በታይላንድ ዋሻ ተቀብረው የነበሩትን ታዳጊዎች ያዳነው በደም መመረዝ ሞተ

በታይላንድ ተቀብረውበት የነበረበት ዋሻ Image copyright Getty Images

በባለፈው ዓመት ለሁለት ሳምንት ያህል በታይላንድ ዋሻ ውስጥ ተቀብረው የነበሩት የታዳጊ ወንዶች የእግር ኳስ ቡድንና አሰልጣኛቸውን ካዳኑት የነፍስ አድን ሰራተኞች መካከል አንደኛው በደም መመረዝ ህይወቱ እንዳለፈ ተዘግቧል።

በደም መመረዝ የተለከፈውም አስራ ሁለቱን ታዳጊ ኳስ ተጫወቾችንና አሰልጣኛቸውን ከተቀረቀሩበት ዋሻ ለማውጣት በሚሞክርበት ወቅት ነው ተብሏል።

ጠፍተው የነበሩት ታይላንዳዊያን ልጆች በማንችስተር ከተማ

አሜሪካ በታሪኳ ከፍተኛ የጅምላ ግድያ የተፈጸመበት ዓመት አስመዘገበች

ታዳጊዎቹ ታም ሉዋንግ የተባለ መጠሪያ ያለውን ዋሻ ለመጎብኘት በሄዱበት ወቅት፤ ዋሻው በውሃ በመሞላቱ ለ17 ቀናት መውጣት ሳይችሉ መቅረታቸው ይታወሳል።

የባህር ጠላቂ ነፍስ አድን አባል የነበረው ቤሩት ፓካብራ ደሙ እንደተመረዘ ከታወቀ በኋላ ለረዥም ጊዜያት የህክምና ክትትል ቢያደርግም ህይወቱ አልፏል።

ሌላኛው የአደጋ ወቅት ሰራተኛ ሳማን ጉናን ታዳጊዎቹን ከተቀረቀሩበት ዋሻ ለማውጣት በሚደረገው ሙከራ መሞቱ ይታወሳል።

ሳማን የቀድሞ የባህር ጠላቂ ነፍስ አድን ሰራተኛ የነበረ ሲሆን የነፍስ አድን ሰራተኞቹ የታዳጊዎችን ህይወት ለማትረፍ በሚረባረቡበት ወቅት አየር አጥሮት ተዝለፍልፎ የወደቀ ሲሆን ህሊናውን ከሳተ ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ህይወቱ አልፏል።

መስዋዕትነቱንም ሆነ መልካም ምግባሩን ለማስታወስ ከዋሻው መግቢያ አካባቢ ሃውልት ቆሞለታል።

ቤሩትም በዚህ ሳምንት አርብ በተወለደበት ግዛት ሳቱን የእስልምና እምነቱ በሚፈቅደው መሰረት የቀብር ስርአቱ ተፈፅሟል።

'ዋይልድ ቦር' የሚል ቅጽል ስም ያለው የእግር ኳስ ቡድን አባላት የሆኑት ከ11-16 ዕድሜ ያላቸው ታዳጊዎችና የሃያ አምስት አመቱ አሰልጣኛቸው ዋሻውን በመጎብኘት እያሉ ከፍተኛ የጎርፍ አደጋ በማጋጠሙ መውጣት እንዳልቻሉ እንደተሰማ የመላው ዓለምን ቀልብ ስበው ነበር።

"የኢትዮጵያ የህክምና ታሪክ አልተጠናም" ዶክተር አሰፋ ባልቻ

በርኖስና ባና -የመንዝ ባህላዊ ልብስ

ከ17 ቀናት በኋላም ከ90 በላይ የባህር ጠላቂ ነፍስ አድን ሰራተኞች በተረባረቡበት የማዳን ሥራ ከዋሻው መውጣት ችለዋል።

Image copyright EPA/CHIANG RAI PROVINCIAL PUBLIC RELATIONS OFFICE

ኳስ ተጫዋቾቹ ልጆችና አሰልጣኛቸው ለዘጠኝ ቀናት ያህል ያሉበት ባለመታወቁ ጠፍተዋል ተብሎ የነበረ ሲሆን፤ በአስረኛው ቀን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በዋሻው ክፍተት በኩል ተመልክተዋቸዋል።

በሰሜናዊ ታይላንድ የሚገኘው ይሄው ዋሻ ከአንድ ዓመት በኋላ ተከፍቶ ታይላንዳውያን መጎብኘት ጀምረዋል።

ተያያዥ ርዕሶች