በዓለም ላይ ሔሮይን ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ያለው በሲሽልስ ነው

ሲሸልስ Image copyright Getty Images

ምድረ ገነትነቷን ብዙዎች የሚመሰክሩላት ሲሽልስ በአደንዣዥ እፅ ወረርሽን ክፉኛ እየተሰቃየች እንደሆነ መረጃዎች ያመለክታሉ። ትላልቅ የዘንባባ ዛፎች ጥላ፣ ነጭ አሸዋማ የባህር ዳርቻዎች ውበት ወደ ሆኗት ሲሽልስ በየዓመቱ 360 ሺህ ቱሪስቶች ይጎርፋሉ።

ነገር ግን ከሲሽልስ የግል ደሴቶች፣ ሪዞርቶችና ምርጥ ምርጥ ሆቴሎች ጀርባ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝቧን የአደንዛዥ እፅ ሱሰኛ ባደረገ ወረርሽኝ የምትመሳቀል አገርን ያስተውላሉ።

ከሲሽልስ አጠቃላይ 94 ሺህ ሕዝብ ከአምስት እስከ ስድስት ሺህ የሚደርሰው በአደንዣዥ እፅ ሱስ የተያዘ መሆኑን የአገሪቱ መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን መረጃ ያሳያል።

ሲሽልስ በዓለም አቀፍ ደረጃም ከፍተኛ የሄሮይ ሱስ የተመዘገበባት አገር ለመሆኗ መረጃዎች አሉ።

የ34 ዓመቱ ጀድ ሊስፐራንስ ካናቢስ መጠቀም የጀመረው የ20 ዓመት ወጣት ሳለ ነበር። ከዚያ ግን በቀን ሁለት ሶስት ጊዜ ሄሮይን መጠቀም ጀመረ። ሱሱን ለመሙላት ከአያቱ ገንዘብ ይሰርቅም እንደነበር ያስታውሳል።

ከ115 ደሴቶች የተሰራችው ሲሽልስ ድንበሯ በዚህም በዛም ክፍት ነው። ሄሮይን ወደ ሲሽልስ የሚደርሰው ከማእከላዊ እስያ በተለይም ከአፍጋኒስታን ተነስቶ በምስራቅ አፍሪካ በማለፍ ረዥም ርቀት አቋርጦ ነው።

በአደንዣዥ እፅ ሱስ የተያዙ ሰዎች በርካታ በመሆናቸው ጉዳዩን በወንጀል ከማየት ይልቅ እንደ በሽታ አይቶ ማከምን ነው የሲሽልስ ባለስልጣናት መፍትሄ ያሉት።

በዚህም መሰረት የሄሮይን ተጠቃሚዎች ለመታከም ሁለት አማራጮች ያሏቸው ሲሆን የህክምናም የስነልቦናም ድጋፍ ማግኘት ይችላሉ። በአሁኑ ወቅት ሁለት ሺህ የሚሆኑ ሰዎች የህክምና አገልግሎቱን ለማግኘት ተመዝግበዋል።

ሁሌም ጠዋት ጠዋት ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ ሆነው የሚገለግሉ አውቶቢሶች ደጃፍ ላይ ተካሚዎች ይሰለፋሉ። ነርስና የስነልቦና ባለሙያዎች በማገገም ላይ ላሉ የአደንዛዥ እፅ ሱሰኞች ተገቢ ያሉትን እና እንዲያገግሙ የሚረዳቸውን ሜታዶን የተሰኘ መድሃኒት ይሰጧቸዋል።

Image copyright Getty Images

ብዙዎች እንደሚሉት በሄሮይን ሱስ ወረርሽኝ ብዙ የሲሽልስ ጎጆዎች ተናግተዋል።

በአገሪቱ የሱስ ማገገም ትልልቅ ፕሮግራሞች መዘርጋታቸውን ተከትሎ የሄሮይን ዋጋ እየቀነሰ እንዳለም መረጃዎች አሉ።

ላይቤሪያ የጦርና የኢኮኖሚ ወንጀሎች ፍርድ ቤት ልታቋቋም ነው

ሲሪላንካ የሞት ቅጣትን ለማስፈፀም ሁለት አናቂዎች ቀጠረች

ተያያዥ ርዕሶች