የሮማ ክለብ ደጋፊዎች በሮናልዶ ቬይራ ላይ የዘረኝነት ጥቃት አደረሱበት

ሮናልዶ ቬይራ Image copyright Getty Images

የጣልያኑ ክለብ ሳምፕዶሪያና የእንግሊዙ ከሃያ አንድ ዓመት በታች ተጫዋች ሮናልዶ ቬይራ ከሮማ ክለብ ደጋፊዎች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶበታል።

የዝንጀሮ ድምፆችን በማውጣት ተጫዋቹ ላይ የዘረኝነት ጥቃት እንዳደረሱበትም ተገልጿል።

ይኸው ሁኔታ የተፈጠረው የጣልያኑ ሴሪያ ጨዋታ ሲካሄድ በነበረበት በሳምፕዶሪያ ሉይጂ ስታዲየም ሲሆን ክለቦቹ ያለግብ ተለያይተዋል።

ደቡብ አፍሪካዊቷ የፓርላማ አባል የዘረኝነት ጥቃት ደረሰባት

ዘረኝነት ሽሽት - ከአሜሪካ ወደ ጋና

የሮማ ደጋፊዎች የዝንጀሮ ድምፅ በማስመሰል ተጫዋቾቹ ላይ መጮሃቸውን ተከትሎ ክለቡ በትዊተር ገፁ ይቅርታን አስፍሯል።

"ሰምቻቸዋለሁ ግን ስለዚህ ጉዳይ ማውራት አልፈልግም" በማለት የ21 ዓመቱ ቬይራ ለጣልያን ቴሌቪዥን የተናገረ ሲሆን "እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ብዙ ጊዜ ይፈጠራል፤ እንዲህም መሆን የለበትም" ብሏል።

ጊኒ ቢሳው የተወለደው ተጫዋች ወደ እንግሊዝ የሄደው ገና በህፃንነቱ ሲሆን፤ ከሊድስ ክለብ ወደ ሳምፕዶሪያ የተዛወረው ባለፈው ዓመት ነው።

አቶ ታደሰ ካሳ፡ "…ወሎዬ ነኝ፤ መታወቂያዬም አማራ የሚል ነው"

ከዚህ ቀደምም በእግር ኳስ ሜዳዎች የዘረኝነት ጥቃቶች የደረሱ ሲሆን ባለፈውም የፊዮረንቲናው ክለብ ተከላካይ ብራዚላዊው ዳልበርት በአትላንታ ደጋፊዎች የዘረኝነት ጥቃት ደርሶብኛል ማለቱን ተከትሎም ጨዋታው ተቋርጦ ነበር።

ሮማ ክለብም ለተከላካያቸው ጁዋን ጂሰስ በማህበራዊ ሚዲያ የዘረኝነት ዘለፋን ልኳል ያለውን ግለሰብም ምንም ጨዋታ እንዳይመለከት አግዶታል።

በኢንተር ሚላን አጥቂ ሮሜሉ ሉካሉ የዘረኝነት ድምፆችን አሰምቷል ተብሎ የነበረው ካሊጋሪ ክለብ ነፃ ተደርገዋል። ይህ ክለብ በባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የዘረኝነት ጥቃቶች ጋር በተያያዘ ሦስት ጊዜ ምርመራ ተከፍቶበት ነበር።

ተያያዥ ርዕሶች