ጉግል የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ላይ እገዳ ሊጥል ነው

የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎች

ጉግል በመላ ዓለም የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ሊያግድ እንደሆነ አስታወቀ።

ይህ እገዳ በምርጫ ቅስቀሳ ወቅት ዩቲውብና ጉግል ሰርችን መራጭ ለማግኘት መጠቀም እንዳይቻል ያደርጋል ተብሏል።

ቢሆንም ግን አሁንም የምርጫ ቅስቀሳ እንቅስቃሴዎች ጉግልን ተጠቅመው የመራጭ እድሜ፣ፆታና አድራሻን ለማወቅ ይችላሉ።

ጉግል በመላ ዓለም ሊተገብረው ያቀደው ይህ እገዳ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ እንግሊዝ ውስጥ ይጀመራል ተብሏል።

የፖለቲካ ማስታወቂያዎችን ማገድ ብቻም ሳይሆን አሳሳች መረጃ በሚይዙ ሌሎች ማስታወቂያዎች ላይም እርምጃ እንደሚወስድ አስታውቋል ጉግል።

ይህ እርምጃ ጉግልን ቀደም ሲል የፖለቲካ እጩዎች ወይም የምርጫ ቅስቀሳ ማስታወቂያዎች መረጃን እንደማያጣራ ካስታወቀው ፌስቡክ ጋር ግጭት ውስጥ ሊከትታቸው ይችላል ተብሎም ተሰግቷል።

የጉግል ዘርፍ ማናገጀር የሆኑት ስኮት ስፔንሰር ሰፊ የፖለቲካ ውይይት የዴሞክራሲ ወሳኝ ክፍል ስለሆነ ማንም እንደፈለገ የፖለቲካ ሃሳቦችን፣ ተቃራኒ ሃሳቦችን ሊያደላድል፤ እንዲሁም ሊመራና ሊቆጣጠር አይገባም ብለዋል።

"በቀጣይ እርምጃቸው የምንወስድባቸው የፖለቲካ ማስታወቂያዎች ምንም እንኳ ውስን ቢሆኑም እንቀጥልበታለን"ብለዋል

ስለጉግል የማያውቋቸው 10 እውነታዎች

«ፌስቡክና ትዊተር ብትጠነቀቁ ይሻላል» ትራምፕ

ሁዋዌ አንድሮይድን እንዳይጠቀም ገደብ ተጣለበት