ካማላ ሃሪስ ከአሜሪካ ፕሬዚዳንትነት ውድድር ራሳቸውን አገለሉ

ካማላ ሃሪስ Image copyright Getty Images

የአሜሪካን ዲሞክራቲክ ፓርቲን ወክለው ለፕሬዚዳንትነት ሲወዳደሩ የነበሩት ካማላ ሃሪስ ከውድድሩ ራሳቸውን አግልለዋል።

በጥር ወር ላይ የምረጡኝ ቅስቀሳ ዘመቻ የጀመሩት የካሊፎርኒያዋ ሴናተር ካማላ ዘመቻቸው ይሳካል በሚል ከፍተኛ ተስፋ ተጥሎባቸው ነበር።

ነገር ግን ከወራት በፊት ለቅስቀሳ ዘመቻ አቅደውት የነበረው የገንዘብ መጠን በማሽቆልቁሉ አጣብቂኝ ውስጥ ስለከተታቸው በውድድሩ መቀጠል እንደማይችሉ ተዘግቧል።

በቴክኖሎጂ ኢ-ፍትሐዊነትን የምትታገለው ኢትዮጵያዊት

የሴቶች መብት ታጋይዋ ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ ማን ናቸው?

የአምሳ አምስት አመቷ ካማላ ሃሪስ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የሰላ ትችት በመሰንዘር ይታወቃሉ፤ በፓርቲያቸውም ውስጥ ከፍተኛ ስፍራ ተሰጥቷቸው ነበር።

ነገር ግን ከፓርቲያቸው ሌሎች ተቀናቃኞቻቸውን ጆ ባይደን፣ በርኒ ሳንደርስና ኤልዛቤት ዋረን መወዳደር አልቻሉም።

ውድድሩን የጀመሩት በመሪነት ሲሆን፤ በባለፈው ሰኔ በነበረው የቀጥታ ቴሌቪዥን ስርጭት ላይ ጆ ባይደንን በክርክር ድባቅ በመምታታቸው (በክርክር በማሸነፋቸው) ቀጣዩን ውድድር ሊያሸንፉ ይችላሉ የሚል ከፍተኛ ግምት ተሰጥቷቸው ነበር ።

"ማንም መብታችንን ሊሰጠን ስለማይችል፤ ሴቶች ማንንም ሳይጠብቁ በራሳቸው መታገል አለባቸው"

"የመከላከያ ሚኒስቴርን በተሻለ መልኩ መምራት ይቻላል" ኢንጂነር አይሻ መሀመድ

"በሁሉም አቅጣጫ ያለሁበትን ሁኔታ አይቸዋለሁ፤ እናም በህይወቴ ከባድ የሚባለውን ውሳኔ ላይ ደርሻለሁ" በማለት ለደጋፊዎቻቸው ማክሰኞ እለት በፃፉት ኢሜይል አሳውቀዋል።

አክለውም " ለፕሬዚዳንትነት የማደርገው ውድድር በገንዘብ እጥረት ምክንያት መቀጠል አልቻለም" ብለዋል።

አክለውም "እኔ ቢሊዮነር አይደለሁም፤ የምርጫ ዘመቻዬ ወጪየን በራሴ መሸፈን አልችልም። አሁን ባለንበት ሁኔታም ደግሞ ገንዘብ እናሰባስብ ብንል እንኳን አንችልም" ብለዋል።

ኮንፈረንስ በመጥራት ለሰራተኞቻቸው ውሳኔያቸውን ያሳወቁ ሲሆን፤ ባለቤታቸውም በትዊተር ገፃቸው፤ "ከጎንሽ ነኝ፤ እደግፍሻለሁ" በማለት አስፍረዋል።

ሌሎቹም ተቀናቃኝ ተወዳደሪዎች ውድድሩን በማቋረጣቸው ሃዘናቸውን ገልፀዋል። ከነዚህም ውስጥ የዴሞክራቲክ ፕሬዚዳንት ተወዳዳሪው ጆ ባይደን ይገኙበታል።

የቀድሞዋ የሳንፍራንሲስኮ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ካማላ ሃሪስ በሚቀጥለው ወር ላይ ሊካሄድ እቅድ የተያዘለትን የዲሞክራቲክ ፓርቲ ክርክሮችን ለመሳተፍም መስፈርቱን አሟልተው ነበር።

ለምረጡኝ ቅስቀሳቸው አስራ ሁለት ሚሊዮን ዶላር በሶስት ወር ውስጥ መሰብሰብ የቻሉት ፖለቲከኛዋ በመጡበት ፍጥነት መቀጠል አልቻሉም።

ተያያዥ ርዕሶች