በአምቦ ዩኒቨርሲቲ የሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን የባህል ጥናት እና ምርምር ማዕከል ተመረቀ

ሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን Image copyright Tsehai Publishers

በሎሬት ጸጋዬ ገ/መድህን ስም የተሰየመው የባህል ጥናት እና ምርመር ማዕከል በአምቦ ዩኒቨርሲቲ ተመረቀ።

ዩኒቨርሲቲው ያስገነባው ማዕከል በሃገሪቱ የሚገኙ የብሄር እና ብሄረሰቦች ባህል ላይ ጥናት ለማድረግ እና ለማስተማር ያቀደ ነው። በሎሬቱ ስም በተሰየመው በዚህ ማዕከል ውስጥ ቤተ-መጽሃፍት እና የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይገኛሉ።

የአለማየሁ ተፈራ ፖለቲካዊ ካርቱኖች

ወመዘክር፡ ከንጉሡ ዘመን እስከዛሬ

የአምቦ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ታደሰ ቀነዓ (ዶ/ር) ማዕከሉ የተቋቋመው ለሁለት ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል። "የመጀመሪያው አዲሱ ትውልድ ታላላቆቹን አውቆ እንዲዘክር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እንደ ሎሬት ጸጋዬ አይነት ትውልድ ለመፍጠር ነው" ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ከተለያዩ የሃገሪቱ ክልል እንደሚመጡ ያስታወሱት ፕሬዝደንቱ ተማሪዎች ባህላቸውን የሚያስተዋውቁበት እና የሚማማሩበት ማዕክል እንደሚሆንም ተናግረዋል።

የማዕከሉ ምረቃ ላይ የተገኙት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚንስቴር ሚንሰትር ዴኤታ የሆኑት ሳሙዔል ክፍሌ (ዶ/ር) በበኩላቸው "ከሎሬት ጸጋዬ በላይ ለፑሽኪን እውቅና የምትሰጥ ሃገር ውስጥ ነው ያለነው" ካሉ በኋላ ኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት ያላትን ሃብት ዘንግታ እና ምሁሮቿ የሚገባቸውን ክብር ተነፍገው ኖረናል ብለዋል።

ይህን መሰል ማዕከላት ማቋቋም የሃገርን አንድነት ከማጠናከር በተጨማሪ ክብር ለሚገባቸው ክብር መስጠት አርአያነት ያለው ተግባርም ነው ብለዋል።

1970 ላይ በአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንደተዋወቁ የሚናገሩት አርቲስት እና የሕግ ባለሙያው አበበ ባልቻ፤ ሎሬት ጸጋዬ በአራት ቋንቋዎች ድንቅ አድርጎ ይጽፍ የነበረ ሰው ነው ብለዋል።

"ጸጋዬ የአርት ሰው ነው። ታሪክም ይጽፋል። የሃገራችንን እና የአፍሪካን ታሪክ ለዓለም ያስተዋወቀ ሰው ነው።"

"ሌቱም አይነጋልኝ" የተባለላት የውቤ በረሃ ትዝታዎች

በብርሃን ታስሰው የማይገኙት ሴት ኮሜዲያን

ሎሬት ጸጋዬ ሲከፋው እና ቅር ሲለው አምቦ መምጣት ይወድ ነበር ያሉት አርቲስት እና የሕግ ባለሙያው አበበ ባልቻ፤ ዩኒቨርሲቲው የሚፈቅድ ከሆነ በቅጥር ግቢው ውስጥ የሎሬቱን ሃውልት ማቆም እንሻለን ብለዋል።

ከሎሬት ጸጋዬ ጋር የስጋ ዝምድና እንዳለው የሚናገረው አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ በበኩሉ ጸጋዬ የእኔ ዘመድ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ዘመድ ጭምር ነው ብሏል።ለሎሬት ጸጋዬ የመታሰቢያ ሃውልት በአምቦ ብቻ ሳይሆን በአዲስ አበባም ሊቆምላቸው ይገባል ብሏል አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ።

ሎሬት ጸጋዬ ምዕራብ ሸዋ አምቦ አካባቢ 1928 ዓ.ም. ነበር የተወለዱት። ለስነ-ጽሁፍ ፍላጎት ማሳየት የጀመሩት ደግሞ ገና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሳሉ እንደነበር ይነገራል።

ባሕልና ተፈጥሮን ያጣመረው ዞማ ቤተ መዘክር

በ16 ዓመታቸው ጄነራል ዊንጌት ትምህርት ቤትን ከተቀላቀሉ በኋላ በይበልጥ የስነ-ጽሁፍ ችሎታቸውን አዳብረዋል። 1959 ዓ.ም. ላይ ሕግ ለማጥናት ወደ አሜሪካ ቺካኮ ማቅናታቸውንም የታሪክ ድርሳናት ይጠቁማሉ።

ከአሜሪካ መልስ የብሔራዊ ቲያትር ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ