ኒውዚላንዳዊያን የጦር መሳሪያ በማውደም ተጠምደዋል

ባለፈው ዓመት መጋቢት ወር ላይ ኒውዚላንድ ውስጥ አንድ ጥቃት አድራሽ ግለሰብ በሁለት መስጂዶች ላይ በፈጸመው ጥቃት ከ50 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ክስተቱ በኒው ዚላንድ ታሪክ 'ጥቁር ቀን' ሆኖ አልፏል። ይህንን ተከትሎም በአገሪቱ የጦር መሳሪያ ክልከላ ተደርጓል። ከክልከላው በኋላ መሳሪያዎች ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ እየተደረገ ሲሆን እስካሁን ከ50 ሺህ በላይ የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች ተሰባብረዋል።