የዓለም መፀዳጃ ቤት ቀን፡ መፀደጃ ቤት ተጠቅሞ መታጠብ ወይስ መጥረግ?

እንዲህ ያሉ የመፀዳጃ ቤት መታጠቢያዎች በተለይም በአንዳንድ አገሮች የተለመዱ ናቸው Image copyright Getty Images

መፀዳጃ ቤት ተጠቅሞ መጥረግ ወይስ መታጠብ የሚለው ጉዳይ ከባህልና ከታሪክ አንፃር አሁንም አለምን በሁለት ጎራ እንደከፈለ ነው።

በምእራቡ ዓለም መፀዳጃ ቤት ተጠቅሞ ከመታጠብ ይልቅ መጥረግ የተለመደ ነው። በተቃራኒው በአረቡና በሙስሊሙ አለም መታጠብ የሚመረጥ ነው።

የመፀዳጃ ቤት ባለ እጀታ መታጠቢያዎች በተለይም በአንዳንድ አገሮች የተለመዱ ናቸው። ይህም በእነዚህ አገራት ወሃ ይዞ ወደ መፀዳጃ ቤት የመሄድን የብዙ ዘመን ልምድ ታሪክ እያደረገ ያለ ይመስላል።

ምንም እንኳ ዘመናዊ ሶፍቶች እጅግ ለስላሳ ቢሆኑም ከውሃ የበለጠ ለስላሳ አለመሆናቸው ግን አያከራክርም።

ቢሆንም ግን አሁንም እንግሊዝና አሜሪካን ጨምሮ አብዛኛው የምእራቡ አለም ሶፍት መጠቀምን ይመርጣል። የእነዚህ ሁለት አገራት የመፀዳጃ ቤት አሰራር በአለም አቀፍ ደረጃ ሰፊ ተፅእኖ እንዳለው ይነገራል።

በግጭት አዙሪት ውስጥ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች

መፀዳጃ ቤት ተጠቅሞ ሶፍት መጠቀም ወይስ መታጠብ? የሚለው እንደ አውስትራሊያው ዙል ኦስማንን የመሰሉ ሰዎችን የሚስብ ክርክር ነው። ባህላዊና ታሪካዊ ሁነቶች የመፀዳጃ ቤት አጠቃቀም ላይ ያላቸውን ተፅኖ አጥንተዋል።

የሳቸው ጥናት እንደሚያሳየው የተወሰኑ የእስልምና እምነት ተከታይ አውስትራሊያዊያን ሁለቱንም ይጠቀማሉ።

ህንዳዊቷ አስታ ጋርግ እንደምትለው ምንም እንኳ የተወሰኑ ህንዳዊያን ሶፍት መጠቀም ቢለምዱም አብዛኞቹ ግን ውሃ ይመርጣሉ። ሁሌም ወደ አሜሪካ ስታቀና የጓደኞቿ ወይም የዘመዶቿ ቤት መፀዳጃ ቤት ባለ እጀታ መታጠቢያ እንደሚኖረው ካልሆነም ልትጠቀምበት የምትችል ትንሽ ፕላስቲክ ጠርሙስ እንደሚኖር ትጠብቃለች።

ውሃ ይበልጥ ያፀዳል፣ ሶፍት ተጨማሪ ወጪ ያስወጣል እንዲሁም የመፀዳጃ ቤት ቱቦ ሊዘጋ ይችላል የሚሉ ምክንያቶችን በማስቀመጥ ወሃ መጠቀም የተሻለ ነው የሚል አስተያየት የሚሰነዝሩም ብዙዎች ናቸው።

Image copyright Getty Images

ተቀምጦ ወይስ ቁጢጥ ብሎ መፀዳዳት ጤናማ ነው? የሚለውም ሌላው ጉዳይ ነው ስለ መፀዳጃ ቤት አጠቃቀም ሲነሳ። በዚህ ረገድም ልዩነቶች አሉ።

ዛሬም ሁለት ሶስተኛ የሚሆነው የአለም ህዝብ የሚፀዳዳው ቁጢጥ በማለት ነው።

ከአካላዊ አቀማመጥ አንፃር ቁጢጥ ማለት በቀላሉ ለመፀዳዳት ትክክለኛው መንገድ ነው የሚሉም አሉ።

ዘመናዊውን የመፀዳጃ መቀመጫ የፈጠረው ሰዓት ሠሪ

Image copyright Getty Images

እነዚህ አስተያየት ሰጭዎች ምንም እንኳ ጤናማው የመፀዳዳት አቀማመጥ ቁጢጥ ማለት ቢሆንም ይህ አዎንታዊ ጎን ብዙም ትኩረት አይሰጠውም ይላሉ።

በሌላ በኩል አሜሪካዊያን ተቀምጦ መፀዳዳትን ተመቻችቶ የመቀመጥ ብቻም ሳይሆን እያነበቡ የሚዝናኑበት እንዲሆን በማድረግም አዘምነውታል።

ቁጢጥ ብሎ መፀዳዳት የብዙዎች ምርጫ በሆነበት ቻይና እናቶች "መፀዳጃ ቤት ሆናችሁ አታንብቡ ኪንታሮት ይይዛችኋል" ሲሉ ልጆቻቸውን ይመክራሉ።

የ7 ዓመቷ ህፃን መፀዳጃ ቤት አልሰራልኝም ስትል አባቷን ከሰሰች

ተያያዥ ርዕሶች