በድንገት ለማረፍ ትምህርት ቤት ላይ ነዳጅ የደፋው አውሮፕላን

አንድ የመንገደኞች አውሮፕላን በሎስ አንጀለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በድንገት ለማረፍ፤ በአንድ ትምህርት ቤት የመጫወቻ ሜዳ ላይ ነዳጅ በማፍሰሱ በርካቶች ጉዳት እንዳጋጠማቸው ተገለፀ።

ቢያንስ 17 ህፃናት እና ሌሎች በርካታ አዋቂዎች ለቆዳ መቆጣትና ለአተነፋፈስ ችግር ተዳርገው ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛሉ።

ኢራን፤ አውሮፕላኑ በሚሳኤል ሲመታ ቀርጿል ያለችውን ግለሰብ አሰረች

ልብ የረሳው አውሮፕላን

አውሮፕላኖች በድንገት ለማረፍ የሚያስገድዳቸው ሁኔታ ሲያጋጥማቸው ነዳጃቸውን በማፍሰስ ሊቀንሱ ይችላሉ፤ ነገር ግን ይህን ማድረግ የሚችሉት በተፈቀዱ አካባቢዎች እና ከከፍተኛ ቦታ መሆን እንዳለበት የአቪየሽን ሕግ ያዛል።

የደልታ አየር መንገድ አውሮፕላን ወደ አየር ማረፊያው ለመመለስ የተገደደው በሞተሩ ላይ ባጋጠመው ችግር ነበር።

ከሎስ አንጀለስ አውሮፕላን ማረፊያ በምስራቅ አቅጣጫ 26 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ኩዳህይ፤ ፓርክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ማህበረሰቦች ላይ የደረሰው ጉዳት ቀላል እንደሆነ ተገልጿል።

እንደ ሎስ አንጀለስ ታይምስ ከሆነ ነዳጁ ሲለቀቅ የሁለት ክፍል ተማሪዎች ከመማሪያ ክፍል ውጭ ነበሩ።

የኩዳህይ ከንቲባ ኤልዛቤት አልካንታር "በጣም ነው የተበሳጨሁት፤ ይህ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው፤ እነዚህ ልጆች ህፃናት ናቸው" ሲሉ የተሰማቸውን ለጋዜጣው ገልፀዋል።

ደልታ አየር መንገድ በበኩሉ በሰጠው መግለጫ፤ የመንገደኞች አውሮፕላኑ ለማረፍ ሲል የነበረውን ክብደት ለመቀነስ ነዳጅ መድፋቱን አረጋግጠዋል።

የግዙፉ ግድብ ግንባታ፡ የኢትዮጵያና ግብፅ ቅራኔ

የፌዴራል አቪየሽን አስተዳደር ቃል አቀባይ አለን ኬኒትዘር፤ ለሮይተርስ የዜና ወኪል፤ "የፌደራል አቪየሽን አስተዳደር ከአደጋው ጀርባ ያለውን እየመረመረ ነው፤ በአሜሪካ ዋና ዋና አየር መንገዶች ውስጥ እና ውጭ ለሚንቀሳቀሱ አውሮፕላኖች የተለየ ነዳጅ መቀነሻ ሂደቶች አሉ" ሲሉ አስረድተዋል።

እርሳቸው እንዳሉት ሕዝብ በማይኖርባቸው አካባቢዎች ነዳጅ እንዲያፈሱ አሠራሩ ይፈቅዳል፤ በተለይ ደግሞ ከከፍታ ቦታ ላይ። ከከፍታ ቦታ ላይ ሲሆን የነዳጁ አቶሞች መሬት ላይ ከማረፋቸው በፊት በአየር ላይ ተሰራጭተው በዚያው ተነው ይቀራሉ።

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ