ላይቤሪያ ከ10 ምርጥ የቱሪስት መዳረሻዎች ዝርዝር ውስጥ ገባች

ሎንሊ ፕላኔት እንዳለው የላይቤሪያ ጥቅጥቅ ያለ ደን ለጎብኚዎች ጀባ የሚለው በርካታ ነገር አለው Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ሎንሊ ፕላኔት እንዳለው የላይቤሪያ ጥቅጥቅ ያለ ደን ለጎብኚዎች ጀባ የሚለው በርካታ ነገር አለው

ምናልባትም ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ ናቸው ብለው ከሚያስቧቸው አገራት ተርታ ላይቤሪያን ላያስቧት ይችላሉ፤ እውነታው ግን ከዚህ ይለያል ይላል ታዋቂው የጉዞ አማካሪ ሎንሊ ፕላኔት ኩባንያ። ላይቤሪያ ጎብኝተናት የምንደሰትባትና ላይቤሪያን ለመጎብኘት በመምረጣችን የማንፀፀትባት ናት ብሏል።

አማካሪ ኩባንያው ባወጣው ደረጃ መሠረት ላይቤሪያ ከሌሎች የዓለም አገራት ጋር ስትነጻጸር ሰባት አገራት ብቻ ይቀድሟታል። አገሪቱ ባላት የቱሪዝም ሃብት ደረጃ ስምንተኛ ላይ ተቀምጣለች።

ሎንሊ ፕላኔት ከላይቤሪያ በተጨማሪ ኢሰዋቲኒ (የቀድሞዋ ስዋዚላንድ) እና ሞሮኮንም ዝርዝሩ ውስጥ አካቷል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ መጽሐፍ ምን ይዟል?

የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው

ላሊበላ፡ የመፍትሔ ያለህ የሚለው ብሔራዊ ቅርስ

ለውጭ ጎብኝዎች ላይቤሪያ ምናልባትም የተወሰነ ምስጢራዊ ልትሆንባቸው ትችላለች፤ ነገር ግን በቦታው ያለው የቱሪዝም ሃብት የሚስጥሩን ቁልፍ ይፈታል ተብሏል።

በተለይ ሳፖ ብሔራዊ ፓርክ የሚገኙ ቺምንፓዚዎች፤ ዝሆንና ዝነኛው የላይቤሪያ ፒግሚ ሕይወትን በተፈጥሯዊ ሃብቶች ለማስደሰት የሚያስችሉ ናቸው ብሏል ኩባንያው። ውብ የባህር ዳርቻዎቿም የላይቤሪያ ሁነኛ የውበት መገለጫ ናቸው።

ሳፖ ብሔራዊ ፓርክ በምዕራብ አፍሪካ ሁለተኛው ግዙፍ የተፈጥሮ ጫካ ነው።

ሎንሊ ፕላኔት የሚጎበኙ ቦታዎችን መዘርዝር አዎንታዊ ለውጥ የሚያመጣ ከሆነ፤ እኤአ በ2016 በተፈጠረው የኢቦላ ወረርሽኝ ምክንያት ከውጭ አገር ጎብኝዎች ጋር የተለያየችው ላይቤሪያ እንደገና ለመገናኘት ሰፊ ዕድል ይፈጥርላታል።

ኢስዋትሊ የደቡብ የአፍሪካ ንፍቀ ክበብ ቀዳሚ የቱሪዝም መዳራሻ ናት ያለው ሎንሊ ፕላኔት፣ ሞሮኮ ደግሞ የሰሜኑን ክፍል የመቆጣጠር ዕድል አላት ብሏል።

ባለፉት ጥቂት ቀናት ላይቤሪያ ከአስሩ የቱሪዝም መዳረሻ ዝርዝር ውስጥ በመግባቷ ምክንያት መልካም የሚባል የቱሪስት ፍሰትን አስተናግዳለች። ከዚህም በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት ቻሪቲስ ኤይድ ፋውንዴሽን በተባለ ተቋም ላይቤሪያ የዓለማችን ምርጥ እንግዳ ተቀባይ አገር ተብላም ተመርጣለች።

እነዚህ ሁለት ክስተቶች ተደማምረው ለላይቤሪያ ቀጣይ ምጣኔ ሃብታዊ ጉዞ በጎ ነገርን ያመጣሉ ተብሎ ተስፋ ተደርጓል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ