ኬኤፍሲ ምግብ ቤት ውስጥ ቀለበት አስረው የደቡብ አፍሪካዊያንን ቀልብ የሳቡት ጥንዶች

ኬኤፍሲ Image copyright Getty Images

ደቡብ አፍሪካ የሚገኝ ኬኤፍሲ ምግብ ቤት (ከዶሮ የሚዘጋጁ ምግቦችን የሚያቀርብ) ውስጥ ቀለበት ያሰሩት ጥንዶች የበርካቶችን ቀልብ ስበዋል።

ጥንዶቹ ዶሮ እየተመገቡ ሳለ፤ ወንዱ ተንበርክኮ "ታገቢኛለሽ ወይ?" ሲል ሴት ጓደኛውን ጠየቀ። "እዎ!" ብላም ቀለበት አሰሩ።

ኬኤፍሲም፤ "እኒህን ጥንዶች አፋልጉን" ሲል ጥንዶቹ ቀለበት ሲያስሩ የሚያሳይ ተንቀሳቃሽ ምስል በማኅበራዊ ሚዲያ የመገናኛ መድረክ ላይ ለቀቀ።

ትዳር ከባድ የጤና ችግሮችን ለመከላከል

ተንቀሳቃሽ ምስሉን 17ሺህ ሰዎች ከተጋሩት በኋላ፤ ጥንዶቹ በኸት ሄክተር እና ኖናሀላና እንደሆኑ ታወቀ። ተንቀሳቃሽ ምስሉን ያዩ ደቡብ አፍሪካዊያንም፤ ጥንዶቹ የተመኙት አይነት ሠርግ እንዲደግሱ ገንዘብ ማሰባሰብ ጀመሩ።

ዛካስ ባንቲዊኒ የተባለ ድምጻዊ ሠርጋቸው ላይ በነጻ ለመዝፈን ተስማምቷል። የጫጉላ ሽርሽር ወደሚያደርጉበት ሥፍራ በነጻ ለማድረስ ፍቃደኝነት ያሳዩም አልጠፉም።

ድራም የተባለ መጽሔት፤ የጥንዶቹን የፍቅር ታሪክ እንደሚዘግብ አሳውቋል። መጠጥና የምግብ ማብሰያ ቁሳቁሶችን ለማቅረብ ቃል የገቡም አሉ።

'ሰልፊ' ለመነሳት ሲሞክሩ የሰመጡት ሙሽሮች

ጥንዶቹ ቀለበት ሲያስሩ ቪድዮ የቀረጻቸው ካታካ ማሎቦላ የተባለ ግለሰብ ነው። ፌስቡክና ኢንስታግራም ላይ ምስሉን ከለቀቀ በኋላ በርካቶች ተጋርተውታል።

ጥንዶቹም ሊደግፏቸው የፈቀዱ ሰዎችን ባጠቃላይ አመስግነዋል። ጥንዶቹ ከስምንት ዓመት በፊት ጋብቻ መስርተው ነበር። ነገር ግን ሙሽራው በወቅቱ በገዛው ቀለበት ደስተኛ አልነበረም።

ስለዚህም ለባለቤቱ ሌላ ቀለበት ለመግዛት ወሰነ።

ቢዮንሴ በህንድ ለቱጃር ልጅ ሰርግ ዘፈነች

"ሥራ ስለሌለኝ ኖናሀላና የሚገባተን አይነት ቀለበት መግዛት አልቻልኩም" ሲል ተናግሯል።

በኸት ሄክተር መላው ደቡብ አፍሪካዊያንን አመስግኖም፤ "የፍቅር ታሪካችን በዚህ መጠን የብዙዎችን ልብ ይነካል ብለን አላሰብንም ነበር" ብሏል።