የብዙ ኢትዮጵያዊያንን ህይወት እየቀየረ ያለው የተፈጥሮ ጥበቃ ሥራ

ጥብቅ ደን

በሰሜናዊ ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ባለፉት አስር ዓመታት በሰው ሰራሽና ተፈጥሯዊ ምክንያት ተጎድተው የነበሩ አካባቢዎች በእጽዋት እየተሸፈኑ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ በቂ ውሃ እንዲኖር ከማድረግ ባለፈ የዱር እንስሳትም እንዲመለሱ አድርጓል፤ ንቦችንም ጨምሮ።

የቢቢሲው ጀስቲን ሮውላት ወደ ትግራይ ክልል በተጓዘበት ወቅት ብዙ አስገራሚ ነገሮችን እንደተመለከተ ይናገራል። የማይረሳው ነገር ግን የነደፉትን ንቦች እንደሆነ ገልጿል።

'' በወቅቱ ያልጠበቅኩትና አስደንጋጭ ነገር ነበር'' ብሏል ስለንቦቹ ሲያስረዳ።

በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ መሪነት የሚሰራው በዓለማችን እጅግ የተራቆቱ ከሚባሉት አንዱ የሆነውን አካባቢ መልሶ በደን የመሸፈን ስራ ትልቅ ራዕይ አንግቦ የተጀመረ እንደሆነ ጀስቲን ይገልጻል።

ወደ ጫካነት የተቀየረው ስታዲየም

ሳናውቀው እያለቁብን ያሉ ስድስት ነገሮች

መልሶ የማልማት ስራውን ከሚቆጣጠሩ የስነ ደን ባለሙያዎች መካከል አንዷ የሆነችው ሳራ ተወልደብርሀን፣ ጀስቲንን ይዘው ወደ ጥብቅ ደኑ ሄደች። ''ይህንን የመሰለ ትልቅ ፕሮጀክት በአግባቡ እንኳን በአጥር አለመከለሉ እያስገረመኝ ተከትለኳት'' ይላል ጀስቲን።

በሳራ መሪነትም ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚከፋፈሉ ችግኞች የሚዘጋጁበትን ቦታ ተመለከቱ። '' አካባቢው ደስ የሚልና ሰላማዊ ስሜትን ይፈጥራል። ወፎች ሲዘምሩ መስማት ደግሞ እጅግ ያስደስታል።''

'' በልጅነቴ ስለ ሰሜን ኢትዮጵያ እየሰማሁት ካደግኩት ታሪክ ጋር ሊጣጣምልኝ አልቻለም። እኤአ በ1980ዎቹ ውስጥ ተከስቶ የነበረው ረሃብ ስለዚህ አካባቢ የተለየ አስተሳሰብ እንዲኖረኝ ነበር ያደረገው።''

Image copyright Getty Images
አጭር የምስል መግለጫ በድርቁ ወቅት ምግብ በመፈለግ ላይ የነበረ ህጻን

በወቅቱ ለተከሰተው ድርቅ ብዙ ምክንያቶች ቢኖሩም መንግስት አካባቢዎቹን ችላ ማለቱ፣ ጦርነት እና የደን ጭፍጨፋ ተጠቃሽ ናቸው።

በምድራችን እጅግ ከፍተኛ ከሚባሉ የደን ጭፍጨፋዎች ከተደረገባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ ቀዳሚውን ስፍራ ትይዛለች። ያለዛፎች ደግሞ ለም የሆነውን የአፈር ክፍል መጠበቅ ከባድ ነው።

ነገር ግን ሳራ እና ጓደኞቿ እያከናወኑት ባለው የተፈጥሮ ጥበቃና መልሶ የማልማት ስራ አካባቢው አረንጓዴና እጅግ ማራኪ ቦታ ሆኗል። የስራቸውን ውጤት በቀላሉ መመልከት ይቻላል።

'' ተፈጥሮ ራሷን መልሳ ማዳን ትችላለች'' በማለት ሳራ እንደነገረችው ጀስቲን ያስታውሳል።

የማዉ ጫካን ለማዳን 60 ሺ ኬንያውያን ከመኖሪያቸው ተባረሩ

ደኑን ወደነበረበት መመለስ ለአካባቢው አዲስ ነገር ነው። ነገር ግን አካባቢው ነዋሪዎች ፕሮጀክቱን ለመደገፍ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይተዋል። ''ከብቶች ለግጦሽ እንዳይጠቀሙትና ዛፎች እንዳይቆረጡ በትብብር ይሰራሉ'' ስትል ስለአካባቢው ነዋሪዎች ሳራ ታስረዳለች።

በማህበረሰቡ ጋር በትብብር የሚሰራው አካባቢውን መልሶ በደን የመሸፈን ስራ፣ ውጤታማ በመሆኑ ምክንያት በትግራይ ክልል 15 ስኩዌር ኪሎ ሜትር የሚሸፍን ቦታ ሙሉ በሙሉ በደን ተሸፍኗል።

በአንዳንድ አካባቢዎች ደግሞ ለብዙ ዓመታት ደርቀው የነበሩ ምንጮች ጭምር ተመልሰው ውሃ ማፍለቅ ጀምረዋል። ወንዞችም ቢሆን ዓመቱን ሙሉ መፍሰስ ከጀመሩ ሰነባብተዋል።

በቅርብ የሚገኙ ገበሬዎች ምርት በእጅጉ ጨምሯል።

'' በደኑ ውስጥ ስንዘዋወር አንድ ነገር ቀልቤን ገዛው። አረንጓዴ ቀለም የተቀቡ የንብ ቀፎዎች በብዛት ይታያሉ፤ በቅርበት ለመመልከት ተጠጋን።''

Image copyright Getty Images

ምንም እንኳን ሳራ በጥንቃቄ እንድንቀሳቀስ ብትነግረኝም ብዙም አላሳሰበኝም ነበር የሚለው ጀስቲን በድንገት ግን ያላሰበው ነገር አጋጥሞታል።

'' ወዲያውኑ በእጄ አካባቢ በጣም የሚያቃጥል ስሜት ወረረኝ። ልብሴን ሰብስቤ ስመለከት ሁለት ንቦች ወደታች ሲወርዱ አየኋቸው። ሁለቱም ንቦች ከነደፉኝ አካባቢ አነስተኛ ደም ተቋጥሮ ይታይ ነበር።''

''እርዱኝ!! ንቦቹ ነደፉኝ!! ብዬ ጮህኩኝ

ሳራ ወደ ጀስቲን ስትሄድ እሷም በንቦች ተነደፈች።

የምድራችን ትልቋ ንብ ተገኘች

ሜድ ኢን ቻይና- የሀገር ባህል አልባሳቶቻችን

ወዲያውም አካባቢያችን በሙሉ በንቦች ተከበበ። አስደንጋጭም አስቂኝም አጋጣሚ ነበር። ሁለታችንም ከንቦቹ ለማምለጥ እርስ በእርስ እየተገጫጨንና እየተረጋገጥን በሩጫ ለማምለጥ ሞከርን።''

''ነገር ግን አጄን፣ ጆሮዬን፣ ከንፈሬን እና ጀርባዬን ንቦቹ ነድፈውኝ ነበር።''

'' በሩጫ በቅርብ ወደነበረው ቤት ገባን። ሳራም በሩን ከዘጋች በኋላ በድንጋጤ ተያየን። ትንሽ ትንፋሻችንን ከሰበሰብን በኋላ አብረን መሳቅ ጀመርን።''

'' እንደውም የሆነ ነገር አስታወስኩኝ አለች ሳራ። ጓደኛዬ ከጫካው ማር ይሰበስባል እኮ፤ ለምን አንድ ገንቦ አልሰጥህም? ብላ ወደ ውስጥ ገባች።''

''በጣም ጣፋጭና ተፈጥሯዊ ማር ነበር። ወደድኩት።''

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ