ፖስተኛው 24 ሺህ ደብዳቤዎችን በቤቱ ደብቆ ተገኘ

ፖስተኛ ከቶኪዮ በስተምእራብ በምትገኘው ሃያካዋ Image copyright Getty Images

የጃፓን የቀድሞ ፖስተኛ የነበረ ግለሰብ ለሰዎች መድረስ የነበረባቸው 24 ሺህ ደብዳቤዎችን ወደ ታለመላቸው አድራሻ በመላክ ፋንታ በቤቱ ደብቆ ማስቀመጡን በምርመራ እንደደረሰበት ፖሊስ አስታወቀ።

ደብዳቤዎቹ የተገኙት ቶኪዮ አቅራቢያ ካናጋዋ በሚባለው አካባቢ የሚገኘው የ61 ዓመቱ የቀድሞ ፖስተኛ ቤት በተፈተሸበት ወቅት ነው።

ፖስታዎቹን ማድረስ አድካሚ ስለሆነበትና በእድሜ ከእሱ ከሚያንሱ ፖስተኞች ጋር ሲነፃፀር ደካማ ሆኖ ላለመታየት ሲል ፖስታዎቹን ቤቱ እንዳስቀራቸው ተናግሯል ግለሰቡ።

ጃፓናዊው ቢሊዬነር ወደ ሕዋ አብራው የምትጓዝ 'ውሃ አጣጭ' እየፈለገ ነው

ጃፓን ከቀበሌ መታወቂያ ያነሰች ሞባይል ሠራች

ግለሰቡ የቅርንጫፍ ሃላፊ ሆኖ ይሰራበት የነበረው 'ኮዮዶ ኒውስ' ባለፈው ዓመት ተጠራጥሮ ነገሮችን ለማጣራት ሲሞክር ግለሰቡ ጥፋቱን በማመኑ ከሥራ አባሮታል።

ይህን ተከትሎም ግለሰቡ ላይ አንድ ሺህ ፖስታዎችን በማጥፋት ክስ ተመስርቷል። መረጃዎች እንደሚያሳዩት ፖስተኛው ለፉት 17 ዓመታት ፖስታዎችን በቤቱ ሲያስቀምጥ ነበር።

ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ ሶስት ዓመት እስር እና አራት ሺህ ስድስት መቶ ዶላር ቅጣት ይጠብቀዋል እየተባለ ነው።

ተያያዥ ርዕሶች

በዚህ ዘገባ ላይ ተጨማሪ መረጃ