በኡራጓይ 40 ቢሊዮን ብር የሚያወጣ ኮኬይን ተያዘ

የኮኬይኑ ክምር ጡብ በትንሹ 40 ቢሊዮን ብር ያወጣል Image copyright AFP
አጭር የምስል መግለጫ የኮኬይኑ ክምር ጡብ በትንሹ 40 ቢሊዮን ብር ያወጣል

ኡራጓይ በታሪክ እጅግ ግዙፍ የኮይኬን ዱቄት መያዟን ዛሬ ይፋ አድርጋለች። የኮኬይን ዱቄቱ 6 ቶን ይመዝናል። ይህም ለኮኬይን አስተላላፊዎች እጅግ መራሩ መርዶ ይሆናል ተብሏል።

የባሕር ትራንዚትና የጉምሩክ መኮንኖች እንደተናገሩት ከሆነ ከ6 ቶን ኮኬይኑ ውስጥ 4 ቶን ኮኬይን የተያዘው በሞንቴቪዲዮ ወደብ ላይ ነው። የሶያ ዱቄት ማከማቻ ብልቃጦች ውስጥ ተደብቆ እንደነበረ የተነገረው ይህ ኮኬይን መዳረሻውን ያደረገው ቶጎ፣ ሎሜ ነበር።

የተቀረው 1.5 ቶን ኬኬይኑ ደግሞ ወደበኋላ ተይዟል።

በድምሩ በቁጥጥር የተያዘው የኮኬይን መጠን አሁን ባለው ገበያ ቢሰላ በትንሹ 1.3 ቢሊዮን ዶላር ወይም 1 ቢሊዮን የእንግሊዝ ፓውንድ ያወጣል። ይህ ወደኛ ገንዘብ ቢመነዘር 40 ቢሊዮን ብር ይጠጋል።

ኡራጓይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁነኛ የአደገኛ እጽ መተላለፊያ እየሆነች ነው። ወደ አውሮፓ፣ አፍሪካና ሰሜን አሜሪካ የሚላላኩ አደገኛ እጾች በኡራጓይ በኩል ለማሳለፍ ሲሞከር ይህ የመጀመርያው አይደለም።

ሲሽልስ፡ የሔሮይን ወረርሽኝ የሚያመሳቅላት ምድረ ገነት

በጀርመን ከፍተኛ መጠን ያለው ኮኬይን በቁጥጥር ሥር ዋለ

በዛምቢያ ከካናቢስ እፅ ኬክ የጋገረው ተማሪ 50 ገጽ ሃተታ በመፃፍ ተቀጣ

ከአንድ ወር በፊት 3 ቶን ኮንቴይነር ኮኬን በሞንቴቪዶ ወደብ አድርጎ ወደ ቤኒን ሊሻገር ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል።

4́.4 ቶን የሚመዝነው ኮኬይን ሊያዝ ምክንያት የሆነው የኤክስሬይ ፍተሻ ማሽኑ ምንነቱ የማይታወቅ ነገር በማሳየቱ በተፈጠረ ጥርጣሬ ነው ተብሏል።

በዋናነት ጥርጣሬው ሊፈጠር የቻለው ግን ኩባንያው ከዚህ ቀደም የሶያ ፍሬ ዱቄትን ወደ አፍሪካ ልኮ አለማወቁ የፈጠረው ጥርጣሬ ነው።

እያንዳንዱ የኮኬይን ግግር ጡብ 1.1 ኪሎ ግራም እንደሚመዝንንና ተመሳሳይ 3000 የኮኬይን ጡብ መያዙን የተናገሩት የባሕር ኃይል ተጠሪው ዲኣጎ ፔሮና ናቸው። የኮኬይን ጡቦቹ ሊጫኑ የነበረው ንብረትንቷ የጣሊያን በሆነች መርከብ ነበር።

ኮኬይኑ መነሻው ከየት እንደሆነ እስካሁንም ያልተደረሰበት ሲሆን ባለፈው ማክሰኞ ግን በአንድ በደቡብ ምዕራብ ሶሪያኖ ከተማ በሚገኝ የእንሰሳት ጋጣ ውስጥ እየወጣ ሲጫን እንደነበር መረጃ ተገኝቷል።

ፖሊስ ይህን የቀንድ ከብቶች ጋጣ በከበበበት ወቅትም ተጨማሪ ኮኬይን ማግኘቱን ገልጧል።

ዋናው ነገር ኡራጓይ በአደገኛ እጽ ዙርያ ያላትን ቁርጠኝነት ለዓለም ማሳየታችን ነው። ከእጽ አስተላላፊዎች ጋር ትግሉ ይቀጥላል ብለዋል የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ።

ተያያዥ ርዕሶች