ሜሲ ለስድስተኛ ጊዜ የባሎንዶር አሸናፊ ሆነ

ሊዮኔል ሜሲ Image copyright EPA

የባርሴሎና እና የአርጀንቲናው የፊት መስመር ተጫዋች ሊዮኔል ሜሲ የዓለማችን ምርጥ ተጫዋች በመባል ለስድሰተኛ ጊዜ የባሎንዶር ሽልማት አሸናፊ ሆነ።

የ32 ዓመቱ ሜሲ ባሎንዶርን ሲያሸንፍ እ.አ.አ. ከ 2015 በኋላ የመጀመሪያው ሲሆን ለክለቡና ለአገሩ 54 ግቦችን በማስቆጠር ባለፈው ዓመት ደግሞ ከባርሴሎና ጋር የላሊጋው አሸናፊ መሆን ችሏል።

ማንችስተር ዐይኑን የጣለባቸው የአቶ ምሥጢረ ኃይለሥላሴ ልጆች

ተሰናባቹ ኡናይ ኤምሪን ሊተኳቸው የሚችሉ 7 አሰልጣኞች

የሊቨርፑሉ ተከላካይ ቨርጂል ቫን ዳይክ ደግሞ በዚህ ዓመት ሁለተኛውን ቦታ መያዝ ችሏል። አምስት ጊዜ ባሎንዶርን ማሸነፍ የቻለው የጁቬንቱስና የፖርቹጋር አጥቂው ክርስቲያኖ ሮናልዶ ሦስተኛ መሆኑ ታውቋል።

በሴቶች ደግሞ ከአሜሪካ ጋር የዓል ዋንጫን ማሸነፍ የቻለችው ሜገን ራፊኖ የባሎንዶር አሸናፊ ስትሆን እንግሊዛዊቷ ሉሲ ብሮንዝ ሁለተኛ ሆናለች።

የሊቨርፑሉ ግብ ጠባቂ ብራዚላዊው አሊሴን ቤከር ምርጥ በረኛ ሲባል ጀርመናዊው የባርሴሎና ግብ ጠባቂ ማርክ ቴር ስቴገን እና ብራዚላዊው የማንቸስተር ሲቲ በረኛ ኤደርሰን ሁለተኛና ሦስተኛውን ቦታ ይዘዋል።

የጁቬንቱሱ የመሀል ተከላካይ ደ ሊክት ከ21 ዓመት በታች ምርጥ ተጫዋች ተብሎ በቀድሞ ባሎንዶር አሸናፊዎች ተመርጧል።

ሜሲ ዘንድሮ የባሎንዶር አሸናፊ ሲሆን ውድድሩን ለ11ኛ ተከታታይ ጊዜ ከስፔን ላሊጋ የመጡ ተጫዋቾች እንዲያሸንፉ አድርጓል።

ከመጠጥ ቀጅነት ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን

ሜሲ በሽልማቱ ወቅት ''ምንም እንኳን ባሎንዶርን ያሸነፍኩት ለስድስተኛ ጊዜ ቢሆንም በጣም የተለየ ደስታ ተሰምቶኛል። ባለቤቴ ሁሌም ቢሆን ትልቅ ህልም እንዲኖረን ትነግረኛለች፤ ለዚህም እራሴን በጣም ዕድለኛ አድርጌ ነው የምቆጥረው።''

ሜሲ ለባርሴሎና እስካሁን 700 ጊዜ ተሰልፎ የተጫወተ ሲሆን በስሙም 614 ግቦችን አስቆጥሯል። ከቡድኑም ጋር 10 የላሊጋና አራት ቻምፒየንስ ሊግን ጨምሮ 34 ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ