የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀትና የልብ ህመም ተጋላጭ ናቸው ተባለ

የምታለቅስ ደጋፊ Image copyright Chris Brunskill Ltd/Getty Images

አንድ የጥናት ተቋም ባወጣው መረጃ መሰረት የእግር ኳስ አፍቃሪዎች ለከባድ ጭንቀት ይጋለጣሉ፤ የሚደግፉት ቡድን ሲሸነፍ የሚሰማቸው ስሜትም ለልብ ህመም ያጋልጣቸዋል ተባለ።

በምሳሌነት ደግሞ በ 2014 ቱ የዓለም ዋንጫ ብራዚል በጀርመን 7 ለ 1 በተሸነፈችበት ወቅት በርካታ ብራዚላውያን ለከባድ የጤና እክሎች መጋለጣቸውን ጥናቱ ጠቅሷል።

ጥናቱ እንደጠቆመው በወቅቱ የብራዚል ደጋፊዎች ብሄራዊ ቡድናቸው በሰፊ የግብ ልዩነት መሸነፉን ተከትሎ ለጭንቀት የሚያጋልጡ ሰውነት የሚያመርታቸው ሆርሞኖች መጠን መጨመር ታይቶባቸዋል።

አሠልጣኝ አብርሃም መብራህቱ፡ "የመጣውን በጸጋ መቀበልና መዘጋጀት ነው"

ከኮከብ እግር ኳስ ተጫዋችነት - ፖለቲካ - ወደ ታክሲ ሹፌርነት

ይህ ደግሞ አደጋ አለው ይላሉ ተመራማሪዎቹ፤ የደም ግፊታቸው ጨምሯል፤ እንዲሁም ልባቸው ተጨንቃ ልትፈነዳ ደርሳም ነበር ብለዋል።

ምንም እንኳን በርካቶች ወንዶች ለእግር ኳስ የበለጠ ፍቅር ስላለቸው ለበለጠ ጭንቀት ይጋለጣሉ ብለው ቢያስቡም፤ ተመራማሪዎቹ አገኘነው ባሉት መረጃ መሰረት ግን በሴትና በወንድ እግር ኳስ ደጋፊዎች የጭንቀት መጠን ላይ ልዩነት አልተገኘም።

''ለረጅም ዓመታት ድጋፋቸውን ለአንድ ቡድን ብቻ አድርገው እግር ኳስን የሚመለከቱ የኳስ አፍቃሪዎች ደግሞ ለበለጠ አካላዊ መዛልና ጭንቀት የተጋለጡ ናቸው'' ይላሉ የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የጥናቱ ተሳታፊ ዶክተር ማርታ ኒውሰን።

እሳቸው እንደሚሉት አልፎ አልፎ ቡድናቸውን ለመደገፍ እግር ኳስን የሚመለከቱ ሰዎች ጭንቀት ቢያጋጥማቸውም እንደ ቋሚ ደጋፊዎቹ ከፍተኛ አይደለም።

ለረጅምና ተከታታይ ጭንቀት የሚጋለጡ ሰዎች ተከታዩቹ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል፡

  • የተወጠሩ የደም ቧንቧዎች
  • የደም ግፊት መጨመር
  • የልብ መድከም

ከባድ የእግር ኳስ ፍቅር ያለባቸው ደጋፊዎች ቡድናቸው ሲሸነፍ ወይም ግብ ሲቆጠርበት የሚያጋጥሙ የልብ ድካም በሽታዎች ከጊዜ ጊዜ እየጨመሩ መምጣታቸውንም ጥናቱ ጠቁሟል።

"በአንድ ጨዋታ ሰባት ግቦችን በማስቆጠር ታሪክ መስራቴ አስደስቶኛል" ሎዛ አበራ

የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎቹ ለማስረጃነት እንዲጠቅማቸው በእግር ኳስ ፍቅር ያበዱ 40 ሰዎችን ከመረጡ በኋላ ከዓለም ዋንጫ ጨዋታዎች በፊትና በኋላ ምራቃቸውን በመውሰድ መርምረዋል።

ባገኙት መረጃ መሰረትም በተለይ ደግሞ ከግማሽ ፍጻሜ በኋላ የደጋፊዎቹ የጭንቀት መጠን በእጅጉ ከፍ ብሏል።