የመንታ እናቷ ኬንያዊቷ የማራቶን ሪከርድ ባለቤት

ኬንያዊቷ የማራቶን ሬከርድ ባለቤት Image copyright AFP

አትሌቶች ለማሸነፍ የሚገፋፋቸውና ፅናት የሚሰጣቸው አንድ ነገር አለ። ለኬንያዊቷ ማራቶን ሪከርድ ባለቤቷ ብሪጅድ ኮስጌይ፤ ፈታኝ የልጅነት ሕይወቷ ነው።

"አስተዳደጌን ሳስበው ምን ያህል አስቸጋሪ እንደነበር ሳስታውስ ወደዛ መመለስ እንደሌለብኝ በማሰብ በርትቼ እንድሰራ ያደርገኛል" በማለት የ25 አመቷ ሯጭ ትናገራለች።

የመጀመሪያ ያሸነፈችበትን ማራቶን ከአራት ዓመት በፊት የሮጠችው ብሪጅድ ኮስጌይ በታሪክ ፈጣኗ ሴት ለመሆን በቅታለች።

"ሥልጣን ለደም ግፊት አጋልጦኛል" ኃይሌ ገብረሥላሴ

በሴቶች ማራቶን የዓለምን ሪከርድ የሰበረችው ኬንያዊቷ አትሌት

በባለፈው ሳምንት በቺካጎ በተደረገው ውድድር ለአስራ ስድስት አመታት ያህል በእንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ ተይዞ የነበረውን ሪከርድ በ81 ሰኮንዶች አሻሽላለች።

2፡14፡04 ሰዓቷን ለማምጣት ከአሰልጣኟ ኤሪክ ኪማይዮ ጋር ሰለቸኝ፣ ደከመኝ ሳትል ለስድስት ወራት ያህል ሰልጥናለች።

መስከረም ወር ላይ ዶሃ ተደርጎ በነበረው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮንሺፕ አገሯን ወክላ እንድትወዳደር ጥሪ ተደርጎላት የነበረ ቢሆንም ግብዣውን አልተቀበለችውም ነበር።

"በዚህ ውድድር ላይ መሳተፍ እንደማትችል ተናግረን ነበር፤ ምክንያቱም ለተለየ ውድድር እየተዘጋጀን ስለነበር። ስለ ውድድሩ ግን ምንም ነገር ይፋ ከማድረግ ተቆጥበን ነበር ምክንያቱም ጫና እንዳይበዛባት በሚል ፍራቻ ነው" በማለት አሰልጣኟ ኪማይዮ ለቢቢሲ ተናግሯል።

"አንድ አትሌት በህይወቱ የሚያስደስተው የአለም ሪከርድን መስበር ነው" ዮሚፍ ቀጀልቻ

ጊነስ ዎርልድ ሪከርድስ፡ «ስለተተከሉት ዛፎች ከኢትዮጵያ የደረሰን ማስረጃ የለም»

በውድድሩ ላይ ያላት ሥርዓትና ፅናት ብሪጅድን የተለየች ያደርጋታል።

ታዳጊም በነበረችበት ወቅት ሥልጠናዋን በሥርዓት እንደምታከናውን ከፍተኛ ብቃትና ችሎታ እንደነበራት የሁለተኛ ደረጃ ተማሪ በነበረችበት ወቅት ያሰለጠኗት ሮበርት ንጊሲሬይ ለቢቢሲ አስታውሰዋል።

ወደ ትምህርት ቤት በሩጫ

በእናት ብቻ ያደገችው አትሌቷ ስድስት እህትና ወንድሞች አሏት።

ብዙ ሯጮችን ካፈራችው ኤልገዮ ግዛት የመጣችው አትሌቷ የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ በነበረችበት ወቅት ከቤቷ ትምህርት ቤት በሩጫ ነበር የምትመላለሰው።

"ከቤት ትምህርት ቤት ያለው ርቀት አስር ኪሎ ሜትር ነው። ላለማርፈድም ስል በሩጫ ነው እመላለስ የነበረው። በምሮጥበትም ወቅት አንዳንድ አትሌቶችም ሲሰለጥኑ አይ ነበር። እንደነሱም መሆን እችላለሁ አልኩኝ" ትላለች።

በመካከለኛ ርቀትም መወዳደር ጀመረች። ምንም እንኳን ከፍተኛ ብቃት ብታሳይም ሃገሯን እንድትወክል አልተመረጠችም።

የትምህርት ቤት ክፍያዋን ለመክፈል እየታገሉ የነበሩትም እናትዋ እጅ እያጠራቸው መጣ። ከሰባት ዓመት በፊትም ትምህርቷን ለማቋረጥ ወሰነች።

"የትምህርት ቤት ክፍያው አርባ ሦስት ሺ ብር የሚጠጋ ሆነ፤ 'እናቴ እንበደራለን ተማሪ' ብትለኝም እስከመቼ እንበደራለን ብየ አቋርጨ ወጣሁ" ብላለች።

የ22 ዓመት ክብረ ወሰንን ያሻሻለው የ19 ዓመቱ ወጣት

የመንታዎች እናት

የአስራ ሰባት ዓመቷ አትሌት ትምህርቷን ካቋረጠች በኋላም ትኩረቷን ሙሉ በሙሉ ሩጫው ላይ አድርጋ ቤተሰቦቿን መርዳት ጀመረች፤ ለእህቶቿና ለወንድሞቿም የትምህርት ቤት ክፍያ የምትከፍለውም እሷ ሆነች።

በጊዜው ከነበረው ወንድ ጓደኛዋ ከአሁን ባለቤቷ ማቲው ኮስጌይ ጋር ነበር አብረው የሚሮጡት። መንታ ልጆቿን ስትወልድ ለአንድ ዓመት ያህል ከሩጫው ዓለም ርቃ ነበር።

እናትነትም የጥንካሬ ምንጭ ሆናት። ከአራት ዓመታት በፊትም ካቆመችበት ሩጫዋን በመቀጠል መኖሪያ አካባቢዋ የሚገኝ ማሰልጠኛ ካምፕም አባል ሆነች።

ሙሉ በሙሉ ትኩረቷን ሩጫው ላይ ብታደርግም ለሴት አትሌቶች ከቤተሰብ ወይም ከልጆች መራቅ ቀላል ባይሆንም የባሏ ድጋፍ እንዳልተለያት ትናገራለች።

"ባሌ ምንም እንዳልጨነቅና ልጆቹንም የመንከባከብ ኃላፊነቱንም ሙሉ በሙሉ እንደሚወጣ ነገረኝ። ሩጫው ላይ እንዳተኩርና ልጆቼም ቤት ስመጣ ቅዳሜና እሁድ ብቻ ማየት እንደሚለምዱም አግባባኝ" ትላለች።

የዛሬዋን አዲስ አበባ በፎቶ መሰነድ ለምን አስፈለገ?

እናቴ ደስተኛ ናት

ማሰልጠኛ ካምፑን በተቀላቀለች በጥቂት ወራት ውስጥ በጎርጎሳውያኑ 2015 በፖርቹጋል በተካሄደው ውድድር አሸነፈች።

ውድድሯንም ያሸነፈችው ሁለተኛ ከወጣችው በአራት ደቂቃ ልዩነት ቀድማ ነው።

በማሰልጠኛ ካምፑ ውስጥ ብዙ የማራቶን ተወዳዳሪዎች መኖራቸው ማራቶን ላይ እንድታተኩር አድርጓታል።

በአብዛኛው የምትሰለጥነው ከወንድ ማራቶን ተወዳዳሪዎች ጋር ነው።

ቤይሩት፡ ባለፉት 7 ወራት 34 ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል

በአሁኑ ወቅት የ2019 ምርጥ የማራቶን አትሌት የተባለች ሲሆን በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ ትኩረቷ ኦሎምፒክስ ነው።

ቢቢሲ ባናገራት ወቅት እናቷን ለመጠየቅ ወደ መንደሯ እየሄደች ነበር። በአካባቢዋም ከዚህ ቀደም ባሸነፈችው ብር ቤት የገዛች ሲሆን ከባለቤቷና ልጆቿም ጋር ለመኖር ነበር እያቀናች ያለችው።

"እናቴ ሪከርድ በመስበሬ በጣም ደስተኛ ናት። ቤት እስክመለስም በጉጉት እየጠበቀችኝ ነው" ብላለች።

ተያያዥ ርዕሶች