ፓኪስታን፡ ሴቶችን የማያሳትፈው በሴቶች ላይ የሚመክረው ስብሰባ ቁጣ ቀሰቀሰ

የፓኪስታን ሴቶች በተቃውሞ ላይ Image copyright Getty Images

'አርትስ ካውንስል' የተባለው የፓኪስታን ማኅበራዊ ተቋም ምንም አይነት ሴቶችን ያላሳተፈ በሴቶች መብትና ተሳትፎ ላይ ያተኮረ ውይይት ለማድረግ በማሰቡ ከፍተኛ ውግዘት እየደረሰበት ነው።

ካራቺ በተባለችው ከተማ ሊካሄድ የነበረው ውይይት፤ በማኅበራዊ ሚዲያዎች በደረሰበት ከፍተኛ ጫና ምክንያት አዘጋጆቹ የውይይቱን ርእስ እንዲቀይሩ አስገድዷቸዋል።

ፈቲያ መሐመድ፡ ከዐረብ ሃገር ኑሮ ወደ ሚሊየነርነት

እርጉዟ የሰደድ እሳት ተከላካይ

አዘጋጆቹ በተለያዩ ዘርፎች ያሉ ውሳኔ ሰጪ ወንዶች ስለ ሴቶች ምን ያስባሉ? የሚለውን ለማወቅ ነው ውይይቱ ላይ ሴቶች ያልጋበዝነው ቢሉም የፓኪስታን የሴቶች መብት ተሟጋቾችና የማኅበረሰብ አንቂዎች ጉዳዩን እንደ ንቀት እንቆጥረዋለን ብለዋል።

ወንዶች በብዛት ሁሉንም ነገር በሚወስኑባት ፓኪስታን፤ ሴቶችን ያላሳተፈው ውይይት በአገሪቱ ላለው የወንዶች የበላይነት በቂ ማሳያ ነው ተብሏል።

በውይይቱ ከሚሳተፉ ባለሙያዎች መካከል ብቸኛዋ ሴት የነበረችው ኡምዛ አል ካሪም ስሟ መጨረሻ ላይ መጠቀሱንም ብዙዎች አልወደዱትም።

ከተለያዩ ዘርፎች የተወጣጡ ናቸው የተባሉት ወንድ ተሳታፊዎችም በሴቶች ስም የራሳቸውን አጀንዳ ለማራማድ በመስማማታቸው ሊያፍሩ ይገባል በሚል በማኅበራዊ ሚዲያዎች ከፍተኛ ተቃውሞ ገጥሟቸዋል።

አንድ ፓኪስታናዊ በትዊተር ገጹ ላይ ባሰፈረው መልእክት ''ለሴቶች እኩልነት እሠራለው የሚሉ ወንዶች በዚህ ውይይት ላይ በመሳተፋቸው ሊያፍሩ ይገባል'' ብሏል።

ብቸኛዋ የውይይቱ ሴት ተሳታፊና የመድረክ መሪ ኡምዛ አል ካሪም በበኩሏ፤ ''የውይይቱ አላማ በትልልቅ የመገናኛ ብዙሀን የሚገኙ ኃላፊዎችና ሌሎች ውሳኔ ሰጪ ወንዶች ስለሴቶች መብትና እኩልነት ያላቸውን ግንዛቤ ለመረዳት ነበር'' ብላለች።

''የእነሱን አስተያየት ማወቅ የፈለግነው በተለያዩ ማኅበራዊ ኃላፊነቶች ላይ ስለሚገኙ የሰዎችን ሃሳብ መቀየር ስለሚችሉ ነው።''

በጃፓን ሴት ሠራተኞች መነጽር እንዳያደርጉ መከልከላቸው ጥያቄ አስነሳ

በውይይቱ ከሚሳተፉ ወንዶች መካከል አንዱ የሆነው የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ጂብራን ናሲር እንድሳተፍ የተጠራሁበት ውይይት ዋና ርዕሰ ጉዳይ አሳሳች ነበር ብሏል።

''በደረሰኝ መረጃ መሠረት ወንዶች ስለሴቶች ያላቸውን የተሳሳተ አመለካከት እንዴት መቀየር ይችላሉ? በሚለው ርዕስ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ነበር የማውቀው'' በማለት ስህተት እንደተፈጠረ ለማስረዳት ሞክሯል።