አውስትራሊያዊው ቦክሰኛ ከልምምድ በኋላ ህይወቱ አለፈ

ዲዋይት ሪቺ (ግራ) ከተጋጣሚው ቲም ታስይዙ ጋር ከሶስት ወራት በፊት። Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ ዲዋይት ሪቺ (ግራ) ከተጋጣሚው ቲም ታስይዙ ጋር ከሶስት ወራት በፊት።

አውስትራሊያዊው የ27 ዓመት ወጣት ቦክሰኛ ዲዋይት ሪቺ ከልምምድ በኋላ ህይወቱ አለፈ።

የሶስት ልጆች አባት የሆነው ቦክሰኛ በሜልቦርን ከተማ የቦክስ ልምምድ ሲያደርግ ነበር ተብሏል።

የቦክሰኛው ወኪል የዲዋይት ሪቺን ህልፈተ ህይወት ይፋ አድርጓል።

ለቦክሰኛው ሞት ቀጥተኛው ምክንያት ባይታወቅም ልምምድ ካደረገ በኋላ በጥቂት ጊዜ ውስጥ ህይወቱ ማለፉ ተነግሯል።

በልምምድ ወቅት ጉዳት ስለማጋጠሙም የተባለ ነገር የለም።

ከጥቂት ሳምንታት በፊት ታዋቂው አሜሪካዊው ቦክሰኛ ፓትሪክ ዴይ በውድድር ላይ ጉዳት አጋጥሞት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል።

ፓትሪክ ዴይ በውድድሩ ወቅት ጭንቅላቱ ላይ ጉዳት አጋጥሞት ለአራት ቀናት እራሱን ስቶ ቆይቶ ነበር ህይወቱ ያለፈው።

"እንደ ወኪሉ እና ጓደኛው የዲዋይት ሪቺ ሞት ዜናን መቀበል እጅግ ከባድ ነው" ሲሉ ወኪሉ ጄክ ኤሊያስ በፌስቡክ ገጹ ላይ አስፍሯል።

የአውስትራሊያዊው ቦክሰኛ ድንገተኛ ሞት በአውስትራሊያዊያን ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤን የፈጠረ ሲሆን፤ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በርካቶች ሃዘናቸውን እየተገለጹ ይገኛሉ።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ