ከሰው ይልቅ ድመት የበዛባት ከተማ

የሳላህ ድመቶች

ለወራት በሶሪያ መንግሥትና በሩሲያ ሃይሎች የቦምብ ጥቃት ሲሰነዘርባት የነበረችው የሶሪያዋ ከተማ ካፍር ናቢ ከሰዎች ይልቅ የድመቶች ቁጥር የበለጠባት ከተማ መሆኗ ተነገረ።

የሶሪያ አማፅያን ጠንካራ ይዞታ በነበረችው ካፈር ናቢ ላይ ከባድ የአየር ጥቃት ሲሰነዘር ብዙዎች ከተማዋን ለቅቀው ቢወጡም አንዳንዶች እዚያው ቀርተዋል።

ቀደም ሲል ከተማዋ 40 ሺህ የሚሆን ኗሪ የነበራት ሲሆን አሁን በከተማዋ የቀሩት መቶ እንኳ አይሞሉም።

የአንበሳ ደቦሏ ላምቦርጊኒ መኪና ውስጥ ተገኘች

ቱርክ ሶሪያ ላይ የከፈተችውን ጥቃት ለማቋረጥ ተስማማች

የአይኤስ አባል የነበረችው ሴት ወደ አየርላንድ ልትመለስ ነው

በተቃራኒው በእርግጠኝነት በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ያሉ ድመቶች ቁጥርን መናገር ባይቻልም በመቶዎች፤ በሺዎችም ሊሆኑ እንደሚችሉ ይነገራል።

ሃያ ሰላሳ የሚሆኑ ድመቶች ከነሳላህ ጎን ሆነው መንገድ ላይ ወዲህ ወዲያ ይላሉ።

የ32 ዓመቱ ሳላህ ጃር ግማሽ ደርዘን ከሚሆኑ ድመቶች ጋር አንድ ፍርስራሽ ውስጥ በስጋት እየኖረ ነው። ግን በዚህ እጅ አስፈሪ ሁኔታ ውስጥ ድመቶቹ በዙሪያው መሆናቸው ስቃዩን እንደቀነሰለት ይናገራል።

"የምበላው አትክልት፣ ኑድልስም ይሁን ወይም የደረቀ ዳቦ የበላሁትን ይበላሉ። በእንዲህ ያለው ፈታኝ ሁኔታ ሁላችንም ፍጡራን ደካሞች ስለሆንን መደጋገፍ ይኖርብናል" ይላል ሳላህ።

ሳላህ፣ ፍሬሽ ለተሰኘ ኤፍ ኤም ሬድዮ ዘጋቢ በመሆን እየሰራ ሲሆን፣ የሬድዮ ጣቢያው ከአየር ድበደባው በኋላ ፍርስራሽ ሆኗል።

ነገር ግን እንደ እድል ሆኖ የጣቢያው ማሰራጫ መሳሪያዎች ጥቃቱ ከመጀመሩ ከጥቂት ቀናት በፊት አቅራቢያ ወዳለ ከተማ ተወስደዋል።

በማያቋርጠው የቦንብ ጥቃት ድመቶችም እንደ ሰዎች ተጎጅ ሲሆኑ አቅም በፈቀደ እነሱንም ለመርዳት ይሞከራል ይላል ሳላህ።

"የአንድ ጓደኛዬ ድመት የፊት እግሩን በሮኬት ተመትቶ በጣም ተጎድቶ ስለነበር ለህክምና ወደ ኢድሊብ ወሰድነው። አሁን አገግሞ በደንብ ይራመዳል" ይላል ሳላህ።

ሳላህ ከድመቶቹ ጋር ጥሩም፣ መጥፎም ጊዜን እንዲሁም የደስታንም የህመምና የስቃይ ስሜትንም እየተካፈሉ እንዳለ ይናገራል። በጥቅሉ የህይወት አጋር ሆነናልም ይላል።

እሱም ሆነ በካፍር ናብል የቀሩ ጥቂት ባልንጀሮቹ ከተማዋን ለቅቀው መውጣት ግድ የሚሆንባቸው ከሆነ የቻሉትን ያህል ድመቶች ይዘው እንጂ ጥለው እንደማይሰደዱ በእርግጠኝነት ይናገራል ሳላህ።

በከተማዋ ምሽት ላይ እየጮሁ በፍርስራሹ መንደር የሚቀመስ የሚያስሱ ውሾችም በርካታ ናቸው። ውሾቹም ቤት አልባዎች፣ የሚበሉትን ፈላጊዎች ናቸው፤ ምንም እንኳ እንደ ድመቶች ብዙ የሚያስጠጋቸው ባያገኙም።

ተያያዥ ርዕሶች