'ሜክሲኳዊ ስለሆነች' ብላ ታዳጊ የገጨችው አሜሪካዊት ታሠረች

ኒኮል ማሪ Image copyright Polk County Jail

"ሜክሲኳዊ" ትመስላለች ያለቻትን ታዳጊ ሆነ ብላ የገጨች አሜሪካዊት በግድያ ሙከራ በቁጥጥር ሥር ዋለች።

የ14 ዓመቷ ታዳጊ የተገጨችው ወደ ትምህርት ቤት እየሄደች ሳለ እንደነበር ፖሊስ ተናግሯል። ፖሊሶች ታዳጊዋ የተገጨችው ሆነ ተብሎ እንደሆነ እንደደረሱበት ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

የፖሊስ ኃላፊው ማይክል ቬኔማ እንደተናገሩት፤ ተጠርጣሪዋ ታዳጊዋን የገጨችው ሆነ ብላ እንደሆነ ስታምን በጣም ተደንቀዋል።

ለመታሰር ብሎ ሰው የገጨው የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት

ሃዩንዳይ የሚራመድ መኪና አምርቷል

የአንበሳ ደቦሏ ላምቦርጊኒ መኪና ውስጥ ተገኘች

"ታዳጊዋን የገጨቻት ሜክሲኳዊ ስለሆነች እንደሆነ ለመርማሪዎች ተናግራለች። የሚያንቋሽሽ ነገርም ተናግራለች" ሲሉ ገልጸዋል።

ሰዎችን ለሚጠሉ፣ ጥቃት ለመሰንዘር ለሚነሳሱ ግለሰቦችም ማኅበረሰቡ ቦታ እንደሌላቸው ኃላፊው ተናግረዋል።

የ42 ዓመቷ አሜሪካዊት ታዳጊዋን በገጨቻት እለት በሌላ ወንጀል ተጠርጥራ ፖሊስ ጣቢያ ቆይታ ነበር። ፖሊሶች ተጠርጣሪዋ ላይ የጥላቻ ተግባር ክስ እንደሚመሰርቱ ገልጸዋል።