ከ3 ሺህ ዓመት በፊት የሞቱት የሃይማኖት መሪ ድምጽ ተሰማ

የእርሶ መሳሪያ ሚዲያ ፕሌይ ባክን ማጫወት ኣልተቻለም።
ከ3 ሺህ ዓመት በፊት የሞቱት ቄስ ድምጽ ተሰማ

ይህችን ዓለም ተሰናብተው አስክሬናቸው ደርቆ የተቀመጠው ግብፃዊው የሃይማኖት መሪ ድምፃቸው በሰው ሰራሽ የድምፅ ማስተላለፊያ ዳግም መሰማቱን ተመራማሪዎች አስታወቁ።

ኔስያማንስ ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1099 እና 1069 ጊዜ መካከል በፋራኦህ ራምሴስ 11ኛ ፖለቲካ አገዛዝ ሥርዓት የኖሩ የሃይማኖት መሪ ነበሩ።

በግብፅ በናይል ወንዝ አቅራቢያ በ800 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጥንታዊቷ የግብፅ ከተማ ቴቤስ ይኖሩ የነበሩት እኝህ የሃይማኖት መሪ፤ ዝማሬን ጨምሮ ለሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት ጠንካራና ተወዳጅ ድምፅ እንዲኖራቸው ይፈልጉ ነበር።

ቢሆንም በሚገጥማቸው የጥርስና ድድ ህመም የፍላጎታቸው ሳይሞላ ይህችን ምድር ተሰናብተዋል።

በጥቅም ላይ የዋሉ የጥንታዊ ግብፅ የህክምና ጥበባት

ግብፅ ከአሜሪካ ያስመለሰችውን ጥንታዊ የሬሳ ሳጥን ለዕይታ አቀረበች

ኔስያማን ሲሞቱ ድምፃቸው ይጥፋ እንጅ ከ3 ሺህ ዓመታት በኋላ ተመራማሪዎች ድምፃቸውን መልሰው ነፍስ ዘርተውበታል- ድምፃቸውም ዳግም ተሰምቷል።

"በአስክሬን ሳጥናቸው ላይ ምን ይፈልጉ እንደነበር ተፅፏል፤ እኛም ይሄን ምኞታቸው እውን እንዲሆን ማድረግ ችለናል" ሲሉ በዮርክ ዩኒቨርሲቲ የቅሪተ አካል ፕሮፌሰር እና የጥናቱ ተባባሪ ፀሃፊ የሆኑት ጆን ፍሌቸር ተናግረዋል።

እንደገና ነፍስ እንዲዘራበት የተደረገው የቄስ ኔስያማን ድምፅ የአናባቢ ድምፆች ድምፀት ያለው ሲሆን በጎች ወይም ፍሎች ሲያዝኑ የሚያሰሙትን ድምፅ ይመስላል።

ተመራማሪዎቹ በቄሱ የድምፅ ቧንቧ ላይ የተመሠረተ ባለ ሦስት አውታር የድምፅ ማተሚያ ሳጥን በመፍጠር ድምፃቸውን የሚያነሳ [ስካን የሚያደርግ] መሳሪያ ተጠቅመዋል።

በሰው ሰራሽ ጉሮሮ የድምፅ ቧንቧ በመጠቀም የቄሱን የሚመስል የአናባቢ ድምፀት በመፍጠር የቄሱን ኔስያመንን ድምፅ እንዲመስል አድርገዋል።

ምርምሩ ከሞተ ሰው በሰው ሰራሽ መንገድ ድምፅ እንደገና በመፍጠር ውጤታማ የሆነ ፕሮጀክት ሳይሆን እንዳልቀረ የታመነ ሲሆን፤ ወደፊት ተመራማሪዎቹ የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂን በመጠቀም የቄስ ኔስያማንን ድምፅ ሙሉ ዓረፍተ ነገር እንደገና ለመፍጠር ተስፋ እንዳላቸው ተናግረዋል።

በሮያል ሆሎወይ፣ በለንደን ዩኒቨርሲቲ፣ በዮርክ ዩኒቨርሲቲ እና በሊድስ ሙዚየም የተሰራው ይሄው ምርምር በሳይንሳዊ ጆርናል ላይ ባለፈው ማክሰኞ ታትሟል።

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቄሱ በድድ እና ጥርስ ህመም ይሰቃዩ ነበር። ከዚያም በጣም ከፍተኛ የሆነ የሰውነት መቆጣትን ተከትሎ በ50 ዎቹ እድሜ ላይ ሳሉ ሕይወታቸው አልፏል።

በእርሳቸው ላይ የተካሄዱ ሳይንሳዊ ምርምሮች ጥንታዊቷን ግብፅ ለመረዳት አስተዋፅኦ እንዳደረገም ይነገራል።

የቄስ ኔስያማን አስክሬን ቅሪት አካል በሊድስ ሲቲ ሙዚየም ለዕይታ ቀርቦ ይገኛል።

ድምፅ ፈታዮቹ መረዋዎች

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ