ሮበርት ሙጋቤ በባንካቸው ውስጥ ያልተናዘዙት አስር ሚሊዮን ዶላር ተገኘ

ሮበርት ሙጋቤ Image copyright DESMOND KWANDE

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ አስር ሚሊዮን ዶላር እንዲሁም ሌሎች ንብረቶችም በመዲናዋ ሐራሬ ትተው ማለፋቸውን የሃገሪቱ የመንግሥት ጋዜጣ 'ሔራልድ' ዘግቧል።

ባለፈው ዓመት መስከረም በዘጠና አምስት ዓመታቸው ያረፉት ሙጋቤ ለገንዘቡም ሆነ ለቀሪው ንብረታቸው ወራሽ ማን እንደሆነ ኑዛዜ ባለማስቀመጣቸው የመንግሥት ኃላፊዎች በጉዳዩ ላይ ጣልቃ እንዲገቡ ሆኗል።

ይህንን ጉዳይ ለመወሰን ስብሰባ ተቀምጠው ነበር።

ሮበርት ሙጋቤ የሞቱት "በካንሰር" ነው ተባለ

ኢኮኖሚያዊ ተቃውሞና ያስከተለው ውጤት

የቀድሞው ፕሬዚዳንት ልጅ ቦና ቺኮዎሬ በጥቅምት ወር ላይ ለከፍተኛው ፍርድ ቤት በፃፈችው ደብዳቤ አስር ሚሊዮን ዶላር በሃገሪቱ ባንክ፣ በሌሎች ገጠራማ ቦታዎች ካሏቸው ቤቶች በተጨማሪ ደግሞ አራት ቤቶች በሐራሬ እንዳላቸውም መጥቀሷን ሔራልድ ልጃቸውን ጠቅሶ ዘግቧል።

አስር መኪኖችም እንዳላቸው ጋዜጣው ጨምሮ አትቷል።

ጃፓኖች ከሰውና ከእንስሳት የተዳቀሉ የሰው አካላትን ለመፍጠር ሙከራ ላይ ናቸው

ዚምባብዌ ነፃ ከወጣችበት ጀምሮ ከሦስት አስርት ዓመታት በላይ ሃገሪቱን የመሩት ሙጋቤ ከስልጣን የተነሱት ከሁለት ዓመታት በፊት ነው።

ሙጋቤ አራት ልጆችም ትተው ነው ይህችን ዓለም የተሰናበቱት። በዚምባብዌ ህግ መሰረት ባለቤታቸው እንዲሁም ልጆቻቸው ሃብታቸውን የሚወርሱ ይሆናል።