የአውስትራሊያ ጋዜጦች የአገሪቱን ሕግ ለመቃወም በ'ጥቁር የተሰረዘ' የፊት ገፅ ይዘው ወጡ

የዴይሊ ቴሌግራፍ እና ዘ ሲድኒ ሞርኒን ሄራልድ ጋዜጦች በጥቁር የቀለመ የፊት ገፆች
አጭር የምስል መግለጫ ባሳለፍነው ሰኞ የአውስትራሊያ ጋዜጦች የፊት ገፃቸውን 'ሳንሱር' በማድረግ ይዘው ወጥተዋል

የአውስትራሊያ ትልቁ ጋዜጣ ባልተለመደ መልኩ በጥቁር ቀለም ሳንሱር የተደረገ የፊት ገፅ ይዞ በመውጣት በፕሬስ ሕጉ ላይ ያለውን ተቃውሞ በመግለፅ አንድነቱን አሳይቷል።

'ኒውስ ኮርፕ አውስትራሊያ' እና 'ናይን ማስትሄድስ' የተባሉ ጋዜጦች ጽሁፎቹን በጥቁር በማቅለም 'ሴክሬት' የሚል በቀይ አልፎ አልፎ የታተመበት የፊት ገፅ ይዘው ወጥተዋል።

"የግሉ ሚዲያ ላይ ስጋት አለኝ" መሐመድ አደሞ

ጋዜጠኞች ስለ ለውጡ ማግስት ሚዲያ ምን ይላሉ?

የተቃውሞው ዋና ዓላማ ጋዜጠኞች በአገሪቷ ያለው "የምስጢር ባህል" ለሥራችን ማነቆ ፈጥሮብናል ያሉትን የአገሪቷ ብሔራዊ የደህንነት ሕግን መቃወም ነበር። የአገሪቷ መንግሥት በበኩሉ የፕሬስ ነፃነትን አስፍኛለሁ፤ ይሁን እንጅ ማንም ሰው ከሕግ በላይ ሊሆን አይችልም ብሏል።

ባሳለፍነው ሰኔ ፖሊስ የአውስትራሊያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን እና የኒውስ ኮርፕ አውስትራሊያ ጋዜጠኞችን ላይ የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በበርካታ ሰዎች ዘንድ ቁጣን ቀስቅሶ ነበር።

የሚዲያ ተቋማቱ ጥቃቱ የተፈፀመው ጋዜጦቹ አፈትልከው የወጡ መረጃዎችን መሠረት ካደረጉ ፅሁፎች ጋር የተያያዘ እንደሆነ ተናግረዋል። አንደኛው ክስ ከጦር ወንጀል ጋር የተያያዘ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ የመንግሥት ተቋም የአውስትራሊያ ዜጎችን የመሰለል ሙከራ አድርጓል ሲሉ ዘግበዋል የሚል ነው።

'ዘ ራይት ቱ ኖው ጥምረት' ሰኞ እለት የተካሄደው ዘመቻ በበርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎች ራዲዮ እና የኦን ላይን ድረ ገፆች ድጋፍ አግኝቷል።

የኒውስ ኮርፕስ አውስትራሊያ ሥራ አስኪያጅ ማይክል ሚለር የፊት ገፃቸውን በጥቁር ቀለም ሰርዘው የወጡ 'ዘ አውስትራሊያ' እና 'ዘ ዴይሊ ኔሽን' ጋዜጦችን ምስል በትዊተር ገፃቸው አጋርተዋል። "መንግሥት ከእኔ የሚደብቀው ምንድን ነው?" ሲሉ እንዲጠይቁ ሕዝቡን አሳስበዋል።

ዘ ሲድኒ ሞርኒንግ ሄራልድ እና ዘ ኤጅ የተባሉት ጋዜጦችም ተመሳሳይ ገጽ ይዘው ነበር የወጡት።

የኤቢሲ ማኔጅንግ ዳይሬክተር ዴቪድ አንደርሰን "አውስትራሊያ በዓለማችን 'የምስጢር ዴሞክራሲ' ያላት አገር በመሆኗ አደጋ ላይ ናት" ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ስኮት ሞሪሰን እንዳሉት የፕሬስ ነፃነት ለአውስትራሊያ ዴሞክራሲ ጠቃሚ ነው፤ ይሁን እንጅ የሕግ የበላይነት ደግሞ መከበር አለበት ብለዋል። ይህ እንግዲህ እኔ ወይም ጋዜጠኞች አሊያም ማንኛውንም ሰው ያካትታል" ሲሉ ተናግረዋል።

የፕሬስ ነፃነት የተመለከተው ጥያቄም በሚቀጥለው ዓመት ለምክር ቤት እንደሚቀርብ አክለዋል።

የሚዲያ ተቋማቱ የሚፈልጉት ምንድን ነው?

በአገሪቷ ባለፉት ሁለት አስርት ዓመታት ተግባራዊ እየሆነ ያለው የብሔራዊ ደህንነት ሕግ የምርመራ ጋዜጠኝነት ፈተና ሆኗል፤ የሕዝብ መረጃ የማግኘት መብትን ሸርሽሯል ሲሉ ባካሄዱት ዘመቻ ላይ አሳስበዋል።

ባለፈው ዓመት አዲሱ ስለላን የሚቆጣጠር ሕግ ከተዋወቀ ጀምሮ የሚዲያ ተቋማት ጋዜጠኞች እና የመረጃ ምንጮች በጣም ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን እንዲዘግቡ ሕጉ እነሱን እንዳያካትት ሲያግባቡ ቆይተዋል።

የሚዲያ ተቋማቱ በሌሎች ዘርፎችም ተመሳሳይ ነፃነት እንዲኖር ጠይቀዋል።።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ