ፕሬዚደንት ኢሳያስ የኢትዮጵያውን ጨምሮ የአምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ

አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ Image copyright Yemane G Meskel

ፕሬዚደንት ኢሳያስ አፈወርቂ በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር የሆኑትን የሬድዋን ሁሴንን ጨምሮ የ29 አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ።

የኤርትራ የኢንፎርሜሽን ሚንስትር የማነ ገብረ መስቀል በምስል አስደግፈው በትዊተር ገፃቸው ላይ እንዳስታወቁት፤ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡት መካከል የኢትዮጵያ፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ጀርመን፣ የዩናይትድ ኪንግደም፣ ህንድ፣ አውሮፓ ሕብረት፣ ግብፅ እና ደቡብ አፍሪካ አምባሳደሮች ይገኙበታል።

የትናንትናዋ እለት- በኢትዮ ኤርትራ ግጭት ቤተሰባቸው ለተለያየ?

እንቅስቃሴ አልባዋ ምጽዋ

የማስታወቂያ ሚንስትሩ ጨምረው እንደጠቀሱት ዛሬ ለፕሬዝደንት ኢሳያስ የሹመት ደብዳቤያቸውን ካቀረቡት መካከል መቀመጫቸውን ኤርትራ ያላደረጉም ይገኙበታል።

ሬድዋን ሁሴን በኤርትራ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው ከተሾሙ 17 ወራት ቢያልፋቸውም እስከ ዛሬ የሹመት ደብዳቤያቸውን ለፕሬዝደንቱ አላቀረቡም ነበር።

ይህንንም ተከትሎ ከወራት በፊት የአምባሳደሩ የአምባሳደርነት ሹመታቸው በኤርትራ መንግሥት ተቀባይነት አላገኝም የሚል መረጃ በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ሲናፈስ ነበር።

በወቅቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃው ትክክል አለመሆኑን ጠቅሷል።

የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብያት ጌታቸው "የአንድ አምባሳደር የሹመት ደብዳቤ በተቀባዩ ሃገር ተቀባይነትን አላገኘም የሚባለው፤ አምባሳደሩ በተቀባዩ ሃገር እንዲሰራ ሳይፈቀድለት ሲቀር ነው። . . . አምባሳደሩ ሥራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ። አንድ አምባሳደር በተቀባዩ ሃገር ተቀባይነትን ሳያገኝ ሥራ መጀመር አይችልም" በማለት አስረድተው ነበር።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ