ፈጣን ለውጥና ጭቆና በሳኡዲ አረቢያ

የሳኡዲ ሴቶች እግር ኳስ ሲመለከቱ

በሪያድ ዓለማቀፍ ስታዲየም የብራዚልና አርጀንቲና ብሄራዊ ቡድኖች ግጥሚያቸውን ሲያደርጉ አንድ ያልተለመደ ነገር ተስተዋለ። የሳኡዲ ሴቶች ፊታቸውና እና ጸጉራቸውን የሚሸፍነውን ሂጃብ አውልቀው እያውለበለቡ ደስታቸውን ሲገልጹ ታይተዋል።

አይደለም ሳይሸፋፈኑ መውጣት፣ ሴቶች ያለወንዶች አጃቢነት መንቀሳቀስ በማይችሉባት ሃገር እንዲህ አይነቱን ነገር መመለከት እንግዳ ሊመስል ይችላል።

ሳዑዲ ያልተጋቡ ጥንዶች ሆቴል እንዲከራዩ ፈቀደች

ሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ያለ ጠባቂ እንዲጓዙ ፈቀደች

የአሁኗ ሪያድ፣ አሁን ካለው ዘመናዊ አስተሳሰብ ጋር ለመቀራረብና የሌሎች ሃገራት ዜጎችን ለመሳብ በከፍተኛ ለውጥ ውስጥ ትገኛለች።

ከዚህ በፊት ማንኛውም ሰው ወጣ ብዬ አንዳንድ ነገሮች ልግዛ ቢል እንኳን የጸሎት ሰአት ሲደርስ የሱቆች በር መዘጋት ይጀምራሉ። የሱቆቹ ሰራተኞች ሃይማኖታዊ ፖሊሶችን በጣም ነው የሚፈሩት፤ በጸሎት ሰአት ሲነግድ የተገኘ የማያዳግም ርምጃ ይወሰድበታል።

የሳኡዲ ወጣቶችም ቢሆኑ እንደልባቸው እዚም እዚያም ተንቀሳቅሰው ነገሮችን ማከናወን አይችሉም ነበር።

ያቺኛዋ ሪያድ አሁን የለችም። በእጅጉ እየተቀየረችም ትገኛለች።

ለዜጎች መተንፈሻ የሚሆኑ የህዝብ መዝናኛዎች እዚም እዚያም የሚታዩ ሲሆን ሃይማኖታዊ ፖሊሶችም ሙሉ በሙሉ እንዲጠፉ ተደርገዋል።

ስሟ እንዲጠቀስ ያልፈለገች አንዲት ወጣት ለቢቢሲ እንደገለጸችው ሴቶች በሪያድ ጎዳናዎች ላይ መኪና እንዲያሽከረክሩ መፈቀዱ ለብዙ ነገሮች በሩን ከፍቷል። ምንም እንኳን እሷ ገና የመንጃ ፈቃዷን ባታገኝም ብዙ ሴቶች መኪና ሲያሽከረክሩ መመልከት እንደ ተአምር እንደሆነ ትገልጻለች።

ሌላው ቀርቶ ሴት ጓደኞቿ የራሳቸውን ቤት ተከራይተው መኖር መጀመራቸው ከጥቂት ዓመታት በፊት የማይታሰብ እንደነበር ታስታውሳለች።

በአሁኑ ሰአት በመላው ሪያድ ለሁለት ወራት የሚቆይ የአደባባይ መዝናኛ ድግስ የተዘጋጀ ሲሆን ክፍት ሲኒማዎች፣ ሰርከስና የሙዚቃ ኮንሰርቶችንም ጭምር ያካተተ እንደሆነ ተገልጿል።

በአስርታት የሚቆጠሩ ምግብ ቤቶች ውስጥ ሴቶችና ወንዶች ያለምንም ገደብ እንደልባቸው ሲዝናኑ ይስተዋላል።

መገደል፣ መደፈር፣ መዘረፍ ማብቂያ የሌለው የኢትዮጵያውያን የስደት ጉዞ

በቅርቡ ደግሞ የሳዑዲ አረቢያ ሴቶች ያለ ወንዶች ጥበቃና ፈቃድ ፓስፖርት እንዲያወጡና ከአገር ውጭ እንዲጓዙ መፍቀዷ የሚታወስ ነው።

እስካሁን ድረስ የሳዑዲ ሴቶች ፓስፖርት ለማግኘትና ወደ ሌላ አገር ጉዞ ለማድረግ ከትዳር አጋራቸው፣ ከአባታቸው አሊያም ከሌላ ወንድ ዘመዳቸው ፈቃድ ማግኘት ይጠበቅባቸው ነበር።

ልዑል ሞሐመድ ቢን ሰልማን የሴቶችን በሥራ ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ከነበረው 22 በመቶ ወደ 30 በመቶ ከፍ በማድረግ የአገሪቱን ኢኮኖሚ በ2030 ለማሳደግ ዓላማ ይዘው እየሠሩ መሆናቸውን ከሦስት ዓመታት በፊት አስታውቀው ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ