ሲንቶያ ብራውን ሎንግ፡ ''የወሲብ ብዝበዛ ተጠቂ መሆኔን ለመረዳት ዓመታት ፈጅቶብኛል"

ሲንቶያ ብራውን ሎንግ Image copyright CBS
አጭር የምስል መግለጫ ሲንቶያ ብራውን አስራ አምስት ዓመታትን በእስር አሳልፋለች

ሲንቶያ ብራውን ገና 16 ዓመቷ ነበር አንድ ደላላን ተኩሳ በመግደል የእድሜ ልክ እስራት ሲፈረድባት። ግለሰቡ በወቅቱ ወሲብ ለመፈፀም ከመንገድ ላይ ነው የወሰዳት።

ከቤት ጠፍታ ወደ መንገድ ላይ የወጣችው ሲንቶያ ሕገ ወጥ የወሲብ አዘዋዋሪ ግለሰብ አማካኝነት በወሲብ ንግድ እንድትሰማራ ሆናለች።

በዚህ ወቅት ነው የ43 ዓመቱን ደላላ ጆኒ አለንም የገደለችው።

የተነጠቀ ልጅነት

"በወንድሜ ለአምስት ዓመታት ተደፍሬአለሁ"

በጎርጎሳውያኑ 2004 በግድያ ተወንጅላ ለ51 ዓመታት፣ ስልሳ ዓመት እስኪሞላት በእስር እንድትቆይ ተፈርዶባት ነበር።

ነገር ግን በነሐሴ ወር የቴኔሲ ኃገረ ገዥ የምህረት ይግባኝ በመፍቀዳቸው በዚህ ዓመትም ነፃ ሆናለች።

ግለሰቧ ነፃ እንድትወጣ ዘመቻ ተካሂዶ የነበረ ሲሆን ሪሃናና፣ ኪም ካርዳሽያን በመሳሳሉ ታዋቂ ግለሰቦችም የተደገፈ ነበር።

የ31 ዓመቷ ሲንቶያ የሕይወት ልምዷን ባጋራችበት ወቅት "የወሲብ ንግድ ብዝበዛ ተጠቂ መሆኔን ለማወቅ ዓመታት ፈጅቶብኛል" ብላለች።

"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው"

በባንግላዴሽ ባለቤቱን አስገድዶ ፀጉሯን የላጨው በቁጥጥር ስር ዋለ

"በሃያዎቹ ላይ ሆኜ ነው ሕገወጥ የወሲብ አዘዋዋሪ በሆነ ግለሰብ ተጠቂ መሆኔን ያወቅኩት" በማለት ለሲቢኤስ የዜና ወኪል ተናግራለች።

"ለዓመታትም ያህል ምን አስብ ነበር . . . ነግረውኛል በወሲብ ንግድ የተሰማራሁ ታዳጊ መሆኔንና የማደርገውን የማውቅ መሆኔን፤ ልክ ናቸው እል ነበር" ብላለች።

ሲንቶያ ፈታኝ የሚባል አስተዳደግ ነው የነበራት።

ከቤት ጠፍታ በሕገወጥ የወሲብ ዝውውር የተሰማራ ኩትሮት የሚባል ግለሰብ ጋር ተዋወቀች፤ ሰውየውንም እንደ ወንድ ጓደኛዋ ታየው ጀመር።

ግለሰቡ ተደጋጋሚ ወሲባዊ ጥቃቶችን ከማድረስ በተጨማሪ ገንዘብ እንድታመጣም በወሲብ ንግድ አሰማራት።

ከቤት መጥፋቷ የእግር እሳት የሆነባት ሲንቶያ፤ እናቷም ላይ ከፍተኛ ኃዘን በማስከተሏም እንደምትፀፀት ትናገራለች።

"አንደኛውና ዋነኛው ፀፀቴ እናቴን ከፍተኛ ኃዘን ላይ መጣሌ ነው። እኔን ከዛ ሕይወት ለማውጣትም በምታውቀው ሁሉ ሞክራለች" ብላለች።

ወደ ኋላ መለስ ብላ ስታይም በሕገወጥ ወሲብ አዘዋዋሪው ሥር እንዴት እንደወደቀች ስታስበው የህፃንነት አዕምሮዋና ምንም አለማወቋ ምከንያት እንደሆነም ትናገራለች።

"ህፃን በመሆኔም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሕይወት ውስጥ እንድገባ አድርጎኛል። ለግለሰቡም ቀላል ሆኖለታል" ትላለች።

Image copyright Nashville Police Department
አጭር የምስል መግለጫ ሲንቶያ ብራውን አምሳ አንድ አመት ተፈርዶባት ነበር

እስር ቤት በገባችበትም የመጀመሪያዎቹ ጊዜያት በከፍተኛ ንዴትና እፍረትም ትሰቃይ እንደነበር ገልፃለች።

በነፍስ ማጥፋት እድሜ ልክ የተፈረደባት አሜሪካዊት በነጻ ተሰናበተች

"ሌሎች ሴቶች ላይ የአሲድ ጥቃት ሳይ ይረብሸኛል፤ ህመሜን ያስታውሰኛል" ካሚላት መህዲ

"ለሆነው ነገር በሙሉ ራሴን ጥፋተኛ አደረግኩኝ፤ ራሴንም እወነጅል ነበር" ብላለች።

"እናም ራሴንም ይቅር ለማለትም ሆነ የነበርኩበት ሕይወት ውስጥ እንዴት እንደገባሁ ለማወቅ ረዥም ሂደት ነበረው። እነዚህን ውሳኔዎች በፈቃደኝነት የገባሁባቸው አይደሉም። ምክንያቱም ልጅ ነበርኩ" በማለት ታስረዳለች።

በእስር ቆይታዋም ወቅት በዲግሪ የተመረቀች ሲሆን የአሁኑ ባሏን ጄ ሎንግንም የተዋወቀችው በዚሁ ወቅት ነው።

ደብዳቤም ይፅፍላት የነበረ ሲሆን ስትፈታም የጋብቻ ሥነ ሥርዓታቸውን ፈፅመዋል።

ሲንቶያ የባሏ ደብዳቤዎች ለየት ያሉና አስደናቂ ነበሩ ትላለች።

"በጣም ከምቀርበው የልብ ጓደኛዬ ጋር እንደምኖር ነው የሚሰማኝ" ብላለች።

Image copyright CBS News

የመፈታት ቅድመ ሁኔታዋም ለማህበረሰቡ አስተዋፅኦ ማድረግን ያካተተ ሲሆን፤ ፀባይ ማረሚያ የገቡ ታዳጊ ሴቶች ጋር አብራ ትሰራለች።

አሲድን እንደ መሳሪያ

"ለታዳጊዎች ታሪኬን አጋራሁዋቸው። ጤነኛ ግንኙነት ማለት ምንድን ነው? ማለፍ ስለሌለባቸው መስመሮች አዋይቻቸዋለሁ። ከልጆቹም ጋር መልካም ግንኙነት መስርተናል" ያለችው ሲንቶያ አክላም "ከጎናቸው አንድ ሰው እንደቆመም ማሳየት እፈልጋለሁ" የምትለው ሲንቶያ ከታሪኳም እንደሚማሩ ተስፋን ሰንቃለች።

"በዛን ጊዜ በዚህ ዓይነት ውጥንቅጥ ያለፈች ሰው ባገኝና፤ የሠራችውንም ስህተት እንዴት መድገም እንደሌለብኝና፤ እንዴት እንደተወጣችው ብረዳ፤ ራሴንም በዛች ሰው ዐይን ማየት ብችል የተለየ ሕይወት ይኖረኝ ነበር" ትላለች።