በብሩንዲ ከአራት ሺህ በላይ የጅምላ መቃብሮች ተገኙ

የሟቾች ልብስ Image copyright CVR

የብሩንዲው የእውነትና እርቅ ኮሚሽን ሃገሪቱ በአውሮፓዊያን 1962 ነጻነቷን ካገኘች በኋላ ከ4000 በላይ የጅምላ መቃብሮችን በምርመራው እንዳገኘ አስታወቀ።

በ2018 የተቋቋመው ኮሚሽኑ፤ ላለፉት አስርት ዓመታት በብሄር ግጭቶች ስትታመስ በቆየችው ብሩንዲ ባደረግኩት ምርመራ በዓመታቱ የተገደሉ 142 ሺ 505 ሰዎች ማንነትም ጭምር ደርሼበታለው ብሏል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚታወቁት በ 1965፣ 1969፣ 1972፣ 1988 እና 1993 የተፈጸሙት የዘር ማጥፋት ዘመቻዎች ላይ የወቅቱ ፖለቲከኞችም ጭምር ተሳታፊ ነበሩ በሚል ክስ ይቀርብባቸዋል።

እግራቸው አሜሪካ ልባቸው አፍሪካ ያለ የሆሊውድ ተዋንያን

በ2019 አፍሪካ ያጣቻቸው ታላላቆች

ፖለቲከኞቹ በሁቱ እና ቱትሲዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት እንዲቀሰቀስም ዋነኛ ተሳታፊዎች እንደነበሩ በርካቶች ገልጸዋል።

የኮሚሽኑ ዋና ጸሀፊ ፒዬር ንዳዪካሪዬ ለሀገሪቱ ፓርላማ ግኝታቸውን ሲያቀርቡ እንደገለጹት ''ከዚህ በኋላ ገና በርካታ የጅምላ መቃብሮችን እንደምናገኝ እናስባለን፤ ምክንያቱም ስለመቃብሮቹ የሚያውቁት ሰዎች ስለጉዳዩ ለማውራት ይፈራሉ። አንዳንዶቹ ደግሞ ከድርጊቱ አሰቃቂነት የተነሳ ስለጉዳዩ ማስታወስ አይፈልጉም'' ብለዋል።

በጅምላ መቃብሮቹ የተቀበሩት ሰዎች እንዴትና በማን እንደተገደሉ ማወቅ በጥቃት ፈጻሚዎቹና በተጎጂዎች ቤተሰብ መካከል ሰላማዊ የሆነ የእርቅና የመግባባት ሥራ ለመስራት መሳኝ መሆኑንም ጸሀፊው አክለዋል።

ሰኞ ዕለት 270 አስክሬኖች የተቀበሩበት አንድ የጅምላ መቃብር በቡጁምቡራ ለሕዝብ ይፋ ተደርጎ ነበር።

መቃብሩ በአውሮፓዊያኑ 1993 የሃገሪቱ የመጀመሪያው ሁቱ ፕሬዝደንት ሜልቾር ንዳዳዬ መገደላቸውን ተከትሎ በተቀሰቀሰ ግጭት የተገደሉ እንደሆነ በርካቶች ገልጸዋል።

ብሩንዲ መጠጥ ቤቶች በጊዜ እንዲዘጉ አዘዘች

የፕሬዝዳንቱን መገደል በሁቱ አማጺያንና በቱትሲዎች በብዛት በተዋቀረው የሀገሪቱ መከላከያ ኃይል መካከል 'እጅግ አሰቃቂ' የሚባል ግጭት ተቀስቅሶ ነበር። 12 ዓመት በፈጀው ጦርነትም ከ300 ሺህ በላይ ዜጎች ሞተዋል።

በቡጁምቡራ የጅምላ መቃብሩን የተመለከቱ አንዳንድ ሰዎች፤ የአስክሬኖቹን አልባሳት በመመልከት የሟቾችን ማንነት መለየት የቻሉ ሲሆን በተጨማሪነት ደግሞ ከአንዳንድ ሟቾች ጋር መታወቂያዎች መገኘታቸውም ታውቋል።

ተያያዥ ርዕሶች