በመንፈሳዊ ፍቅር የሚያሰክረው የሱፊዎች ዝማሬና ውዝዋዜ...

በመንፈሳዊ ፍቅር የሚያሰክረው የሱፊዎች ዝማሬና ውዝዋዜ...

ሱፊዎች ክፍለ ዘመናትን የተሻገረ ዕምነት አላቸው። የምስጋና ዝማሬያቸውና ውዝዋዜያቸው በርካቶችን በፍቅር ማርኳል። መቻቻልና ታማኝነት የዕምነታቸው ዋነኛ ማጠንጠኛ ነው። ማንንም መጉዳት አይሹም፤ አስተምህሯቸውም አይፈቅድም። 'ዝክር' ብለው በሚጠሩት ሥነ ሥርዓት ተሰባስበው እየዘመሩ የፈጣሪያቸውን መልካምነት ይመሰክራሉ። ይህ ተወዳጅ ባሕላቸውና ዕምነታቸው ግን በአክራሪዎች ዘንድ አልተወደደም። በዚህም ምክንያት ከግብጽ እስከ ፓኪስታን የጥቃት አደጋ እየወደቀባቸው ነው። ተከታዩ ተንቀሳቃሽ ምስል ምዕመናኑ በመንፈሳዊ ፍቅር እንዴት እንደሚሰክሩ ያሳያል።