ከንቲባ ታከለ ኡማ በስህተት ለወጣው የኤርትራ ካርታ ይቅርታ ጠየቁ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር ) Image copyright Addis Ababa city mayor

የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ በስህተት ለወጣው የአፍሪካ ካርታ ይቅርታ ጠይቀዋል።

ጥያቄንና ውዝግብን ያስነሳው ይህ ካርታ ብዙዎች በተለያዩ ማህበራዊ ድረ ገፆች የተጋሩት ሲሆን ኢትዮጵያንና ኤርትራን የሚለየው ድንበር በትክክል እንደማይታይና የኢትዮጵያ ግዛትም እስከ ቀይ ባህር ድረስ እንደሚዘረጋ የሚያሳይ ነው ተብሏል።

ሐሰተኛ ዜና ወይስ የተቀለበሰ ውሳኔ?

''አዲስ አበባ የሁላችንም ከተማ ናት'' ከንቲባ ታከለ ኡማ

ከንቲባ ታከለ ኡማ በትዊተር ገፃቸው ላይ ይቅርታን ጠይቀው መስተካከል ያለበት እንደሆነ አፅንኦት ሰጥተው አስፍረዋል።

"ኤርትራውያን ወንድሞቼንና እህቶቼን ይህንን ስህተት ስለጠቆማችሁን በጣም አመሰግናለሁ። እንዲህ ሳናውቅ ያደረግናቸው ስህተቶች ቶሎ መስተካከል ስላለባቸው እንዲወርዱ አድርገናል። ከጥቆማውም ተነስተን ሌሎች ስህተቶችንም አግኝተናል" ብለዋል

አየር መንገዶች "ከምድራችን ይልቅ ጥቅማቸውን ያስቀድማሉ"

ታከለ ኡማና የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ብራውዘርን አብረውት የተነሱት ፎቶ ከኋላቸው ያለው የአፍሪካ ካርታ የተሳሳተ መሆኑንና ማስተካከያ እንደሚገባም የኤርትራ ፕሬስ የተባለው በድረገፁ አስፍሮ ነበር።

ከተስተካከለ በኋላ የኤርትራ ፕሬስ ምስጋናውን በማህበራዊ ሚዲያ ገፁ አስፍሯል።