በቦሊቪያ ተቃዋሚዎች የከንቲባዋን ጸጉር አስገድደው ላጩ

ፓትሪሽያ አስር Image copyright EPA
አጭር የምስል መግለጫ ከንቲባዋ፤ በተቃዋሚዎቻቸው መሬት ላይ በባዶ እግራቸው ተጎትተው፣ ቀይ ቀለም ተደፍቶባቸው፣ ጸጉራቸው በግድ ተቆርቷል

ቦሊቪያ ውስጥ የምትገኘው ቪንቶ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ፓትሪሽያ አስር፤ በተቃዋሚዎቻቸው መሬት ላይ በባዶ እግራቸው ተጎትተው፣ ቀይ ቀለም ተደፍቶባቸው፣ ጸጉራቸው በግድ መቆረጡ ተሰማ።

የገዢ ፓርቲው 'ማስ ፓርቲ' አባል የሆኑት ከንቲባዋ፤ ከሰዓታት በኋላ ለፖሊስ ተላልፈው ተሰጥተዋል።

ባለፈው ወር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ያካሄደችው ቦሊቪያ፤ በመንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ግጭት እየተናጠች ሲሆን፤ እስካሁን ሦስት ሰዎች ሞተዋል።

ከቼጉቬራ ልጅ ጋር ሞተር ሳይክል መንዳት

የደቡብ ኮርያ ፖለቲከኞች ለምን ጸጉራቸውን በአደባባይ ይላጫሉ?

ተቃዋሚዎች ቪንቶ ከተማ ውስጥ የሚገኝ ድልድይ ዘግተው ሳለ፤ በከተማዋ አቅራቢያ ሁለት ተቃዋሚዎች በመንግሥት ደጋፊዎች እንደተጎዱ ወሬ ተናፍሶ ነበር። ይህን ተከትሎም ተቃዋሚዎቹ ከንቲባዋን ተጠያቂ ያደርጉ ጀመር።

ከንቲባዋን፤ ፕሬዘዳንት ኤቮ ሞራሌስን ደግፈዋል ብለው የኮነኑት ተቃዋሚዎች፤ "ገዳዮች፣ ነፍስ አጥፊዎች" እያሉ ይጮሁ ነበር። በዚህ መሀል ጭንብል ያጠለቁ ወንዶች ከንቲባዋን በባዶ እግር ወደ ድልድዩ ወስደዋል።

ከንቲባዋን አንበርክከው፣ ቀይ ቀለም ቀብተው፣ ጸጉሯቸው ከቆረጡ በኋላ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ እንዲፈርሙም አስገድደዋቸዋል።

ከሰዓታት በኋላ ለፖሊስ ተላልፈው የተሰጡት ከንቲባዋ፤ በፖሊሶች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።

ፈቲያ መሐመድ፡ ከዐረብ ሃገር ኑሮ ወደ ሚሊየነርነት

ቻይና ጌም በሚያዘወትሩ ታዳጊዎች ላይ ሰዓት እላፊ ጣለች

ምርጫ በተካሄደበት ዕለት፤ የድምጽ ቆጠራው ለ24 ሰዓት መቋረጡን ተከትሎ፤ ቦሊቪያ ውጥረት ውስጥ ናት።

የተቃዋሚው ካርሎስ ሜሳ ደጋፊዎች፤ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር ከ2006 ጀምሮ አገሪቱን የመሩት ፕሬዘዳንት ኤቮ ሞራሌስ ለቀጣይ አምስት ዓመታት ሥልጣን ላይ እንዲቆዩ ለማስቻል ምርጫው ይጭበረበራል ብለው ይሰጋሉ።

የአገሪቱ ፕሬዝዳንት በምርጫው የመጀመሪያው ዙር ከተቃዋሚው አስር በመቶ የሚበልጥ ድምጽ እንዳገኙ ተነግሯል። ሆኖም 'ኦርጋናይዜሽን ኦፍ አሜሪካን ስቴትስ' የተባለው የታዛቢ ቡድን ውጤቱን እየመረመረ ነው።

ተቃዋሚው ካርሎስ ሜሳ፤ ምርመራው ፖርቲያቸውን ያገለለ መሆኑን በመግለጽ ተቃውሞ አሰምተዋል።

ፕሬዝዳንቱ በበኩላቸው ተቃዋሚያቸውን መፈንቅለ መንግሥት ሞክረዋል ብለው ይከሳሉ። የሁለቱም ወገኖች ደጋፊዎች በተደጋጋሚ ግጭት ውስጥ እየገቡም ይገኛሉ።

ተያያዥ ርዕሶች