በካሜሮን በመሬት መንሸራተት 37 ሰዎች ሞቱ

ሰዎችን ከአፈር ናዳ ውስጥ የማውጣት ጥረት Image copyright Reuters

በምእራባዊ ካሜሮን ባፎሳም በተሰኘች ከተማ ትናንት ከባድን ዝናብን ተከትሎ በደረሰ የመሬት መንሸራተት 37 ሰዎች ህይወታቸውን እንዳጡ ሮይተርስ ዘግቧል።

ከተማው የሚገኝበት ክልል አስተዳዳሪ ፎንካ አዋ ምንም እንኳ መንግሥት ማስጠንቀቂያ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ሰዎች አካባቢው ላይ ቤት ሰርተው መስፈራቸውን ተናግረዋል።

አልበርት ኬንጌ የተባለና ከአደጋው የተረፈ ሰው " ከባድ የአቧራ ተመለከትኩ ከዚያም ተራራው ሲደረመስ አየሁ" በማለት የመሬት መንሸራተቱ እንዴት እንደጀመረ ገልጿል።

ባለስልጣናት የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።

የአይኤሱ መሪ አቡ ባክር አልባግዳዲ እንዴት ተገደለ?

ቦይንግ ከተሳፋሪዎች ደህንነት ትርፉን አስቀድሟል ተባለ

የሠርጋቸው ቀን ምሽት ለትዳራቸው መፍረስ ምክንያት የሆነባቸው ሴቶች