በሺዎች የሚቆጠሩ በጎች በዓመታዊው ፌስቲቫል ለመሳተፍ ወደ ማድሪድ ጎዳናዎች ተመዋል

በፌስቲቫሉ የተገኙ በጎች Image copyright AFP

የማድሪድ መንገዶችና ጎዳናዎች ከወትሮው በተለየ ተጨናንቀው ነበር ምክንያቱም ከሁለት ሺ በላይ በጎች መታዊውን ፌስቲቫል ለመታደም በመምጣታቸው ነው።

ታሪክ ወደ ኋላ ሲመዘዝ የአሁኗ የስፔን መዲና በጥንት ጊዜ እረኞች የቀንድ ከብቶቻቸውን ክረምት በሚሆንበት ጊዜ ወደ ደቡባዊ ክፍል የሚወስዱባት መስመር ነበረች።

ፊየስታ ደ ላ ትራንስሂዩማኒካ (የቀንድ ከብቶችን ማስተላለፍ) በሚለው በዚህ ፌስቲቫል በነዋሪው እንዲሁም በባለሥልጣናት ይደገፋል።

"የወሲብ ብዝበዛ ተጠቂ መሆኔን ለመረዳት ዓመታት ፈጅቶብኛል"

የናሳ ተመራማሪዎች በሴቶች ብቻ የተካሄደውን የህዋ ጉዞ አጠናቀቁ

በጎርጎሳውያኑ 1994 የተጀመረው ይህ ፌስቲቫል የገጠሪቷ ስፔይንን አመጣጥ ለመዘከር ያለመ ነው።

Image copyright EPA
Image copyright EPA

የመካከለኛውን ዘመን ሕግጋትን በመጠቀም እረኞቹ እንስሳታቸውን ለማሳለፍና ከተማን አቆራርጠው ለመሄድ ክፍያን መክፈል የሚጠበቅባቸው ሲሆን እሱንም ለማስታወስ በአሁኑ ሰዓት ክፍያ ይፈፅማሉ።

የዛሬዋን አዲስ አበባ በፎቶ መሰነድ ለምን አስፈለገ?

በየአመቱም እንስሳቱ በሰላም እንዲያልፉ የእረኞቹ ዋና አለቃ ከከንቲባዋ ጋር የክፍያውን ስምምነት ይፈፅማሉ።

በጎርጎሳውያኑ 1418 የነበረውን የከተማዋን ምክር ቤት ትዕዛዝ በመጠቀምም አንድ ሺ እንስሳትን ለማሳለፍ 50 ማራቬዲስ አል ሚላር ወይም አስራ ዘጠኝ ብር ያህል ይከፈላል።

Image copyright AFP

በጎቹን አጅበው የሚመጡ ግለሰቦችም በባህላዊ ልብስ ለብሰው ፌስቲቫሉን ለመታደም መጥተዋል።

ከተለያዩ ከተሞች የመጡ ግለሰቦች በታደሙበት በዚህ ፌስቲቫል ከትራፊክ እንቅስቃሴም ነፃ ተደርጎም ነበር።

"አላወቅንም ነበር ግን እድለኞች ነን" በማለት አንድ ቱሪስት ለሮይተርስ ዜና ወኪል ተናግረዋል።

የሆሊውዱ ሃኪም ገብረወልድን ያውቁታል?

"ትናንትና ነው የደረስነው እናም ፌስቲቫሉ ዛሬ መሆኑ ተነገረንም። በዓመት አንድ ጊዜ የሚከበር ፌስቲቫል ላይ እኛም ተገኝተን መገጣጠማችን ያስደስታል" ብለዋል።

Image copyright AFP

በጎቹ በሙሉ አንገታቸው ላይ ደወል ያንጠለጠሉ ሲሆን የማድሪድ ጎዳናዎችን በጩኸት ሞልተዋት ነበር።

በትናንትናው ዕለት ጥዋት የነበረው ይህ ፌስቲቫል በከተማዋ ትልቅ በሚባለው ካዛ ዴ ካምፖ ተብሎ በሚጠራው ፓርክም ተካሂዷል።

ከፓርኩም ተነስተው ባህላዊውን ክፍያ ለመፈፀም ወደ ማዘጋጃ ቤት የሄዱ ሲሆን ወደ ከሰዓትም አካባቢ ዝግጅቱ ተጠናቋል ተብሏል።

ከ2ሺህ በላይ በጎች በተጨማሪ መቶ የሚሆኑ ፍየሎችም እንደተሳተፉ ሮይተርስ ዘግቧል።

Image copyright EPA