የአሜሪካ ምርጫ፡ ቢሊየነሩ ማይክል ብሉምበርግ ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ ነው

ማይክል ብሉምበርግ Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ ማይክል ብሉምበርግ

ቢሊየነሩ የንግድ ሰው ማይክል ብሉምበርግ የዴሞክራቲክ ፓርቲን በመወከል ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ለመቅረብ ራሳቸውን በእጩነት የማቅረብ ጠንካራ ፍላጎት እንዳላቸው ተገለጸ።

የቀድሞው የኒው ዮርክ ከተማ ከንቲባ የነበሩት የማክል ብሉምበርግ ቃል አቀባይ እንደተናገሩት፤ አሁን ካሉት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር በመፎካከር ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለመቅረብ እጩ የሆኑት ሰዎች አሸናፊ ሆነው ለመውጣት ባላቸው ብቃት ላይ ብሉምበርግ ስጋት እንዳላቸው አመልክተወል።

የ77 ዓመቱ ብሉምበርግ አላባማ ውስጥ የሚካሄደው የዕጩዎች ፉክክር ላይ ለመቅረብ የሚያስችላቸውን ማመልከቻ በዚህ ሳምንት ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በቀጣይ ዓመት በሚደረገው የአሜሪካ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመፎካከር በአጠቃላይ 17 ዕጩዎች ቀርበዋል።

የማርቲን ሉተር ኪንግ ስም ከመንገድ ላይ እንዲነሳ ተደረገ

ከንቲባው "ክቡርነትዎ" አትበሉኝ አሉ

የአየር ንብረት ለውጥ 52 ሚሊዮን አፍሪካውያንን ለረሃብ አጋለጠ

የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን፣ የማሳቹሴትስ ግዛት ምክር ቤት አባል ኤልዛቤት ዋረንና የቬርሞንት ግዛት ምክር ቤት አባሉ በርኒ ሳንድስ በምርጫ ፉክክሩ ላይ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ።

በቅርቡ በተሰበሰቡ የተወሰኑ የሕዝብ አስተያየት መለኪያዎች በተገኘ ውጤቶች መሰረት ኤልዛቤት ዋረንና በርኒ ሳንደርስ የዴሞክራቲክ ፓርቲን ፕሬዝዳንታዊ ዕጩነት ካገኙና ከወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጋር ከተፎካከሩ ትራምፕ አሸንፈው ለሁለተኛ ዙር ዋይት ሐውስ ውስጥ የመቆየት እድላቸው የሰፋ ይሆናል ተብሏል።

የማይክል ብሉምበርግ ቃል አቀባይ ጨምረው እንዳሉት፤ "ትራምፕ የሚሸነፉበትን መንገድ ለማመቻቸት ሥራችንን መጨረስ አለብን። ነገር ግን ብሉምበርግ የዴሞክራቲክ ፓርቲውን ወክለው ለመወዳደር የቀረቡት እጩዎች ብቃት አሳስቧቸዋል" ብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች