በሱዳን በፋብሪካ ላይ በተፈጠረ የእሳት አደጋ የሟቾች ቁጥር 23 ደረሰ

የእሳት አደጋ ሠራተኞች እሳት ሲያጠፉ Image copyright Getty Images

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በአንድ የሴራሚክ ማምረቻ ፋብሪካ በተከሰተ ፍንዳታ እና የእሳት አደጋ ቢያንስ 23 ሰዎች ሲሞቱ ከ130 በላይ ሰዎች ለጉዳት መዳረጋቸውን የአገሪቱ መንግሥት አስታወቀ።

የእሳት አደጋው የጋዝ ታንከር በመፈንዳቱ የተከሰተ እንደሆነ ታውቋል።

የወላይታ ዞን ተወካዮች ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር በምን ተስማሙ?

ኤርትራዊው ድምጻዊ በአዲስ አበባ ጥቃት ደረሰበት

ሕንፃው በእሳት ከመያያዙ አስቀድሞም ከባድ ፍንዳታ መሰማቱ ተገልጿል።

"የፍንዳታው ድምፅ ከባድ ነበር፤ በግቢው ውስጥ ቆመው የነበሩ በርካታ መኪኖችም በእሳት ተያይዘዋል" ሲል የፋብሪካው ሠራተኛ የሆነ ግለሰብ የተመለከተውን ለኤ ኤፍ ፒ ተናግሯል።

በፋብሪካው ውስጥ ሌሎች በትክክል ያልተቀመጡ ተቀጣጣይ ነገሮች በመኖራቸው እሳቱ በቀላሉ እንዲዛመት ምክንያት መሆኑንም ኤ ኤፍ ፒ የዜና ወኪል ዘግቧል።

የእሳት አደጋ ሠራተኞች በሥፍራው ከመድረሳቸው በፊትም የእሳት ነበልባልና በጣም የጠቆረ ጭስ በሰማዩ ላይ ተስተውሏል።

የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ተጎጂዎችን እና የሟቾችን አስክሬን እያወጡ ሲሆን ሌሎቹን ለመታደግ ፍለጋ ላይ ተሰማርተዋል።

አደጋውን የአገሪቷ የቴሌቪዥ ጣቢያ "ከባድ የሆነ የሰው እና ንብረት ጥፋት" ሲል ገልፆታል።