የናሳ ጠፈር ተመራማሪዎች፡ ክርስቲና ኮች እና ጀሲካ ሜር በሴቶች ብቻ የተደረገውን የህዋ ጉዞ አጠናቀቁ

ጀሲካ ሜርና እና ክርስቲና ኮች Image copyright Science Photo Library
አጭር የምስል መግለጫ ጀሲካ ሜር እና ክርስቲና ኮች በጣቢያው ውስጥ

የናሳ የህዋ ተመራማሪዎች ክርስቲና ኮች እና ጀሲካ ሜር የመጀመሪያውን በሴቶች ብቻ የተደረገ የህዋ ጉዞ በማጠናቀቅ ታርክ ሠርተዋል።

ተመራማሪዎቹ የተቋረጠባቸውን የኃይል መቆጣጠሪያ ክፍል ለመተካት ከዓለም አቀፉ የጠፈር ጣቢያ (አይ ኤስ ኤስ) ውጭ ሰባት ሰዓታትን አሳልፈዋል።

ናሳ ህዋ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ ወንጀል ተፈጸመ አለ

ዓለም ለሴቶች እንዳልተሰራች የሚያሳዩ ነገሮች

ናሳ እንዳለው ክሪስቲና ከዚህ ቀደም አራት የህዋ ጉዞዎችን ያደረገች ሲሆን ወደ ህዋ በመጓዝ አሁን 15ኛዋ ሴት ለሆነችው ጀሲካ ግን ይህ የመጀመሪያዋ ነው።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለቱ ሴቶች ለተቀዳጁት ድል በቪዲዮ ደውለው እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋቸዋል።

ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው "በጣም ጀግኖች ናችሁ ፤ ጎበዝ ሴቶች!" ሲሉ የህዋ ጉዞውን በማድረጋቸው አድናቆታቸውን ገልጸውላቸዋል።

እነርሱም "ለሴቶች ብቻ ሳይሆን ሕልም ላላቸው፤ ህልማቸውን ለማሳካት ጠንክረው ለሚሠሩት በሙሉ መነሳሳትን እንፈጥራለን ብለን እናስባለን" ሲሉ ያላቸውን ተስፋ ገልፀዋል።

የኤሌክትሪካል መሃንዲስ የሆነችው ክርስቲና እና የሥነ ሕይወት ዶክተር የሆነችው ጀሲካ አርብ እለት የናሳ የጠፈር አልባሳታቸውን እንደለበሱ ወደ ውጭ ወጥተዋል። ፖርት 6 ወደተባለ ክፍልም በመሄድ 'battery charge-discharge unit' (ቢሲዲዩ) የተባለውን የመንኮራኩሩ አካልን በሌላ ተክተዋል።

ከጥቅም ውጭ የሆነውን ቢሲዲዩ የተባለውንም አካል በመውሰድ ወደ ኦክስጅን ጭምብላቸው የተመለሱ ሲሆን፤ ምርምር ተደርጎበት በሚቀጥለው የስፔስ ኤክስ ድራገን የጠፈር ጉዞም እንደገና ይሞላል ተብሏል።

ወደ መሬት ሲመለሱም የዲሞክራት ፕሬዚደንት እጩ የነበሩት ካማላ ሃሪስ "የጠፈር ጉዞው ከታሪክ በላይ ነው" ሲሉ በትዊተር ገፃቸው አስፍረዋል።

ናሳ ባለፈው ሚያዚያ ወር ኮች ከስራ ባልደረቦቿ አንና ማክሌይን ከመንኮራኩሯ ውጭ በመንሳፈፍ የሴቶች ብቻ የጠፈር ጉዞ አካል ይሆናሉ ብሎ ቢያሳውቅም ለማክሌይን የሚሆን መካከለኛ መጠን የጠፈር ልብስ ባለመገኘቱ ከመንኮራኩር ውጭ የመራመድ (መንሳፍፈፍ) እቅድ ሳይሳካ ቀርቷል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በሌላ ፕላኔት ላይ ውሃ ተገኘ

በጎርጎሮሳዊያኑ 1984 በቀድሞዋ ሶቭየት ህብረት ሳልዩት 7 የህዋ ጣቢያ ለሦስት ሰዓታት ከ35 ደቂቃ ያህል በመቆየት ሩሲያዊቷ ስቬትላና ሳቪትስካያ የመጀመሪያዋ ሴት ነበረች።

በታሪክ ወደ ህዋ የተጓዘው የመጀመሪያው የቀድሞው የሶቪየት ኅብረት ተመራማሪ አሌክሲ ሌኦኖቭ ሲሆኑ በዚህ ወር መጀመሪያ በ85 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

ባሳለፍነው ማክሰኞ ናሳ የሚቀጥሉት የህዋ ተመራማሪዎች ሊለብሱት የሚችሉት እና ወደ ጨረቃ የሚጓዙ ተመራማሪዎችን አዲስ ልብስ ያስተዋወቀ ሲሆን ስሙም 'አዲሱ የጨረቃ ልብስ' ይሰኛል። ለሁሉም ዓይነት የሰውነት ቅርፅና መጠን ጋር ተስማሚ ሆኖ የተዘጋጀ ነው።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ