱን ስር ማየት እንደሚያስፈልግት ትመክራለች።

በሥራዋ አጋጣሚ እኔ ያልኩት ይሁን ብቻ የሚሉ ጥንዶች ገጥመዋት ማየቷን በማስታወስ 'ተቀባይነት የለኝም፣ ተወዳጅ አይደለሁም' የሚለው ሀሳብ በተለይ ከትዳር አጋር የሚመጣን ሃሳብ ውድቅ ማድረግ ከሆነ ደግሞ እንደ ጥቃት የመቁጠር ዝንባሌ አዳብረው ማስተዋሏን ትናገራለች።

ስለዚህ ጥንዶች ስለራሳቸው የሚሰማቸው ነገር ምን እንደሆነ ማጤንና መፈተሽ ቀዳሚው ነገር ቢሆን የሚል ሀሳብ ታነሳለች።

ቤይሩት፡ ባለፉት 7 ወራት 34 ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል

የመደፈሬን ታሪክ ከስልሳ ሰባት ዓመታት በኋላ የተናገርኩበት ምክንያት

ለራሳቸው ዝቅተኛ ግምት የሚሠጡ ሰዎች በትዳራቸው ላይ ቁጡ፣ ጯሂ፣ ለማንኛውም ነገር ቀድመው መልስ የሚሠጡ፣ ሁሉን ነገር አውቃለሁ የሚሉ ስለሚሆኑ ለትዳር አጋራቸው ፈታኝ ይሆናሉ ስትልም ሃሳቧን ታጠናክራለች።

Image copyright Getty Images

"የትዳር ስንክሳሮች ብዙ ቢሆኑም" የሚለው እንዳልክ "ችግሮች ሁሌም መፍትሔ እንዳላቸው መረዳት ለጥንዶቹ ቀዳሚ ነጥብ መሆን አለበት" ይላል።

ሌላው እንዳልክ የሚያነሳው ነጥብ ከመፋታት ይልቅ ችግርን መፍታት አስፈላጊ በመሆኑ ተረጋግቶ፣ የጥሞና ጊዜ ወስዶ ለችግሮቻቸው መፍትሄ መስጠትን ይመክራል።

ችግሮቻቸውን ራሳቸው መፍታት ካልቻሉም ለሌላ ወገን እድል ሊሰጡ ይገባል የሚለው እንዳልክ የጋብቻ ምክክር ባለሙያዎች፣ የኃይማኖት አባቶች፣ በእድሜ በሰል ያሉ ሰዎች ለዚህ መፍትሄ ናቸው ይላል።

ትዳር ከተመሰረተ በኋላ በዕለት ተዕለት ሕይወት ውስጥ ግጭት ተከስቶ፣ የነበረው እንዳልነበር ሲሆን፣ አፍ ቁልምጫን ረስቶ ዘለፋ ሲቀድም፣ የሚያሳየን "የትዳር የፍቅር ባንክ ውስጥ ያለው ሂሳብ ማለቁን ነው" ይላል እንዳልክ።

ከዚህ አንጻር ሁለቱም ባለሙያዎች በአንድ ድምፅ የሚስማሙት በትዳር ውስጥ የሚኖር ፍቅር በክፉ ጊዜ እንደሚቀመጥ ገንዘብ ነው በማለት ነው። ማንኛውም ባለትዳር በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ የትኞቹንም ግጭቶች ችሎ የሚኖረው፣ ጥንዶቹ በደህና ጊዜ ያጠራቀሙት ፍቅር በመኖሩ መሆኑን ይጠቅሳሉ።

የአምስት ቤተሰብ አባላትን ሕይወት የቀጠፈው የመሬት ናዳ

"የፍቅር ካዝናችሁ ባዶ ከሆነ መልሶ በስሜት በመተካከም፣ ፍቅርን በመገላለጥና አንዳችሁ ለአንዳቸሁ ያላችሁን ስሜት በመገላለጥ የተራቆተውን ትዳር ዳግም ማሞቅ" እንደሚያስፈልግ ትዕግስት ትናገራለች።

ትዳር ውስጥ ግጭት ተከስቶ ሽምግልና የሚቀመጡ ሰዎች በቅድሚያ የሚሰሙት ግጭቱ የጀመረው ትናንት አለመሆኑን እንደሆነ የምትናገረው ትዕግስት፤ ከዓመታት በፊት የጀመረ የጠብ እርሾ ተብላልቶ ወደ አደባባይ እስኪወጣ ያኖራቸው የተጠራቀመው "የፍቅር የቁጠባ ሂሳብ" እንደሆነ ትገልፃለች።

ባለቤቷ ወይንም ባለቤቱ በፍቅር ወቅት የቆጠቡት "የፍቅር ሂሳብ" ካለቀ እንደ አዲስ የሚያዋጡት "የፍቅር ሂሳብ" መኖር አለበት ሲል እንዳልክ ይመክራል።

በትዳር ውስጥ አንድ ባልና ሚስት በአካል ቢራቆቱ እንደማይተፋፈሩ ሁሉ፤ በስሜትም ራቁት መሆን እንደሚያስፈልጋቸው የምትናገረዋ ትዕግስት ደግሞ በመካከላቸው ሚስጥር መኖሩና መደባበቅ መፈጠሩ ለግጭት እርሾ ትቶ እንደሚያልፍ ታስረዳለች።

ነገር ግን ይህ ግልፅ መሆን በአንድ ጊዜ የሚመጣ ሳይሆን በሂደት መሆኑንም ታሰምርበታለች።

ባልና ሚስት ከተጋቡ በኋላ የሚኖራቸው ቅርበት የበለጠ እየጠነከረ የሚሄደው፤ ባልም እናት አባቱን ትቶ ሚስትም ቤተሰቦቿን ርግፍ አድርጋ ከትዳር አጋሯ ጋር የምትጣበቀው በሂደት መሆኑንም ታሰምርበታለች።

ጥንዶች ለቤተሰቦቻቸው ያላቸው ስሜትና ቅርበት የግጭትና የፍቺ ምክንያት ሆኖ እንደሚታይ በማስታወስም፤ ከትዳር ተጣማጅ ጋር የሚኖር ቅርበት ሂደት መሆኑን ማስታወስ ለሁለቱም ጠቃሚ መሆኑን ትናገራለች።

ሚስጥርንም ሆነ ሌሎች ጉዳዮችን ግልፅልፅ አድርጎ ለመናገርና "በስሜት ራቁት ለመሄድ" ጊዜ እንደሚያስፈልግ ትዕግስት ትናገራለች።

ስለትዳር መቼ ነው ምክር የምንጠይቀው?

የትዳር የመጀመሪያ ወራቶች ሁሉም ነገር ጥዑም መዓዛ ያለው፣ መስኩ አበባ፣ እዳው ገለባ የሆነበት ጊዜ መሆኑን በማስታወስ፣ አዲስ ተጋቢዎችን በቅድሚያ ራሳችሁን ፈልጋችሁ አግኙ ብሎ መመካከር 'አይደለም ራሴን የትዳር አጋሬን ፈልጌ አግኝቻለሁ' ወደ ሚል ምላሽ ሊያመራ ይችላል የምትለው ትዕግስት ናት።

ቅድመ ጋብቻ ትምህርት የሚሰጠው ሁሉን ነገር ጨርሶ ለመጣ ሰው ሲሆን እንደሚያስቸግር በመጥቀስ ታዳጊዎች ስለራስ ማወቅ በእድሜያቸው ለጋነት ቢማሩ ጤናማ ትዳር ለመመስረትና ጤናማ ቤተሰብ ለመምራት ይረዳቸዋል ይላሉ ባለሙያዎቹ።

"ከቅድመ ጋብቻ ትምህርት በፊት ቀድመው የሚሰሩ ነገሮች ቢኖሩ መልካም ነው" በማለትም አፍላ ወጣትነት ላይ እያሉ ስለ ራስን ፈልጎ ማግኘት፣ እሴትን ማስቀመጥ፣ ስለ ፍቅር ግንኙነትና የትዳር አጋር የሚያማክራቸው ቢኖር መልካም ነበር ትላለች።

ዕድሜያችን የማቱሳላን ሲሶ እንኳ መሄድ የተሳነው ለምን ይሆን?

እንዳልክ በበኩሉ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችም ውስጥ ሆነ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርቱ ቢኖር ጤናማ ቤተሰብ ለመመስረት እንደሚረዳ ይናገራል።

ከመጋባታቸው በፊት ልጅ ወልደው ቤት ውስጥ ሆነው ለማሳደግ የተስማሙ ሚስቶች፣ ወይንም ልጆቹን እናታቸው ሥራ ፈትታ እንድታሳድግ በሚፈልግ ባል መካከል አለመግባባት የሚነሳው በቅድሚያ የሕይወት እሴታቸውን ሲበይኑ በግልፅ ባለማስቀመጣቸው መሆኑን ትዕግስት ታብራራለች።

'ትምህርት መማር እፈልጋለሁ'፣ 'ከልጅ ጋር ቤት ውስጥ ታስሮ መዋል ጨነቀኝ'፣ 'መማር የልጅነት ህልሜ ነበር' የሚሉ ነገሮች የሚመጡት በቅድሚያ በግልፅ የተበየነ የሕይወት ዕሴት ባለመኖሩ መሆኑን ትገልፃለች።

ይህ ንግግር የተጀመረው ትዳር ከተጀመረ በኋላ ከሆነ ደግሞ የትዳር አጋሩ ከጊዜ በኋላ የመጣ ባህሪ እንደሆነ እንዲሰማውና ለጠብ መንስኤ እንዲሆን እንደሚያደርግ ታስረዳለች።

የፍቅር ጓደኛ አልያም የትዳር አጋር ከመምረጣችን በፊት ስለግንኙነቱ በደንብ ራሳችንን በዕውቀት ማነፅ እንደሚያስፈልግ የምትመክረው ትዕግስት፤ አንድ ጊዜ ምርጫ ካደረጉ በኋላ ስለራስ አመለካከት፣ ለራስ ስለሚኖር ክብር፣ ከራስ ጋር ስለሚኖር ግንኙነት፣ ፍላጎትን ስለ መለየት፣ ዕሴትን ስለማስቀመጥ ማወቅና ተገቢውን እርምጃ መውሰድ አስፈላጊ መሆኑን ትናገራለች።

የትዳር አጋሮች ሲጋቡ መደራደር የማይችሉት፣ የማይቀይሩት፣ ካላቸው ዕሴት ውጪ ቢኖሩ ደስተኛ የማይሆኑባቸው ጉዳዮች ይኖራሉ የምትለው ትዕግስት፤ ይህንን አስቀድመው ለይተው ያላወቁ ተጋቢዎች ትዳር ውስጥ ገብተው የማያስደስታቸውን ነገር እያደረጉ መኖር ሲጀምሩ ከሌላኛው ወገን ጥያቄ መነሳት እንደሚጀመር ትጠቅሳለች።

Image copyright Getty Images

"ዕሴትን ከትዳር አጋር ጋር መነጋገርና ማስረዳት አለመቻል ራስን አለማወቅ ነው" በማለትም ራሳችንን በሚገባ ፈልገን ሳናውቅ ሌላ ሰው ሕይወታችን ውስጥ በማምጣት ትዳር ከመሰረትን በኋላ፣ የአጋራችንን ፍላጎት ለመረዳት፣ ህልሙንና እሴቱን ለመኖር ጥረት ስናደርግ ጠብ ይከሰታል ትላለች።

የትዳር አጋሮች የጋራ ራዕይ

ጥንዶች 'ዓለምሽ ዛሬ ነው' ተብሎ ተዘፍኖ፣ ትከሻ እስኪነቀል ተጨፍሮ ከተዳሩ በኋላ ልጅ ሲመጣ፣ ቤት ሲሰሩ ከዚያም ሌሎች በህይወታቸው ውስጥ የሚያስፈልጋቸውን ነገሮች ሲያሟሉ "እርስ በእርስ ፍቅር መገላለጡን ይረሱታል የምትለው" ትዕግስት ለዚህ መፍትሔው የጋራ ራዕይ ማኖር ነው ትላለች።

አንድ ሰው በግሉ ዓላማ እንዳለው ሁሉ ትዳር ውስጥ ደግሞ ሲገባ የጋራ ሕልም፣ ግብና ራዕይ ማኖር አስፈላጊ መሆኑን ታሰምርበታለች።

የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል?

ፍቅር እና ግንኙነት ከቲንደር አብዮት በኋላ

"የጋራ ህልማቸው ቤት መሥራት ከሆነ ቤት ብቻ ይሰራሉ። ስሜታቸው ላይ ግን አይሰሩም። የጋራ ግቡ መኪና መግዛት ከሆነ መኪና ይገዛሉ ቤተሰባቸው ላይ ግን አይሰሩም" ትላለች ትዕግስት።

አክላም የመሰረቱት ቤተሰብ ከአምስት ዓመት በኋላ በስሜት፣ በኢኮኖሚና ከሚኖሩበት ማህበረሰብ ጋር እንዴት አድርገው አጣጥመው እንደሚሄዱ እንዲሁም ከቤተሰቦቻቸው ጋር የሚኖር ግንኙነት ምን መምሰል እንዳለበት ካላቀዱ ለቤተሰቡ ኪሳራ መሆኑን ታስረዳለች።

ይህንን የጋራ እቅድ ሲያወጡ ልጆቻቸውን እንዴት ማሳደግ እንደሚችሉ፣ እርስ በእርስ እንዴት እንደሚተናነፁ ካላወሩ የቁስ ግንባታ ብቻ ትዳርን በሁለት እግሩ እንደማያቆመው ትናገራለች።

በትዳር ያሉ ጥንዶች ልጅ ወልደው ስመው፣ ቤት ሰርተው፣ መኪና ገዝተው፣ በቂ ገንዘብ ኖሯቸው በትዳራቸው ደስተኛ ሳይሆኑ አስተውላ እንደምታውቅ የምትናገረው ትዕግስት፤ ያኔ የጥንዶቹ የፍቅር የሂሳብ መዝገብ መጉደሉን አልያም ማለቁን እንደሚነግራት ትጠቅሳለች።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ