የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን እና የመንግሥት ዝምታ

የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን እና የመንግሥት ዝምታ

የታገቱት ተማሪዎች፡ የቤተሰብ ሰቀቀን እና የመንግሥት ዝምታ።

ከሚማሩበት የደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ለደህንነታቸው በመስጋት ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ ሳለ ማንነታቸው ባልታወቀ ወጣቶች የታገቱ ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም ምላሽ አላገኘም።

ተማሪዎቹ ከታገቱ 50 ቀናት አልፏቸዋል። ወላጆች ልጆቻቸው መታገታቸውን ከሰሙ አንስቶ ለሚመለከታቸው አካላት ልጆቻቸውን እንዲመለሱላቸው ሲጠይቁ ቆይተዋል።

ይሁን እንጂ መንግሥት በጉዳዩ ላይ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ አልሰጠም።

የተማሪዎችን መታገት ተከትሎ ከቀናት በፊት ወደ አዲስ ዘመን ያቀናው የቢቢሲ ዘጋቢ ከተማዋ ሃዘን እንዳጠላባት ይናገራል።

የታጋች ቤተሰቦች ፊታቸው ጠቁሮ በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ሆነው ነው ያገኘኋቸው የሚለው ዘጋቢያችን ቤተሰቦችን ማነጋገር እጅግ አሳዛኝ እንደነበረም ያስረዳል።