ለአንድ አመት ያህል ሳይበላሽ የሚቆየው አዲሱ አፕል በአሜሪካ በገበያ ላይ ዋለ

አፕል Image copyright PVM

በአሜሪካ በአይነቱ አዲስ የሆነ የአፕል ዝርያ ይፋ ተደርጓል፤ ባሳለፍነው እሁድም ለገበያ ውሏል።

ፍሪጅ ውስጥ ለአንድ አመት ያህል ቢቆይ የማይበላሽ ሲሆን፤ ይህንንም ዝርያ ለማግኘት ሁለት አስርታት ፈጅቷል።

ኮስሚክ ክሪስፕ የሚል ስያሜ የተሰጠው ይሄ አፕል በዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርስቲ ከሃያ ሁለት አመታት በፊት ተመርቶ የነበረው ሃኒክሪስፕ ጋር የተዳቀለ ነው ነው ተብሏል።

ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው

ጃፓን ያለ መሬትና ያለ አርሶ አደሮች የፈጠረችው የግብርና አብዮት

በዋሽንግተን አካባቢ የሚገኙ አርሶ አደሮች በቀጣዩ አስር አመታትም አፕሉን እንዲያመርቱ ብቸኛ መብት ተሰጥቷቸዋል።

ከሌላው አፕል ጋር ሲነፃፀር ትንሽ ጠንከር ያለ ሲሆን፤ ጣፋጭ እንዲሁም ፈሳሹም በርከት ያለ እንደሆነ ይህንን ዝርያ የማምረቱን ስራ በዋነኝነት የያዘው የዋሽንግተን ስቴት ዩኒቨርስቲ አንደኛዋ መሪ ኬት ኤቫንስ ተናግረዋል።

የዋግ ኽምራ አርሶ አደሮች ለከፋ ችግር ተጋልጠናል እያሉ ነው

አፕሉ እንደሌሎች ፍሬዎች በቀላሉ የማይበላሽ ሲሆን በማቀዝቀዣ (ፍሪጅ ) ውስጥ ከ10-12 ወራት ቢቀመጥም ምንም አይነት ለውጥ እንደማያመጣ አስረድተዋል።

እስካሁን ባለው ከአስራ ሁለት ሚሊዮን በላይ ኮስሚክ ክሪስፕ የአፕል ዛፎች የተተከሉ ሲሆን ያለው የፈቃድ ሁኔታም ከዋሽንግተን በስተቀር በሌሎች አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች እንዳያበቅሉ ይከለክላቸዋል።

የአፕሉ የመጀመሪያ ስያሜ ደብልዩ ኤ38 (WA38) የሚል ቢሆንም በፍሬው ላይ የታዩት ጠቆር ያሉ ነጠብጣቦች ከምሽት ሰማይ ጋር በመመሳሰሉ ኮስሚክ ክሪስፕ የሚል ሆኗል።

በአሜሪካ ከሙዝ በመቀጠል አፕል ትልቅ ሽያጭ ያለው ፍሬ ነው።

ይህንን አፕልም ወደ ገበያ ለማውጣት አስር ሚሊዮን ዶላር ያህል ፈጅቷል ተብሏል።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ