ንቅሳት እንደ ወሲብ ንግድ ማሳለጫ. . .
የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።

ንቅሳት እንደ ወሲብ ንግድ ማሳለጫ. . .

አሜሪካ ውስጥ በርካታ ሴቶች ተገደው በወሲብ ንግድ ላይ እንዲሰማሩ እንደሚደረግ ከአገሪቱ መንግሥት የፍትህ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በዚህ ድርጊት ውስጥ በግድ የሚሰማሩ ሴቶች በአጋቾቻቸው የተለያዩ ንቅሳቶችን እንዲነቀሱ ይደረጋል። ከዚህ የወሲብ ባርነት ነጻ የወጡ ሴቶችን ለመርዳት ከሚደረጉ ጥረቶች መካከል ያለፈ ሕይወታቸውን የሚያስታውሰውን ንቅሳት ማጥፋት አንዱ ነው።