የፖሊዮ ቫይረስን ከምድረ ገጽ ለማጥፋት የሚያስችል ትልቅ ርምጃ

በፓኪስታን የጤና ባለሙያ ለሕፃናት የፖሊዮ ክትባት ስትሰጥ Image copyright EPA Wires

ፖሊዮ ሦስት ዓይነት ዝርያ እንዳለው የዘርፉ ባለሙያዎች ይናገራሉ። ከእነዚህም መካከል ሁለተኛው ዝርያ መጥፋቱን ባለሙያዎች ይፋ አድርገዋል።

በሳይንስ ሦስት ዓይነት የፖሊዮ ቫይረሶች እንዳሉ የሚታወቅ ቢሆንም ሦስቱም በሚያስከትሏቸው የሕመም ምልክቶች እንዲሁም በሚያደርሱት የጤና ጉዳት ተመሳሳይ ናቸው።

ዓለማችን ዝርያ ሁለት ከተባለው የፖሊዮ አይነት ነፃ የተባለችው ከአራት ዓመት በፊት የነበረ ሲሆን፤ አሁን ደግሞ የዓለም ጤና ድርጅት ዝርያ ሦስትም ከምድራችን ላይ ጠፍቷል ሲል ተናግሯል።

ከሁለቱ ቀናት ግጭት ጋር በተያያዘ የሟቾች ቁጥር 27 ደረሰ

አሁንም ግን ዝርያ አንድ በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን በስፋት ተሰራጭቶ ይገኛል።

ፖሊዮ አብዛኛውን ጊዜ ዕድሜያቸው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ ሕፃናትን የሚያጠቃ ቫይረስ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ከ200 የፖሊዮ ተጠቂዎች አንዱ ወደ ማይቀለበስ የጤና ቀውስ ወይም ልምሻነት እንደሚያድግ ተናግሯል። በዚህም የመተንፈሻ አካል ጡንቻ የተጎዳ ከሆነ ደግሞ ሞት ሊከሰት እንደሚችል የድርጅቱ መረጃ ያመለክታል።

ይህ የልጅነት ልምሻ መድሃኒት ባይኖረውም በቀላሉ በክትባት መከላከል ይቻላል።

በሩዋንዳ ለነፍሰጡር እናቶች የሚሆን የስፖርት እንቅስቃሴ ተጀመረ

ከፖሊዮ ቫይረሶች መካከል አንዱ የሆነው ዝርያ ሁለት ከምድረ ገፅ መጥፋቱ የተነገረው ከአራት ዓመታት በፊት ሲሆን በሕንድ የመጨረሻው ታማሚ ከተገኘ 16 ዓመት ሆኖታል።

በሰሜናዊ ናይጄሪያ ዝርያ ሦስት የሆነው የፖሊዮ ቫይረስ ከተገኘ ሰባት ዓመት ሆኖታል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ፖሊዮን ለማጥፋት የሚሰራው ዓለም አቀፍ ኮሚሽን አባል ከሆነው የዓለም ጤና ድርጅት ጋር በጋራ በመሆን የዝርያ ሦስት መጥፋትን ሲከታተል ነበር።

የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ማትሺዲሶ ሞዪቲ እንዳሉት "የፖሊዩ ቫይረስ የሆነው ዝርያ ሦስት መጥፋት ዓለማችንን ከፖሊዮ ነፃ ለማድረግ የመሰረት ድንጋይ ነው፤ ነገር ግን ልንዘናጋ አይገባም" ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገራት ሕዝቦቻቸውን ለመከላከል እንዲያስችላቸው ክትባት መስጠቱን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ያሳሰቡት ኃላፊው፤ በየጊዜው ክትትል በማድረግ ፖሊዮ በሚከሰትበት ወቅት በፍጥነት ምላሽ መስጠት እንደሚገባ አሳስበዋል።

በባንግላዴሽ ተማሪዋን አቃጥለው የገደሉ 16 ግለሰቦች ሞት ተበየነባቸው

በአሁኑ ሰዓት ዝርያ አንድ የፖሊዮ አይነት በአፍጋኒስታንና በፓኪስታን ብቻ ተወስኖ እገኛል።

ይህ ዝርያ በናይጄሪያ ለመጨረሻ ጊዜ የታየው በ2016 (እአአ) ነበር።

"ይህ ሥራ ተጠናቀቀ የምንለው ዝርያ አንድ ከምድረ ገፅ ጠፍቶ ስናይ ነው፤ እንዲሁም ከክትባቱ ጋር በተያያዘ የሚያጋጥም ወረርሽኝንም ለመከላከል መስራት አለብን " ብለዋል።

በአሁኑ ሰዓት በ12 ሀገራት ይህን የፖሊዮ ቫይረስ ወረርሽኝን ለማጥፋት እየተሰራ ሲሆን ከእነዚህም ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ አንዷ ናት።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ