የአየር ንብረት ለውጥ 52 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ለረሃብ አጋለጠ

አንድት ሴት ህፃን ይዛ እየተራመደች Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ኦክስፋም እንዳለው በአየር ንብረት ለውጡ ምክንያት በተከሰተው ድርቅ በአብዛኛው ሴቶችና ህፃናት የተጎዱ ሲሆን መቋቋማቸውና ማገገማቸው አጠያያቂ ነው

በአፍሪካ 18 አገራት በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት በተከሰተ ድርቅ ከ52 ሚሊየን በላይ ሰዎች ለረሃብ መዳረጋቸውን ዓለም አቀፉ ድርጅት ኦክስፋም አስታወቀ።

ድርጅቱ በተከሰተው ድርቅና ጎርፍ ሳቢያ አገራቱ በአጠቃላይ በዓመት 700 ሚሊየን ዶላር እያጡ እንደሆነ ግምቱን አስቀምጧል።

በመላው ዓለም ከ4 ሚሊየን በላይ ሰዎችን ያሳተፈው ሰላማዊ ሰልፍ

የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው

በደቡብ አፍሪካ የኦክስፋም ዳይሬክተር ኔሌ ኒያንግዋ "አስደንጋጭ" ባሉት በዚሁ የከፋ ድርቅ ሳቢያ ራሳቸውን ያጠፉ አርሶ አደሮች መኖራቸውን ሪፖርቶች አመልክተዋል።

ድርቁ ምስራቅ አፍሪካንና የአፍሪካ ቀንድ የሚገኙ አገራትንም እየተፈታተነ ነው።

ሪፖርቱ እንዳሚያሳየው በምዕራብ ኬንያ የሰብል ስብሰባው 25 በመቶ ቀንሷል፤ በሶማሊያ ደግሞ ማሽቆልቆሉ 60 በመቶ ይደርሳል። በተለያዩ የገጠር አካባቢዎች የእንስሳት እርባታና የወተት ምርት መቀነሱንም የድርጅቱ ሪፖርት ጠቁሟል።

"በቀጠናው ወደ ሰባት ሚሊየን የሚጠጉ ሰዎች ለአስከፊ ረሃብ ተጋልጠዋል" ሲሉ የኦክስፋም የአፍሪካ ቀንድ፣ ምስራቅ እና ምዕራብ አፍሪካ ዳይሬክተር ልይዲያ ዚጎሞ ተናግረዋል።

በሚቀጥለው ሳምንት በአካባቢ ጥበቃ ላይ በሚያተኩረውና በደቡብ አፍሪካ በሚካሄደው የአፍሪካ የሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ሚኒስትሮች የአፍሪካን የአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነትን ለማረጋገጥ አቋም መያዝ እንደሚገባቸው ኦክስፋም አሳስቧል።

የስብሰባው ዓላማም ይሄው ነው ተብሏል።

ድርጅቱ አክሎም የዓለም ሙቀትን ከ1.5 ሴልሽየስ በታች ለማድረስ በፓሪስ የተደረገውን ስምምነት ዓላማ መሠረት፤ በማደግ ላይ ባሉ አገራት የአየር ንብረት ለውጥን ለመታገል ለሚደረገው ጥረት በሚቀጥለው ዓመት 100 ቢሊየን ዶላር ለማሰባሰብ ስምምነት ላይ መደረሱ የሚታወስ ነው።

በዚህም መሠረት ሚኒስትሮቹ ከኢንዱስትሪ የሚወጡ የካርቦንዳይኦክሳይድ ልቀቶችን ለመቀነስ መስራት እንደሚገባቸው ማረጋጋጥ አለባቸው ብሏል ድርጅቱ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ