የዓመቱ የቢቢሲ የዓለማችን ተጽዕኖ ፈጣሪ 100 ሴቶች

ከቢቢሲ የዓመቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ ሴቶች መካከል የተወሰኑት ምስል

ቢቢሲ በአውሮፓዊያኑ 2019 በዓለም ዙሪያ ለሌሎች መልካም ተነሳሽነት የፈጠሩና ተጽእኖ ፈጣሪ ያላቸውን የ100 ሴቶችን ስም ይፋ አድርጓል።

የዚህ ዓመት ሴት ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ለመለየት በተደረገው ምዘና፤ ዋነኛው ጥያቄ ሆኖ የቀረበው፤ ሴቶች ከፊት ሆነው መምራት ቢችሉ መጪው ዘመን ምን ሊመስል ይችላል? የሚል ነው።

በዚህ የዓመቱ የቢቢሲ የዓለማችን ሴት ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ዝርዝር ውስጥ በጦርነት የፈራረሰችውን ሶሪያን መልሶ ለመገንባት እያቀደች ካለች የሥነ ህንጻ ባለሙያ አንስቶ በናሳ ውስጥ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊ እስከሆነች ባለሙያ ድረስ ተካተዋል።

"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው"

"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

በዝርዝሩ ውስጥ ያሉት አብዛኞቹ በያሉበት የሙያ መስክ ከከፍተኛው ደረጃ ላይ ያሉ ሲሆኑ ከአስር ዓመታት በኋላ ህይወት በምድራችን ላይ ምን ልትመስል እንደምትችል ከሙያቸው አንጻር ትንበያ ሰጥተዋል።

ሌሎቹ ደግሞ የማፍያ ቡድንን እየተጋፈጠች ያለች ፖለቲከኛና በሴቶች ላይ ያለውን የተዛባ አመለካከት እየታገለች ያለች እግር ኳስ ተጫዋች የተለየ የህይወት ልምዳቸውን ተጠቅመው ለሚከተሏቸው መንገድ የሚመሩ ሴቶች ናቸው።

የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው?

ከዓለም ዙሪያ ከተለያዩ የሙያ ዘርፎች ተጽዕኖ ፈጣሪ ናቸው ተብሎ በቢቢሲ የተመረጡት ሴቶች የሚከተሉት ናቸው።.

1) ፕሪሺየስ አዳምስ፣ አሜሪካዊት፣ የባሌ ዳንሰኛ

2) ፓርቪና አሃንገር፣ በህንድ ከምትተዳደረው ካሽሚር፣ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ

3) ፒየራ አዬሎ፣ ጣሊያናዊት፣ ፖለቲከኛ

4) ጃስሚን አክተር፣ ዩኬ/ባንግላዲሽ፣ የክሪኬት ተጫዋች

5) ማናል አልዶዋያ፣ ሳዑዲ አረቢያዊት፣ አርቲስት

6) ኪሚያ አሊዛዴህ፣ ኢራናዊት፣ የቴክዋንዶ ስፖርተኛ

7) ማርዋ አል ሳቡኒ፣ ሶሪያዊት፣ የሥነ ህንጻ ባለሙያ

8) አላኑድ አልሻሬኪህ፣ ኩዌታዊት፣ የሴቶች መብት ተሟጋች

9) ሪዳ አል ቱቡሊ፣ ሊቢያዊት፣ የሠላም ተሟጋች

10) ታባታ አማራል፣ ብራዚላዊት፣ ፖለቲከኛ

11) ያሊትዛ አፓሪሲዮ፣ ሜክሲኳዊት፣ ተዋናይትና የሰብአዊ መብት ተሟጋች

12) ዳያና አሽ፣ ሌባኖሳዊት፣ የባህላዊ መብቶች ተሟጋች

13) ዲና አሸር ስሚዝ፣ እንግሊዛዊት፣ አትሌት

14) ሚሚ አውንግ፣ አሜሪካዊት፣ የናሳ ፕሮጀክት ኃላፊ

15) ኒሻ አዩብ፣ ማሌዢያዊት፣ ጾታቸውን የቀየሩ ሰዎች ተሟጋች

16) ጁዲት ባክሪያ፣ ኡጋንዳዊት፣ አርሶ አደር

17) አያህ ብዲር፣ ሌባኖሳዊት፣ ሥራ ፈጣሪ

18) ዳማናንዳ ቢኹኒ፣ ታይላንዳዊት፣ መነኩሴ

19) ማቤል ቢያንኮ፣ አርጀንቲናዊት፣ የህክምና ዶክተር

20) ራያ ቢድሻሂር፣ ኢራናዊት፣ የትምህርት ባለሙያ

21) ካቲ ቦማን፣ አሜሪካዊት፣ ሳይንቲስት

22) ሲናድ በርክ፣ አየርላንዳዊት፣ የአካል ጉዳተኞች መብት ተከራካሪ

23) ሊሳ ካምፖ-ኢነግለስቲን፣ አሜሪካዊት፣ የሥነ ህይወትና ሥነ ምግባር ባለሙያ

24) ስካርሌት ከርትስ፣ እንግሊዛዊት፣ ጸሐፊ

25) ኤላ ዳይሽ፣ እንግሊዛዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ተመራማሪ

26) ሻራን ዳሊዋል፣ እንግሊዛዊት፣ ጸሐፊና አርቲስት

27) ሳልዋ ኢድ ናስር፣ ናይጄሪያ/ባህሬን፣ አትሌት

28) ራና ኤል ካሉቢ፣ ግብጻዊት፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀነስ ባለሙያ

29) ማሪያ ፈርናንዳ ኤስፒኖሳ፣ ኤኳዶራዊት፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ፕሬዝዳንት

30) ሉሲንዳ ኢቫንስ፣ ደቡብ አፍሪካዊት፣ የሴቶች መብት ተሟጋች

31) እህት ጄራርድ ፈርናንዴዝ፣ ሴንጋፖራዊት፣ የሮማ ካቶሊክ መነኩሴ

32) ቤታኒ ፊርዝ፣ እንግሊዛዊት፣ አካል ጉዳተኛ የዋና ስፖርተኛ

33) ኦውል ፊሸር፣ አይስላንድ፣ ጋዜጠኛና የጾታዊ መብቶች ተሟጋች

34) አሽሊ-አን ፍራዘር-ፕራይስ፣ ጃማይካዊት፣ አትሌት

35) ዛሪፋ ጋፋሪ፣ አፍጋኒስታናዊት፣ ከንቲባ

36) ጃሊላ ሃይደር፣ ፓኪስታናዊት፣ ጠበቃ

37) ታይላ ሃሪስ፣ አውስትራሊያዊት፣ እግር ኳስ ተጫዋችና ቦክሰኛ

38) ሆሊ፣ አሜሪካዊት፣ ከወሲባዊ ጥቃት ያመለጠች

39) ሁጋን ዌንሲ፣ ቻይናዊት፣ ቦክሰኛ

40) ሉቺታ ሁርታዶ፣ ቬኔዙዌላዊት፣ አርቲስት

41) ዩሚ ኢሺካዋ፣ ጃፓናዊት፣ የመብት ተሟጋች

42) አስማ ጄምስ፣ ሴራ ሊዮናዊት፣ ጋዜጠኛና የመብት ተሟጋች

43) አራንያ ጆሃር፣ ህንዳዊት፣ ገጣሚ

44) ካትሪና ጆንስተን፣ አሜሪካዊት፣ አንትሮፖሎጂስት

45) ጋዳ ካዶዳ፣ ሱዳናዊት፣ መሀንዲስ

46) ኤሚ ካርል፣ አሜሪካዊት፣ የሥነ ህይወት አርቲስት

47) አህላም ኹድር፣ ሱዳናዊት፣ የተቃውሞ መሪ

48) ፊዮና ኮልቢንገር፣ ጀርመናዊት፣ ብስክሌተኛ

49) ሂዮሪ ኮን፣ ጃፓናዊት፣ የጃፓን ነጻ ትግል ስፖርተኛ

50) አይሳታ ላም፣ ሞሪታኒያዊት፣ የጥቃቅን የገንዘብ ተቋማት ባለሙያ

51) ሱ የንግሊ፣ ደቡብ ኮሪያዊት፣ ሳይኮሎጂስት

52) ፊ ፊ ሊ፣ አሜሪካዊት፣ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ባለሙያ

53) ኤሪካ ለስት፣ ስዊዲናዊት፣ የፊልም ባለሙያ

54) ሎሪን ማሆ፣ እንግሊዛዊት፣ ከካንሰር የዳነች

55) ጁሊ ማካኒ፣ ታንዛኒያዊት፣ ተመራማሪና ዶክተር

56) ሊሳ ማንዲማከር፣ ኔዘርላንዳዊት፣ ዲዛይነር

57) ጄሚ ማርጎሊን፣ አሜሪካዊት፣ የአየር ጸባይ ለውጥ ተሟጋች

58) ፍራንሲያ ማርኬዝ፣ ኮሎምቢያዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያ

59) ጊና ማርቲን፣ እንግሊዛዊት፣ የመብት ተሟጋች

60) ሳራ ማርቲንስ ዳ ሲልቫ፣ እንግሊዛዊት፣ የማህጸንና ጽንስ አማካሪ

61) ራጂ ሜዚያን፣ አልጄሪያዊት፣ ድምጻዊ

62) ሱስሚታ ሞሃንቲ፣ ህንዳዊት፣ የህዋ ሥራ ፈጣሪ

63) ቤኔዲክት መንዴል፣ ኮንጎ ዲሞክራቲክ፣ የምግብ ባለሙያ

64) ሱባላክሽሚ ናንዲ፣ ህንዳዊት፣ የጾታ እኩልነት ባለሙያ

65) ትራንግ ንጉየን፣ ቬትናማዊት፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያ

66) ቫን ታይ ንጉየን፣ ቬትናማዊት፣ ዋና ሥራ አስፈጻሚና፣ የአካል ጉዳተኞች መብት ተሟጋች

67) ናታሻ ኖኤል፣ ህንዳዊት፣ የዮጋ ባለሙያ

68) አሌክሳንድሪያ ኦካሲዮ-ኮርቴዝ፣ አሜሪካዊት፣ የምክር ቤት አባል

69) ፋሪዳ ኦስማን፣ ግብጻዊት፣ ዋናተኛ

70) አሻሪያ ፔሪስ፣ ሲሪ ላንካዊት፣ ዲዛይነር

71) ዳኒት ፔሌግ፣ እስራኤላዊት፣ ዲዛይነር

72) ኦተም ፔልቲየር፣ ካናዳዊት፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት መብት ተከራካሪ

73) ስዌቲኒያ ፐስፓ ሌስታሪ፣ ኢንዶኔዢያዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያና ሾፌር

74) ሜጋን ራፒኖ፣ አሜሪካዊት፣ እግር ኳስ ተጫዋች

75) ኦንጃሊ ራኡፍ፣ እንግሊዛዊት፣ ጸሐፊ

76) ቻርሊን ሬን፣ ቻይናዊት፣ የንጹህ ውሃ አቅርቦት መብት ተከራካሪ

77) ማሪያ ሬሳ፣ ፊሊፒናዊት፣ ጋዜጠኛ

78) ጃሚላ ሪቤሮ፣ ብራዚላዊት፣ ጸሐፊና የእኩልነት ተሟጋች

79) ጃዋሂር ሮብሌ፣ እንግሊዝ/ሶማሊያዊት

80) ነጃት ሳሊባ፣ ሌባኖሳዊት፣ የኬሚስትሪ ፕሮፌሰር

81) ናንጂራ ሳምቡሊ፣ ኬንያዊት፣ የዲጂታል እኩልነት ባለሙያ

82) ዚሃራ ሳየርስ፣ ቱርካዊት፣ ሳይንቲስት

83) ሃይፋ ስዲሪ፣ ቱኒዚያዊት፣ ሥራ ፈጣሪ

84) ኑር ሼከር፣ ሶሪያዊት፣ የኮምፒውተር ሳይንስ ባለሙያ

85) ቦኒታ ሻርማ፣ ኔፓላዊት፣ የፈጠራ ባለሙያ

86) ቫንዳና ሺቫ፣ ህንዳዊት፣ የተፈጥሮ አካባቢ ባለሙያ

87) ፕራጋቲ ሲንግ፣ ህንዳዊት፣ ዶክተር

88) ሉቦቭ ሶቦል፣ ሩሲያዊት፣ ጠበቃ

89) ሳማህ ሱቤይ፣ የመናዊት፣ ጠበቃ

90) ካሊስታ ሲ፣ ሴኔጋላዊት፣ የፊልም ጸሐፊና ፕሮዲዩሰር

91) ቤላ ቶርን፣ አሜሪካዊት፣ ተዋናይና አዘጋጅ

92) ቬሮኒክ ቱቬኖት፣ ቺሊያዊት፣ ዶክተር

93) ግሬታ ተንበርግ፣ ስዊዲናዊት፣ የአየር ጸባይ ለውጥ ተሟጋች

94) ፓውላ ቪላሪያል፣ ሜክሲኳዊት፣ የኮምፒውተር ፕሮግራም ቀማሪ

95) ኢዳ ቪታሊ፣ ኡራጓያዊት፣ ገጣሚ

96) ፒዩሪቲ ዋኮ፣ ኡጋንዳዊት፣ የህይወት ተሞክሮ አሰልጣኝ

97) ማሪሊን ዋሪንግ፣ ኒው ዚላንዳዊት፣ ኢኮኖሚስትና የተፈጥሮ አካባቢ ጥበዋ

98) ኤሚ ዌብ፣ አሜሪካዊት፣ እየተከናወኑ ባሉ ነገሮች ላይ በመመርኮዝ ስለሚጪው ዘመን የምትተነብይ

99) ሳራ ዌስሊን፣ ፊንላንዳዊት፣ ጋዜጠኛ

100) ጊና ዙርሎ፣ አሜሪካዊት፣ የሃይማኖት ምሁር

ተያያዥ ርዕሶች