የዚምባብዌ አልማዝ ማዕድን ቁፋሮ በጉልበት ብዝበዛ ይሆን የሚካሄደው?

የአልማዝ ማዕድን Image copyright Getty Images

የአሜሪካ መንግሥት ከዚምባብዌ የሚመጣውን ያልተጣሩ የአልማዝ ምርቶችን በማዕድን ቁፋሮው ወቅት የጉልበት ብዝበዛን ይጠቀማሉ በሚል አግጃለሁ ብሏል።

ዚምባብዌ ጉዳዩን ተራ ውንጀላ ነው በማለት አጣጥለዋለች። የመረጃ ሴክሬታሪው ኒክ ማንግዋና እንደሚሉት አሜሪካ ምንም ዓይነት መረጃ የላትም "መረጃ የላቸውም፤ ወይም ያሳሳታቸው አካል አለ" ብለዋል።

"የተርባይኖች መቀነስ በሚመነጨው ኃይል ላይ የሚያመጣው ለውጥ የለም" የህዳሴ ግድብ ዋና ሥራ አስኪያጅ

የቀድሞው ፕሬዝደንት ልጅ በጉልበት ብዝበዛ ወንጀል ተፈረደባቸው

የማዕድን ቁፋሮው በምስራቃዊቷ አገሪቷ ክፍል ማራንጅ ግዛት አካባቢ የሚካሄድ ሲሆን፤ በዓለም ላይ ካሉ ከፍተኛ የአልማዝ ምርት የሚገኝበት ሲሆን በኢኮኖሚ ቀውስ ለምትንገዳገደው ዚምባብዌም የውጭ ምንዛሬን በማስገኘት አገሪቷን የሚያንቀሳቅሳት ነው።

የአሜሪካ ውንጀላ ምንድን ነው?

የአሜሪካ ከተሞች የሥራ ልምዶችን የሚፈትሸው ድርጅት እንዳሳወቀው በማዕድን ቁፋሮ ሥራ ለመሰማራትና በተከለለው ቦታ ላይ ፍቃድ ለማግኘት ለፀጥታ ኃይሎች ጉቦ መክፈል ነበረባቸው።

የአሜሪካ ጉምሩክና ድንበር ኤጀንሲ ተወካይ ብሬንዳ ስሚዝ እንደተናገሩት ሠራተኞች ያለ ፈቃድ የማዕድን ቁፋሮ አካባቢውን ለቀው መሄድ እንደማይችሉና፤ እምቢተኝነትን ያሳዩት ደግሞ አካላዊና ወሲባዊ ቅጣቶች እንዲሁም ለእስር ይዳረጋሉ ተብሏል።

የአሜሪካ መንግሥት እንዳሳወቀው እንዲህ ዓይነት ጥቃቶችን በመረጃ አጠናቅረን ይዘናል ብለዋል።

ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ረቂቅ ህግ የሞት ቅጣት ተካቶበታል

"ሰልፍ የዜጎች መሰረታዊ መብት ነው" መስፍን ነጋሽ

መረጃው ምንድን ነው?

ጋዜጠኞችም ሆነ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች ቡድን አካባቢውን እንዲጎበኙ የማይፈቀድላቸው ሲሆን፤ አካባቢውን ለማየትም ልዩ የሆነ ፍቃድ ያስፈልጋል።

በማራንጌ የአልማዝ ቁፋሮ ቦታ ላይ የሥራ ሁኔታዎችን የሚቆጣጠረው ቡድን እንዳሳወቀው የጉልበት ብዝበዛ በተለይም የግዳጅ ሥራ እንደሚከናወን አሳውቋል።

የቦቻ ዳይመንድ ትረስት ኩባንያ ሊቀመንበር ሞሰስ ሙክዋዳ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፤ የአካባቢው ሰዎች ተገደው በማዕድን ቁፋሮው ሥራ እንደተሰማሩ አጋልጠዋል።

አንዳንድ ኩባንያዎች የግዳጅ ሥራ አለ ለማለት አልደፈሩም።

ለማዕድን ቁፋሮ ሰራተኞች መብት የሚታገለው ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ የተባለው ድርጅት ከአስራ ስምንት ዓመት በታች ያሉ ታዳጊዎች አካላዊ ጥቃት እንደደረሰባቸው ቢገልፅም ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል ከሚለው አስተያየት ተቆጥቧል።

"ሰራተኞች በግዳጅ ተሰማርተዋል የሚለውን ሃሳብ ሙሉ በሙሉ አናጣጥለውም፤ ከአሜሪካ መንግሥትም ሆነ ከየትኛውም አካል በግዳጅ የተሰማሩ ሰራተኞች እንዳሉ መረጃ አልደረሰንም። ማን ማንን እያስገደደ ነው የሚለውንም የበለጠ ማወቅ እንፈልጋለን" በማለት የድርጅቱ ቃል አቀባይ ሲሚሶ ምሌቩ ተናግረዋል።

Image copyright AFP/Getty Images

በማራንጄ የማዕድን ቁፋሮ ቦታ ላይ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ውንጀላዎች ሲቀርቡ የመጀመሪያው አይደለም።

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በተደጋጋሚ እንዳሳወቁት ከአካባቢው የሚመጣው አልማዝ "ከግጭት አካባቢ የተገኘ አልማዝ" ስለሆነ ወደ ውጭ የሚላከው የአልማዝ መጠን ሊገደብ ይገባል በሚል አሳውቀው ነበር።

በጎርጎሳውያኑ 2011 ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ በአካባቢው የከፋ ድብደባና ወሲባዊ ጥቃት እንደሚደርስም መረጃ ሰብስቧል።

"በማራንጌም ሆነ ከተለያዩ አካባቢዎች የሚመጡ የአልማዝ ምርቶች በከፍተኛ ሁኔታ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ቢያጠላባቸውም ወደ አለም አቀፉ ገበያ መድረሳቸው አልቀረም" በማለት ዘ ሴንተር ፎር ናቹራል ሪሶርስስ ገቨርናንስ አስታውቋል።

ሰራተኞች ላይ በሚደርሱ ጥቃቶች እንዲሁም ባለው የከፋ ሁኔታ አርባ ሰዎች በየአመቱ ይሞታሉ ተብሏል።

ቤይሩት፡ ባለፉት 7 ወራት 34 ኢትዮጵያዊያን ህይወታቸውን አጥተዋል

ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት

የሰራተኞች መብት በዚምባብዌ

የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ነኝ የሚለው ድርጅት ሂውማን ራይትስ ዋች ባለፈው ዓመት ባወጣው ሪፖርት በሃገሪቷ በሚገኙ የትምባሆ እርሻዎችም የግዳጅ ሥራ እንደተንሰራፋ ይፋ አድርጓል።

የአሜሪካ መንግሥትም እንዲሁ ባለፈው አመት የህፃናት ጉልበት ብዝበዛ እንደሚከናወን አንድ መረጃ አውጥቶ ነበር።

ዚምባብዌ በበኩሏ የተባበሩት መንግሥታት የጉልበት ብዝበዛን ለማስቀረት ያፀደቃቸውን ሕጎች በዚህ ዓመት እንደተቀበለችና የግዳጅ ሥራ ልምድንም ለማስቀረት እየሞከሩ እንደሆነ ገልፃለች።