ከ11 ኪሎ በላይ የኮኬይን ዕጽ አዲስ አበባ ውስጥ ተያዘ

ከተያዙት ዕጾች መካከል Image copyright MINISTRY OF REVENUES

የገቢዎች ሚኒስቴር በትናንትናው ዕለት [ረቡዕ] በቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ በኩል ሊዘወወር የነበረ ከ11 ኪሎ ግራም በላይ የሚመዝን የኮኬይን ዕጽ መያዙን አስታወቀ።

ይህ የተያዘው ኮኬይን የተባለው አደንዛዥ ዕጽ፤ ገበያ ላይ ቢውል ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ዋጋ ሊያወጣ ይችል እንደነበር ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ዕጹን ከተለያዩ አገራት አንስቶ፣ በአዲስ አበባ በኩል በማለፍ ወደ ሌላ ቦታ ለማዘዋወር ሲሞከር፤ በጉምሩክ የምርመራ ሠራተኞችና በብሔራዊ የመረጃና ደህንነት አገልግሎት አባላት አማካይነት መያዙ ተገልጿል።

የገቢዎች ሚኒስቴር እንደገለጸው፤ አደንዛዥ እጹን ሲያዘዋውሩ ነበር ተብለው የተያዙት ሁለቱም ሴቶች ሲሆኑ፤ ከተለያዩ አገራትና በተለያዩ በረራዎች ተጉዘው አዲስ አበባ የደረሱ መሆናቸውም ተጠቅሷል።

ዕጽ በማዘዋወር የተጠረጠረችው ናይጄሪያዊት ከእስር ተለቀቀች

"በጥሩ ጤንነት ላይ አይደለችም" የስምረት ካህሳይ ቤተሰቦች

ከፍተኛ መጠን ያለው ዕፅ በአሜሪካና ሜክሲኮ ድንበር ተያዘ

በዚህም መሰረት ከደቡብ አፍሪካ የተነሳችውና የዚያው አገር ዜጋ የሆነችው ኖምዛሞ ግላዲየስ ቦዛ 7.4 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን ይዛ በአዲስ አበባ በኩል ወደ ህንዷ ዴልሂ ከተማ የመጓዝ እቅድ ነበራት ተብሏል።

ሌላዋ ተጠርጣሪ አንቲቃ ሱለይማን ቂዚ አባሶባ ደግሞ ደግሞ የአዘርባጃን ዜጋ ስትሆን፤ የተነሳችው ከሩሲያዋ ሞስኮ ከተማ ነበር። ግለሰቧ 4 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን ይዛ በአዲስ አበባ በኩል በማቋረጥ ወደ ታይላንዷ ባንኮክ ልትጓዝ ነበር ተብሏል።

የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳሳወቀው፤ በአንድ ቀን ብቻ ከሁለቱ ግለሰቦች 11.4 ኪሎ ግራም የሚመዝን ኮኬይን በኢትዮጵያ በኩል ወደ ሌሎች አገራት ሊተላለፍ ሲል ተያዟል።

ተያያዥ ርዕሶች