በኢትዮጵያ ተራራ ጫፍ ላይ የሚገኘው ባለ 900 ዓመቱ መንደር

በኢትዮጵያ ተራራ ጫፍ ላይ የሚገኘው ባለ 900 ዓመቱ መንደር

በአማራ ክልል ውስጥ በተራራ ጫፍ ላይ የሚገኘው የሾንኬ መንደር ለ900 ዓመታት ሰዎች ኖረውበታል።

የመንደሯ ነዋሪዎቹም "ከሚያብረቀርቁት ዘመናዊ ከተሞች" ተራራ ጫፍ ላይ በባህላዊ መንገድ በድንጋይ የተገነቡትን ቤቶቻቸውን እንደሚመርጡ ይናገራሉ።

ሃያ የሚደርስ ትውልድ በዚህ በተራራ ጨፍ ላይ በሚገኘው መንደር ውስጥ ኖረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት አሁን ግማሽ የሚደርሱት የመንደሩ ቤተሰቦች የእርሻ መሬት ፍለጋ በተራራው ላይ ያለውን መንደራቸውን ለቀው ሄደዋል።